05/08/2025
ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
'''"""""""""""""""""""""'""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
የአብይ አህመድ አገዛዝ በሚከተለው የሽብር መንገድ ምክንያት የኢትዮጵያን ወጣቶችን የመኖር፣ የመማር፣ የመስራት እና የመበልፀግ ተስፋ አጨልሞታል። ለወትሮውም በድህነት ውስጥ የሚኖረው ወጣት በሰላም ወጥቶ የማይገባበት አደገኛ ሁኔታ ተፈጥሯል።
የአገዛዙ ካድሬወች እና የወራሪው ሰራዊት መኮንኖች ከህዝብ በሚዘርፉት ገንዘብ የቅንጦት ኑሮ በሚኖሩበት፤
የኑሮ ውድነቱ ጣሪያ ነክቶ ዜጎች ከተማ ውስጥ ሳይቀር በረሃብ የሚያልቁበት ሁኔታ እንግዳ ሳይሆን የተለመደ የሀገሪቱ መገለጫ ሆኗል።
የአብይ አህመድ የጦርነት ፕሮጀክት የነበረውን ኢኮኖሚ መብላቱ ሳያንስ ለሜጋ ፕሮጀክቶች ጭምር ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት በሀገር ስም የሚመጣን ገንዘብ አገዛዙ አማራ ክልል ለሚያደርገው ጦርነት አውሎታል።
የማምረቻ ኢንዱስትሪወች ተዘግተው፣ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሽባ ሆኖ አረመኔው አገዛዝ ለማያልቀው የጦርነት አዙሪት የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
በእነዚህ እና መሰል አገዛዙ በፈጠራቸው ምክንያቶች ስደትን አማራጭ ያደረጉ ወጣቶች በሞት መንጋጋ ማለፍ ምርጫቸው ከሆነ ውሎ ያደረ ጉዳይ ነው።
በመሆኑም በዚህ ዓመት ብቻ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም 48፤ ጥር 10 ቀን 2017 ከ 20 በላይ፤ መጋቢት ወር 2017 ዓ.ም 31 እንዲሁም ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከ60 በላይ ኢትዮጵያዊያን ድህነት እና ጦርነትን በመሸሽ ስደትን መርጠው በጀልባ ሲጓዙ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ አሳዛኝ ክስተትም በአገዛዙ ሚዲያወች በኩል ለይስሙላ እንኳን ሽፋን አይሰጠውም።
የአማራ ፋኖ በጎጃም በዚህ መንገድ ህይወታቸውን ባጡ የሀገራችን ወጣቶች ከፍተኛ ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለፀ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ይመኛል።
የሀገራችን ወጣቶች ከስደት ይልቅ ፀረ- አብይ አህመድ አገዛዝ ትግሎችን ተቀላቅለው የተነጠቀውን ሀገር በትግል ማስመለስ ምርጫቸው እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን!!
አዲስ ትውልድ! አትውልድ! ስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!