Agriculture and natural resources management

Agriculture and natural resources management "Sharing sustainable and profitable farming for all."

በዳንግላ ወረዳ፣ በጉምድሪ፣ ጉልት፣ ውፍጣ ዳጢ እና ድምሳ ቀበሌዎች በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /FSRP/ በጀት ድጋፍ የምግብ ስርዓት ጥራትን ማሻሻልና የመሬት ለምነት እድገት ለማመ...
09/08/2026

በዳንግላ ወረዳ፣ በጉምድሪ፣ ጉልት፣ ውፍጣ ዳጢ እና ድምሳ ቀበሌዎች በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /FSRP/ በጀት ድጋፍ የምግብ ስርዓት ጥራትን ማሻሻልና የመሬት ለምነት እድገት ለማመቻቸት እየተጠናከረ ነው። እንዲሁም የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማጠናከር የሳይንሳዊ አረንጓዴ ማዳበሪያዎችን አሰራር ትግበራ የሚያሳይ ከፊል ገጽታ ።
source, FBC

በአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ጓንጓ ወረዳ፣ አንጓይ ቀበሌ፣ ልዩ ጎጥ ኩረይታ በሚገኘው አካባቢ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በወረደው ከባድ በረዶ የታጀበ ዝናብ ምክንያት የህብረተሰቡ የበቆሎ ማሳ...
07/08/2026

በአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ጓንጓ ወረዳ፣ አንጓይ ቀበሌ፣ ልዩ ጎጥ ኩረይታ በሚገኘው አካባቢ፣ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በወረደው ከባድ በረዶ የታጀበ ዝናብ ምክንያት የህብረተሰቡ የበቆሎ ማሳ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
በአሁኑ ወቅት ለአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ዋስትና መሠረት የነበረው የበቆሎ ሰብል በመውደሙ ህብረተሰቡ በከፍተኛ ሀዘንና ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ።

 #ሐምሌ 28/11/2018ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትአዲስ አበባ​ጉዳዩ፦ በውል ስምምነት መሰረት የሚገባንን የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ ከተያዘ...
04/08/2026

#ሐምሌ 28/11/2018
ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ
ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
አዲስ አበባ
​ጉዳዩ፦ በውል ስምምነት መሰረት የሚገባንን የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ ከተያዘብን ጊዜ አንፃር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን ስለመጠየቅ
​እኛ ለሀገራችን ህገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ሂደት ስኬት ስንል የተጣለብንን ሀገራዊ አደራ በከፍተኛ ታማኝነት፣ ታታሪነትና ኃላፊነት ተወጥተን ስራችንን ያጠናቀቅን የምርጫ አስፈጻሚዎች ነን።
​በስራችን ወቅት የተደቀኑብንን የደህንነት ስጋቶች፣ የትራንስፖርትና የእንግልት ገጽታዎች ሁሉ ችለን ሀገራዊ ጥሪን አክብረን አገልግሎት የሰጠን ቢሆንም፣ ስራችንን አጠናቅቀን ከተመለስን ከሁለት ወራት በላይ አልፎናል። ሆኖም ግን በውላችን መሰረት ሊከፈለን የሚገባው ህጋዊ አበልና ክፍያ እስካሁን አልተፈጸመልንም።
​በዚህ ሂደት ውስጥ ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) ያቀረብን ቢሆንም፣ ተቋሙ አወንታዊም ሆነ አሉታዊ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን «አለ» ወይም «የለም» ሳይል ሙሉ በሙሉ ዝምታን መርጧል። ይህ ተቋማዊ ምላሽ አልቦነት እና የውል ስምምነት አለማክበር በበርካታ የምርጫ አስፈጻሚዎችና በቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ፈጥሯል።
​የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር፤
​የሀገር አደራን በታማኝነት የተወጣ ዜጋና ሰራተኛ ድካሙና የላቡ ዋጋ በዚህ መልኩ ችላ ሊባል እንደማይገባውና ለህግ የበላይነትም አርአያ መሆን የሚገባው ተቋም ውሉን ማክበር እንዳለበት እናምናለን። በመሆኑም ይህ በርካታ ዜጎችን ያንገላታውና ምላሽ ያጣው የክፍያ ጥያቄ በእርስዎ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እና አዛኝነት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲያገኝና ህጋዊ አበላችን እንዲፈጸምልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
​ከታላቅ አክብሮት ጋር!
​የምርጫ አስፈጻሚዎች
#የኮንትራት የኮንትራት ሠራተኞች ድምጽ

ይህ ልጅ በ2011 ዓ.ም ቢመረቅም እስካሁን ድረስ በሚወደው የግብርና ሙያ ሥራ ሳያገኝ ሰባት ዓመታት ሞልተዋል።አሁን ደግሞ በእናንተ በኩል የሥራ ዕድል Challenge ቢጀምር ምን ትላላችሁ?
31/07/2026

ይህ ልጅ በ2011 ዓ.ም ቢመረቅም እስካሁን ድረስ በሚወደው የግብርና ሙያ ሥራ ሳያገኝ ሰባት ዓመታት ሞልተዋል።
አሁን ደግሞ በእናንተ በኩል የሥራ ዕድል Challenge ቢጀምር ምን ትላላችሁ?

Temperature Temperature is the degree of hotness or coldness of the air at a particular place and time. It is measured w...
27/07/2026

Temperature

Temperature is the degree of hotness or coldness of the air at a particular place and time. It is measured with a thermometer, usually in °C (Celsius), °F (Fahrenheit), or K (Kelvin).

👉Factors Affecting Temperature

1. Latitude

The most important factor.

Temperatures decrease from the Equator towards the Poles because the Sun's rays become more slanting.

Example: Singapore is hotter than Greenland.

2. Altitude

Temperature decreases with increasing height.

Normal lapse rate: 6.5°C per 1,000 m (or 1°C per 165 m).

3. Distance from the Sea (Continentality)

Coastal areas have moderate temperatures due to the sea's influence.

Interior areas experience greater extremes of heat and cold.

4. Ocean Currents

Warm currents raise the temperature of nearby coasts.

Cold currents lower coastal temperatures.

5. Prevailing Winds

Winds carry the temperature characteristics of their source region.

Maritime winds are generally moist and moderate; continental winds are drier and more extreme.

6. Cloud Cover

Clouds reduce daytime heating by reflecting sunlight.

At night, they reduce heat loss, keeping temperatures higher.

7. Slope and Aspect

Sun-facing slopes receive more solar radiation and are warmer.

In the Northern Hemisphere, south-facing slopes are warmer; in the Southern Hemisphere, north-facing slopes are warmer.

8. Nature of the Surface

Dark surfaces absorb more heat than light-colored surfaces.

Urban areas are warmer than rural areas due to the urban heat island effect.

9. Vegetation

Dense vegetation lowers temperature through shade and evapotranspiration.

Areas with little vegetation heat up more quickly.

10. Atmospheric Conditions

Humidity, dust, aerosols, and greenhouse gases influence the amount of heat absorbed and retained in the atmosphere.

ዛሬ የእኔ ንብረት በሆነው የበቆሎ ማሳ ላይ ዩሪያ (top dressing) እየጨመርኩ ነው።እስኪ ግብርና ባለሙያ ሆናችሁ የራሳችሁ የበቆሎ ማሳ ያላችሁ ልምዳችሁን አካፍሉን?
24/07/2026

ዛሬ የእኔ ንብረት በሆነው የበቆሎ ማሳ ላይ ዩሪያ (top dressing) እየጨመርኩ ነው።
እስኪ ግብርና ባለሙያ ሆናችሁ የራሳችሁ የበቆሎ ማሳ ያላችሁ ልምዳችሁን አካፍሉን?

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ በሰሜን ደገራ ቀበሌ ነፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለው  ከባድ ዝናብ በቤትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የጓንጓ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወ...
23/07/2026

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ በሰሜን ደገራ ቀበሌ ነፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በቤትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የጓንጓ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።
******************//******************
ሐምሌ16/2018 ዓ.ም (ጓንጓ ኮሙዩኒኬሽን )

በጓንጓ ወረዳ በሰሜን ደገራ ቀበሌ በቀን 15/11/2018 ዓ.ም ነፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በቤትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የጓንጓ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።

የጓንጓ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው አምሳል በሰሜን ደገራ ቀበሌ በቀን 15/11/2018 ዓ.ም ነፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በቤትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልፀው ሁሉም የግብርና ባለሙያዎች በየ አካባቢ ክስተቱን በመከታተል አርሶ አደሮች አማራጭ ሰብል እንዲጠቀሙ ከጎኑ ሆኖ ምክረ ሀሳብ በመስጠት ማህበረሰቡ መሬቱን ፆም እንዳያሳድር ማድረግ እንደለበት አሳስበዋል ።

ኃላፊው አክለውም አርሶ አደሮቹ ቶሎ የሚደርሱ ሰብሎችን በመተካት ጉዳቱን መሸፈን እንዳለባቸው እና ሌሎቹንም ሰብሎች ቀድሞ በመዝራት ከዝናብ ሁኔታ ጋር አብረው መራመድ መቻል እንዳለባቸውና የግብርና ሙያተኞችና ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያድርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ምንጭ ጓንጓ ኮሚኒኬሽን

‎ሰማዩ በደመና ተሸፍኖ ዝናብ ሲጥል የህይወትና የበረከት ማብሰሪያ መሆኑ ቀርቶ፣ ከሰማይ የወረደው ድንገተኛና ከባድ በረዶ የሰዎችን ድካም በቅጽበት ወደ ከንቱነት ቀይሮታል።‎‎ባለፈው ሐምሌ 1...
23/07/2026

‎ሰማዩ በደመና ተሸፍኖ ዝናብ ሲጥል የህይወትና የበረከት ማብሰሪያ መሆኑ ቀርቶ፣ ከሰማይ የወረደው ድንገተኛና ከባድ በረዶ የሰዎችን ድካም በቅጽበት ወደ ከንቱነት ቀይሮታል።
‎
‎ባለፈው ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በባንጃ ወረዳ በሚገኙት የጋጋስታ እና የአተታ ቀበሌዎች ላይ የተከሰተው ያልተጠበቀ የተፈጥሮ አደጋ፣ የበርካታ ዜጎችን ህይወትና ኑሮ አናግቷል።
‎
‎ከዝናብ ጋር ተቀላቅሎ የወረደው ይህ ያልተለመደና ከባድ በረዶ፤ በመሬት ላይ የደረሰውን ለምለም ሰብል በመጥረግ፣ የመኖሪያ ቤቶችን እና ንብረቶችን በማውደም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ድንጋጤ ፈጥሯል።
‎
‎አርሶ አደሩ ለወራት ላባቸውን አንጠፍጥፈው ያለሙዋቸው ማሳዎች በበረዶው ንብርብር ስር ተቀብረዋል። የበቀሉትንም ሆነ እያደጉ ያሉ ሰብሎች ሙሉ በሙሉ በመውደማቸው የዓመቱን የምግብ ዋስትና ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል።አርሶ አደሮችም የሚመለከተው አካል ፈጥኖ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል
‎
ምንጭ:-‎ባንጃ ኮሙኒኬሽን
‎ሐምሌ 2018ዓም
‎

 በአዊ ብሔረሰብ ዞን በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ እየተስተናገደ ቢሆንም፣ በቅርብ ቀናት የፎል አርሚወርም (Fall Armyworm) ተባይ በቆሎ ማሳዎችን እያጠቃ መሆኑ መረጃ ደርሶናል።...
30/06/2026


በአዊ ብሔረሰብ ዞን በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ እየተስተናገደ ቢሆንም፣ በቅርብ ቀናት የፎል አርሚወርም (Fall Armyworm) ተባይ በቆሎ ማሳዎችን እያጠቃ መሆኑ መረጃ ደርሶናል። ይህ ተባይ በወቅቱ ቁጥጥር ካልተደረገበት በቆሎ ማሳውን እስከ 100% ድረስ ሊያወድም ይችላል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማሳውን በየጊዜው በመመርመር ተባዩን በእጅ በመልቀም ወይም ከግብርና ባለሙያዎች በሚሰጥ ምክር መሠረት ተገቢውን የቁጥጥር ዘዴ እንዲተገብሩ እናሳስባለን።

29/06/2026

በአዊ ብሔረሰብ ዞን በጓንጓ እና በባንጃ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ከንጉድጓድ በረዶ ጋር የተቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ፣ በእርሻ መሬቶችን እንዲሁም በወንዞች ዳርቻ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከጎርፍ እና ከሌሎች ተያያዥ አደጋዎች ራሳቸውንና ንብረታቸውን በመጠበቅ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

Address

Adis Ababa
Addis Ababa
BOLE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agriculture and natural resources management posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share