ዛውያ ቲቪ Zawya TV

ዛውያ ቲቪ Zawya TV በተግባራዊ ጥሪ (ዳዕዋ) የእስልምናን ውበት በየቤቱ ለማድረስ የሚተጋ የቴሌቪዥን ጣቢያ

   በቅርብ ቀን በሚንበር ቲቪ!  ★ ★ ★Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000   !
30/05/2025




በቅርብ ቀን በሚንበር ቲቪ!

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
!

የሃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የምክክር አጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል         ዛውያ ቲቪ፣ግንቦት 22/2017የሃይማኖት ተቋማትን የሚያሳትፈው ...
30/05/2025

የሃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የምክክር አጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

ዛውያ ቲቪ፣ግንቦት 22/2017

የሃይማኖት ተቋማትን የሚያሳትፈው ሀገራዊ የምክክር አጀንዳዎችን የማሰባሰቢያ መድረክ ዛሬ ግንቦት 22/2017 ዓል በሚሊንየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል ፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የላቀ ድርሻ እንዳለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ገልፀዋል ።ሀገራዊ ምክክር የሃሳብ ልዩነቶችን ተቀራርቦ በውይይት መፍታት የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ዛሬ በፌደራል ተቋማትና ማህበራት ደረጃ እያካሄደ የሚገኘው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ 14ኛ መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል። ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደትን ማካሄድ እንዲሁም በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ እንደሚቀሩትም ገልጸዋል።

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የፌዴራል ተቋማትና የማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የነጻነት ተምሣሌት ፋና ወጊ የበርካታ ቋንቋ፣ ባህል እና እሴት ሀገር ናት ብለዋል።

ኮሚሽኑ ዛሬ በፌደራል ተቋማትና ማህበራት ደረጃ እያካሄደ የሚገኘው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ 14ኛ መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደትን ማካሄድ እንዲሁም በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ እንደሚቀሩትም ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ወደ ዋናው የምክክር ሂደት ለመግባት የመዳረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በጉዞው አካታችነትና አሳታፊነትን ተግባራዊ እያደረገ መምጣቱን ተናግረዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የላቀ ድርሻ እንዳለውም ነው ዋና ኮሚሽነሩ የተናገሩት።

በዚህ መድረክ ላይ የእስልምና መምህራን እና የታሪክ አጥኚዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች በተገኙበት መድረክ ላይ ከ38 ተቋማት የተመረጡ ከ800 በላይ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል ።

በዛሬ ዕለት የተጀመረው የምክክር ምዕራፍ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓል ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ

800 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች ድጋፍ ተደረገ             ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 21/2017የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ...
29/05/2025

800 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች ድጋፍ ተደረገ

ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 21/2017

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት ከኦርፍን ኤድ አሜሪካ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ አስተባባሪነት የተገኘ የመድሀኒትና የህክምና ግብአቶች ለአምስት የመንግስት ሆስፒታሎች የርክክብ ስነስረዓት ዛሬ ግንቦት 21/2017 ዓል ተከናውኗል።

ለሆስፒታሎቹ የተበረከቱት የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች አሜሪካ ከሚገኘው ኦርፋን ኤድ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ አስተባባሪነት የተገኙ ናቸው።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የርክክብ ስነ ሥርዓት ላይ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹን ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለጅማ እስፔሻላይዝድ (ኦሮሚያ )ለደሴ እስፔሻላይዝድ ፣ለገለምሶ ሆስፒታል ፣ለሐሰን ኢንጃሞ ና ለኢንጌ የጤና ተቋማት ተወካዮች አስረክበዋል።

ሼይኽ ሐጂ በርክክቡ ወቅት ድጋፉን ያደረጉትን እና በሂደቱ ላይ አስተዋፅዖ የነበራቸው ግለሰቦችን፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን አመስግነዋል።

ክቡር ሸይኽ ሐጂ መድኃኒቶቹና ግብዓቶቹ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ የጤና ሚኒስቴር ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል።

በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ መንግሥት የጤና አገልግሎቱን እያሰፋ መኾኑን ተናግረው ድጋፉ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል።

የጤና ጥበቃ ስራ የሁሉም ትብብር የሚጠ ይቅ ተግባር መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ያደረገው ድጋፍ በተለይ ከፍለው መታከም የማይችሉ ዜጎችን ጫና እንደሚያቃልል ዶክተር መቅደስ ተናግረዋል።

የሕክምና ቁሳቁሶቹን ድጋፍ አስመልክቶ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ እንደገለፁት ኦርፋን ኢን ኒድ አሜሪካ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት እንደሐገር ሐገራችን የሁላችንን ድጋፍ ያስፈልጋታል ብለዋል።

ይህንን የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በአሜሪካ ሀገር በማስተባበር አቶ ፈትሁዲን ኢብራሒም እንዲሁም ሀገር ቤት እስኪደርስ ድረስ የትራንስፖርት ወጪውን በመሸፈን በድር የሙስሊሞች ድርጅት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም በሐገራችን ለሚገኙ የመንግስት ጤና ተቋማት ከሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ. ግብረ ሰናይ ድርጅት በተገኘ ድጋፍ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ማከፋፈሉን ዑስታዝ አቡበከር ተናግረዋል።

በመጨረሻም የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ሀገር ቤት እንዲገባ ሚና ለነበራቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች የሰርትፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

ኢማም አል ቡኻሪ የሸሪዓ እና ዓረበኛ ቋንቋ ኮሌጅ የሴት ዳዒያት ማዕከል መሰረተ          ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 20/2017የኢማም አል ቡኻሪ የሸሪዓ እና ዓረበኛ ቋንቋ ኮሌጅ የሴት ዳዒያት...
28/05/2025

ኢማም አል ቡኻሪ የሸሪዓ እና ዓረበኛ ቋንቋ ኮሌጅ የሴት ዳዒያት ማዕከል መሰረተ

ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 20/2017

የኢማም አል ቡኻሪ የሸሪዓ እና ዓረበኛ ቋንቋ ኮሌጅ የሴት ዳዒያት ማዕከል ዛሬ ግንቦት 20/2017 ዓል ተመስርቷል።

በምስረታ መረሀ ግብሩ ላይ የኮሌጁ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ኡስታዝ ሰለሀዲን መለስ፣ የኢትዮጵያ የኡለማዎች ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ጀይላን ኽድር፣ አሊሞች ፣ኡስታዞች፣ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የኢማም አል ቡኻሪ የሸሪዓ እና ዓረበኛ ቋንቋ ኮሌጅ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ኡስታዝ ሰለሀዲን መለስ እንደገለፁት ኮሌጁ በትምህርት ፣በኢልም እንዲሁም በዘረፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።

የምስረታ አላማውም ዳዕዋን ተደራሽ ለማድረግ በሚያግዝ እውቀትና ክህሎት የበለፀጉ የሴት ዳዒያትን ማብቃት፣ በሴት ዳዒያት መካከል አውንታዊ ትስስር ማጎልበት እና ልምድ ለመለዋወጥ የሚያስችል ከባቢን ማመቻቸት፣የድግሪ እና ድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማዘጋጀት፣ኢስላማዊ ግንዛቤን በህብረተሰቡ ውስጥ በማስፋፋት ረገድ አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

የቅበላ መስፈርቱ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀች ወይም (8ኛ ክፍል ሙሉ ቁርዓን ከመሀፈዝ ጋር ፣የቅበላ ፈተናውን ከ60 % ባላነሰ ውጤት ማለፍ የምትችል፣ የኮሌጁን ህግና ደንብ ለማክበር ዝግጁ የሆነች፣ ለትምህርቱ በቂ ጊዜን መስጠት የምትችል ፣እድሜ ከ 15-35 ፣አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የምትችል መሆን እንዳለበት ተገልጿል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

28/05/2025

የጋሸናው መስጅዳችን ድጋፍ 1ሚሊዮንን ተርሻግሯል።

አሁንም ድጋፋችን ይሻል በአላህ ፈቃድ እንቀጥላለን

ንግድባንክ
1000605055064
ዳሸን
292784487272711
አቢሲንያ
174560404

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የምዝገባ መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ተከናወነ       ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 19/2017የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላ...
27/05/2025

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የምዝገባ መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ተከናወነ

ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 19/2017

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ጽ/ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የምዝገባ መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ዛሬ ግንቦት 19/2017 ዓል በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።

የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ዓብዱልዓዚዝ ኢብራሂም ባደረጉት ንግግር በጥር 24/2017 ጠቅላይ ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ጉባኤ እርሳቸው የሚመሩት ዘጠኝ አባላት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ከተቋቋመ በኋላ በተሰሩ ስራዎች እንዲሁም ቀጣይ ተግባራትን የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ምርጫውን ለማካሄድ በሀገር አቀፍ በአራት ክላስተር መደራጀቱን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ይፋ ባደረገው የምርጫ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ቀጣዩ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምርጫ የሚካሄደው በሁሉም ክልል እና የከተማ አስተዳደሮች ሲሆን ምርጫውን ለማከናወን የምርጫ አስፈጻሚ አካላት የሚቋቋሙት በፌዴራል፣ በክልል/የከተማ አስተዳደር፣ የዞን/ልዩ ዞን/ ክፍለ ከተማ/ ዲያስፖራ ቅርንጫፍ፣ የወረዳ/ ልዩ ወረዳ/ የቀበሌ እንዲሁም የመስጂድ በሚል አደረጃጀት እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በዚህም በፌዴራል ደረጃ ዘጠኝ፣ ለክልል/ከተማ አስተደደር ሰባት፣ ለዞን/ክፍለ ከተማ እና ዲያስፖራ አምስት እንዲሁም ለቀበሌና መስጂድ ደግሞ ሦስት ነው፡፡

በመረሃ ግብሩ ላይ የክልል ተወካዮች የምርጫ ሰነድ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን ምርጫውን ለሚዘግቡ መገናኛ ብዙኃን የዘገባ ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የምዝገባ መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል        ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 19/2017የኢትዮጵያ እስልምና ጉ...
27/05/2025

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የምዝገባ መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል

ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 19/2017

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ጽ/ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የምዝገባ መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ዛሬ ግንቦት 19/2017 ዓል በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል ።

የግንዛቤ ማስጨበጫና ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱን ወደ አናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

ለ6 መቶ ሺ ሰዎች ተደራሽ የሚሆን የ200 ብር የሶሻል ሚዲያ የገቢ ማሰባሰቢያ  የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ይፋ ተደረገ          ዛውያ ቲቪ፦ ግንቦት 16/2017  እዝነት አካል ጉዳተኛ ...
24/05/2025

ለ6 መቶ ሺ ሰዎች ተደራሽ የሚሆን የ200 ብር የሶሻል ሚዲያ የገቢ ማሰባሰቢያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ይፋ ተደረገ

ዛውያ ቲቪ፦ ግንቦት 16/2017

እዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መረጃ ድርጅት ለ6 መቶ ሺ ሰዎች ተደራሽ የሚሆን የ200 ብር የሶሻል ሚዲያ የገቢ ማሰባሰቢያ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ይፋ ማድረጉን ዛሬ ግንቦት 16/2017 ዓል አሳውቋል ።

እዝነት የአካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መረጃ ድርጅት ከዚህ በፊት ባሳለፈው አራት አመታት በርካታ ችግሮች አጋጥመውት እንደነበር በመግለጫው ላይ ተገልጿል ።

ከችግሮቹ መካከል መኪናና ከኪራይ ቤት ነፃ የሆነ የልጆች መኖሪያ ቤት ለድርጅቱ ከባድ ፈተና ሆኖ እንደነበር ዋና ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

የእዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መረጃ ድርጅት ያለበትን የመኖሪያ ቤት ችግር በተረዱ እህትና ወንድሞች ያለሰለሰ ጥረት ምክንያት አሁን ላይ ችግሩ ተቀርፎ የራሱ የሆነ ለልጆች ምቹ ቦታ ሊሆን የሚችል መኖሪያ ቤት ድርጅቱ ማግኘቱ ተገልጿል።

የተገኘው አዲሱ ቤት የእዝነት የበጎ አድራጎት ድርጅትን አገልግሎት ለማግኘት በተጠባባቂነት ለተመዘገቡ ተደራራቢ ችግር ላለባቸው ህፃናትና ወላጆች መልካም ዕድል ቢሆንም ቤቱን ደረጃውን በጠበቀና ለልጆቹ የሚመች አድርጎ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እድሳትና ግንባታ እንደሚያስፈልገው ዋና ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

በዚህ ለህብረተሰብ በሚጠቅም በጎ አድራጎት ላይ ሁሉም የራሱን አሻራ በማሳረፍ የእዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መረጃ ድርጅት የቆመለትን የፀና አላማ ከግብ እንዲያደርስ የሚችለውን ድጋፍ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።

የገቢ ማሰባሰቢያው ለእዝነት አንድ ጎጆ እንገነባለን በሚል መሪ ሀሳብ ከግንቦት 16 እስከ ሰኔ 16/2017 ዓል የሚቆይ ሲሆን በቀጣይም የተለያዩ የገቢ መርሀ ግብሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

የረመዷን ወር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሙስሊም የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ      ዛውያ ቲቪ፦   ግንቦት 16/2017 የአ...
24/05/2025

የረመዷን ወር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሙስሊም የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ

ዛውያ ቲቪ፦ ግንቦት 16/2017

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በ1446 ዓ.ሂ የረመዷን ወር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሙስሊም የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኤምባሲዎች፣የበጎ አድራጎት ማህበራትና ድርጅቶች የምስጋና እና የእውቅና መረሃ ግብር ዛሬ ግንቦት 16/2017 ዓል በም/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

በምስጋና እና እውቅና መረሃ ግብሩ ላይ የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ ፣ ዋና ፀሀፊው ሼህ ሁሴን በሽር ፣የም/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጁ ሀጂ ሪያድ ጀማል፣እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ ባስተላለፋት መልዕክት ረመዳን ላይ ጥሪውን ተቀብለው ብዙ ስራዎችን ላከናወኑ አላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱ በቀጣይም ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በጋራ እንደሚሰራ እና እንደሚቆም ገልፀዋል።

በመጨረሻም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኤምባሲዎች፣የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የእውቅና እና የሰርትፊኬት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!

23/05/2025

240 ሜትር ኬዚንግ ለአውቃቅር
ጉራጌን አይጥማው ዘመችሃ ተጀምሯል።

አንድ ባለ 5.8 ሜትር ኬዚንግ ዋጋ 52,200 ብር
የአንድ ሜትር ኬዚንግ ዋጋ 9000 ብር
የምንፈልገው ኬዚንግ መጠን 240 ሜትር

0911229537/0993535353

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት 3ኛ መደበኛ የኡለማዎች ጉባኤ ተካሄደ          ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 11/2011  የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር...
19/05/2025

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት 3ኛ መደበኛ የኡለማዎች ጉባኤ ተካሄደ

ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 11/2011

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ግንቦት 11/2011 ዓል በግራንድ ኤሊያና ሆቴል ተካሂዷል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ፣የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ ፣ የኢትዮጵያ የኡለማዎች ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ጀይላን ኽድር ፣ዋና ፀሀፊው ሼህ ሁሴን በሽር ፣አሊሞች ፣ኢማሞች፣እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ መልዕክት ያስተላለፋ ሲሆን በመልዕክታቸውም ኡለማዎች የነብያት ወራሾች መሆናቸውን አንስተው የሙስሊሙ አንድነት እንዲጠበቅ እያደረጉት ላለው አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ አክለውም የዛሬው 3ተኛ ኡለማዎች ጉባኤ ዓላማ የዳዕዋ ስርዓቱ ተግባራት ከከተማ እስከ ወረዳ እንዲሁም መስጂድ ዘልቆ እንዲደርስ ማድረግ፣ ወጣ ያለ እና የተለየ እሳቤዎችን ማርቀቅ፣ለኡለማዎች የመሪነት የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኙ ለማስቻል፣በአካዳሚክ ትምህርት የግንዛቤ አድማስ ለማስፋት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ የዑለማዎች ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ እና የአፍሪካ ዑለማዎች ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ ዶ/ር ጄላን ኸደር 'የምርጫ ሸርዐዊ መሰረት እና የዑለማ አመለካከት' በሚል እንዲሁም በሼህ ኤልያስ አህመድ 'የዑለማ ሚና ለማህበረሰብ አንድነት' የሚል ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ

የሸገር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዘጠኝ መስጃድ ቦታዎች እና የምክር ቤቱ ዋና መስሪያቤት የሚገነባበትን ቦታ ሳይት ፕላን መቀበሉን ገለፀ ።       ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 11...
19/05/2025

የሸገር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዘጠኝ መስጃድ ቦታዎች እና የምክር ቤቱ ዋና መስሪያቤት የሚገነባበትን ቦታ ሳይት ፕላን መቀበሉን ገለፀ ።

ዛውያ ቲቪ፦ግንቦት 11/2011

የሸገር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዘጠኝ (9) መስጂድ ቦታዎች እና የሸገር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና መስሪያ ቤት የሚገነባበትን ቦታ ጨምሮ ባጠቃላይ 10 ሳይት ፕላኖችን ጁመዓ እለት ግንቦት 08/ 2017 መቀበሉን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቋል።

የሸገር መጅሊስ የተቋቋመው በወቅቱ በፊንፊኔ ዙርያ የነበሩ ከተሞችን መንግስት በአንድ ላይ አጣምሮ ታላቋን የሸገር ከተማ በመመስረቱ የመጅሊስ መዋቅርም በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት የመንግስትን መዋቅር ጠብቆ ስለሚሄድ የሸገር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ግንቦት 29 /2015 በፊንፊኔ የኦሮሞ ባህል ማዕከል አዳራሽ 13 ስራ አስፈፃሚ አመራሮች ያሉት ሆኖ በኦሮምያ መጅሊስ እንደተመሰረተ የሚታወስ ነው።

በወቅቱ መንግስት ከሸገር ከተማ መመስረት ጋር ተያይዞ ህጋዊ ሰነድ የላቸውም ያላቸውን ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ የነበረ በመሆኑ በርካታ መስጂዶች ያለ አግባብ በመፍረሳቸው ህዝበ ሙስሊሙ በአንድ ድምፅ ይህንን ተግባር ማውገዙ ይታወቃል ።

የሸገር መጅሊስ በወቅቱ የተቋቋመለት አንዱ እና ዋንኛው ዓላማ ፣ ከመስጂዶች ፈረሳ ጋር የተያያዘ ቢሆንም ፣ ተቋሙን በማደራጀት ላይ የተለያዩ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ።

ለአብነት ያክልም :-
1ኛ. ከመስጂዶች ፈረሳ ጋር ተያይዞ በጠቅላይ ምክር ቤቱ እና በኦሮሚያ መጅሊስ አማካኝነት ከፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት :
1.1. የመስጂድ ፈረሳ እንዲቆም
1.2. በፈረሱ መስጂዶች ምትክ ቦታ እንዲሰጥ
1.3. በመኖርያ አካባቢ ላይ የፈረሱ መስጂዶች በቦታቸው እንዲመለሱ
1.4. ለትልቅ ኢስላማዊ ማዕከል መገንብያ የሚሆን ቦታ እንዲሰጥ
እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮችን በመከታተል በወቅቱ የመስጂድ ፈረሳ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም በማድረግ ፣ መጅሊሱ ከተቋቋመም አንስቶ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር በመወያየት አንድም መስጂድ እንዳይፈርስ አድርጓል ።
2ኛ. በፈረሱ መስጂዶች ጉዳይ ከሚመለከታቸው የፌድራል እና የኦሮሚያ መጅሊስ እንደዚሁም ከመንግስት አካል ጋር ጥናት ማድረግ ።
3ኛ. በከተማዋ የሚገኙ መስጂዶች ፣ መድረሳዎች ፣ የመቃብር ቦታዎች እና ኢስላማዊ ተቋማትን በሙሉ በባለሙያ ኮኦርድኔተር መውሰድ እና ችግሮቻቸውን ለይቶ በማውጣት ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ።
4ኛ. የምክር ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀት ።
5ኛ. የምክር ቤቱን ቢሮ መከራየት እና ማደራጀት ።
6ኛ. የምክር ቤቱን እቅድ እና ሪፖርት ማዘጋጀት ።
7ኛ. በ12ቱም ክፍለ ከተማ መዋቅር መዘርጋት እና ወደ ስራ ማስገባት ።
8ኛ. የምክር ቤቱን የገቢ ምንጭ ማፈላለግ ፣ ስራ አስኪያጅ እና ቋሚ ሰራተኞችን መቅጠር ።
9ኛ. በምክር ቤቱ ስር የተላያዩ የኡለማ ጉባኤ ፣ የወጣቶች ካውንስል ፣ የሴቶች ሊግ፣ የምክር ቤቱን ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ጨምሮ የተለያዩ አደራጃጀቶችን እና ዲፓርትመንቶችን አቋቁሞ ወደ ስራ ማስገባት ።
10ኛ. የ12ቱንም ክፍለ ከተማ መጅሊሶች ወደ ስራ እንዲገቡ ከማድረግ በተጨማሪ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ በየ3 ወሩ መገምገም እና ማበረታታት ።
11ኛ. በሸገር ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ከ360 በላይ ለሚሆኑ የመስጂድ አስተዳደር ኮሚቴዎች ስልጠና መስጠት እና ውይይት ማድረግ ።
12ኛ. ለፈረሱ መስጂዶች ፣ በከተማችን ለተጠየቀው ታላቅ ኢስላማዊ ማዕከል ፣ በየክፍለ ከተሞች ለሚገነቡ ታላላቅ መስጂዶች እና ለሸገር ከተማ መጅሊስ ዋና መስርያ ቤት ዲዛይን እና ፕላን ማዘጋጀት

በዋናነትም ከመስጂጆች ጋር የተያየዙ ጉዳዮችን ለሁለት ተከታተይ አመታት ከመደበኛው የተቋሙ ስራ በተጨማሪ እለት በእለት እየተከታተለ መቆየቱን እና ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ በተለያየ ግዜ ለህዝበ ሙስሊሙ ሲያሳውቅ መቆየቱ ተገልጿል ።

በዚህም መሰረት እለተ ጁሙኣ ግንቦት 6 /2017 የዘጠኝ መስጂዶች ቦታዎች እና የሸገር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና መስርያ ቤት የሚገነባበት ቦታ እንደዚሁም በሸገር ከተማ ለሚገነባው የኦሮሚያ መጅሊስ ዋና መስራያ ቤት የቦታ ሳይት ፕላን ።

ቀሪዎቹ አንድ ታላቅ ኢስላማዊ ማዕከል የሚገነባበት ቦታ ጨምሮ በየክፍለ ከተማዎች ታላላቅ መስጂዶች የሚገነቡበት ቦታዎች እና ሌሎችም ጥያቄዎቻችን በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተጠቅሷል ።

የሸገር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተቋቋመ 2 አመት ሊሞላው በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ብቻ እንደቀሩት ተገልጿል።

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ

Address

Addis Ababa Piyassa, Sumaletera Building 3rd Floor 314
Addis Ababa

Telephone

+251972484848

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዛውያ ቲቪ Zawya TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዛውያ ቲቪ Zawya TV:

Share

Category