Yetneberk Tadele

Yetneberk Tadele NB: Please read our RULES before commenting on this page
1. No hate speech is allowed
2. Do not spam our page with offensive images or videos.

Do not use obscene, rude, crude, or insulting nicknames towards the admin of this page.
3. Do not harass, threaten, embarrass, swear at, sexually harass or abuse another participant.
4. For your safety, please do not post personal information like (ID number, phone number, smart card number) on our wall or in the comments.

5. One-liner comments that are negative, defamatory in nature, or intende

d to incite hostility may be moderated.
6. Duplicate postings (to queries already answered or any efforts at spam) will be viewed as 'flooding' and will be deleted.

7. Responses to any posts or users that are guilty of violating the above rules, and that also violate them, will also be moderated accordingly.

8. Any links posted to this page that don't have anything to do with our objectives will be deleted.

9. This platform is intended to be a space to share News information, political and social criticism especially in Ethiopia not inclined to any of the identity politics or religious groups.

* Please note: If you repeatedly disregard the above rules, you will be banned from our page.

እግዚአብሔር የጀመረውን ስራ ያጠናቅቃል:: ከእኔ የሚፈለገው ትእግስት ብቻ ነው::
18/10/2025

እግዚአብሔር የጀመረውን ስራ ያጠናቅቃል:: ከእኔ የሚፈለገው ትእግስት ብቻ ነው::

I love this kind of newsከፋኖ ጋር ድርድር ሊጀመር ነውበአማራ ክልል ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት ጥረት እያደረኩ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡የአማራ ክልል...
17/10/2025

I love this kind of news

ከፋኖ ጋር ድርድር ሊጀመር ነው

በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት ጥረት እያደረኩ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽ ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ያለውን ግጭት ለማስቆም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያለው ግጭት ሀብት፤ ንብረትና የሰው ነፍስ ላይ ውድመት እያደረሰ ነው፤ ግጭቱ እያደረሰ ያለውን ውድመት በማስቆም የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ግጭቱን በድርድር ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡

ግጭቱን በድርድር ለማስቆም እየተሰራ ያለው ስራ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት አመራሩን ከላይ እስከ ታች ድረስ የማደራጀት፤ የጸጥታ ኃይሉ ላይ ሪፎርም የመስራት፤ የሰላም ጥሪ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

15/10/2025

እንመን!

አ ል ሰ ለ ጠ ን ም !!!!!!!

14/10/2025

ለሀገር ይሞታል! ለድንበር ይሞታል! ለኢትዮጵያ ይሞታል!! ለውስጣዊ የፖለቲካ ልዩነት ግን አይሞትም! ይደራደሯል ይመክሯል ይሟገቷል እንጂ ለሀሳብ ልዩነት በጭራሽ እይሞትም!!

14/10/2025

ሞትህ ማንንም አይጠቅምም! ስለዚህ ለህዝብ ነው የምሞተው አትበል! ማንም ሰው ለኔ እንዲሞትልኝም እንዲገድልልኝም አልፈልግም:: ህይወት ከባድ ብትሆንም ጣፋጭ ናት! ኑር! በህይወት ኑር! ትግል በሚሉት ፈሊጥ ሞተህ ደመ ከልብ አትሁን! ኑርና ባንተ ሞት ተንፈላሰው ሊኖሩ የቋመጡትን እያየህ ተገረም! ብቻ በትግል ስም አትሙት!!!

13/10/2025

እስኪ በማርያም ጦርነቱን አቁሙና ሌላ መፍትሄ ፈልጉ!? በእግዚአብሔር ይሁንባችሁ እርስ በእርስ አንተላለቅ?

ሆሊውድ ሮማንስም ይሁን ሆረር፣ አክሺን ሆነ ድራማ ፊልሞች ሲያመርት በየአጋጣሚው ሁሉ የአሜሪካንን ባንዲራ ያሳያችሁዋል። በተለይ የጦርነት ፊልም ከሆነማ ባንዲራው በጦርነት መሀል በእሳት ውስጥ...
11/10/2025

ሆሊውድ ሮማንስም ይሁን ሆረር፣ አክሺን ሆነ ድራማ ፊልሞች ሲያመርት በየአጋጣሚው ሁሉ የአሜሪካንን ባንዲራ ያሳያችሁዋል። በተለይ የጦርነት ፊልም ከሆነማ ባንዲራው በጦርነት መሀል በእሳት ውስጥ አመድ ለብሶ በእሳት ተያይዞ ወድቆ፣ በደምና በላብ ተነክሮ....በስተመጨረሻ ከፍ ብሎ ደሞቆ ሲውለበለብ ያሳያችሁዋል። እንኳን አሜሪካዊው ፊልሙን ያየ የአለም ዜጋ ሁሉ በአሜሪካ ባንዲራ ፍቅር ይወድቃል፣ የባንዲራው ድል አድራጊነት እና አሸናፊነት ሳያስበው በልቡ ውስጥ ይናኝና በአሜሪካ ይማረካል። እንዲህ እያደረጉ ነው አሜሪካውያን በሀገራቸው የማይደራደሩ ያደረጋቸው፣ በዚህ ሳቢያ ነው አሜሪካ ልዕለ ሀያል ሆና እንድናከብራት የሆንነው። እኛ ሀገር እንዲህ ያለ አጋጣሚ ካለ አንድ ቦታ ብቻ ነው። እሱም ቤተክርስትያን ናት። ቤተክርስትያን ነች ደክሞህ፣ ርቦህ፣ ጨንቆህ ልታማክራት ወደ አጸዷ ስትመጣ፣ በደስታህ በሰርግህ፣ በንግስህ በአል፣ በአመት አውዳመት ሁሉ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ አድርጋ እያውለበለበች ሀገርህን እንድታስባት የምታደርግህ። ኢትዮጵያ ውስጥ በትውልዱ ልብ ላይ የሀገርን ፍቅር የምታትም፣ ተሰደህ ከሀገርህ ብትወጣ ተከትላ መጥታ እያገለገለችህ በዝያውም ሀገር እንደ ሌለው ብቸኝነት እንዳይሰማህ ባንዲራዋን እያሳየች ሀገርህን የምታስታውስህ፣ በስደት የወለድካቸውን ልጆች ያላይዋትን ኢትዮጵያን በባንዲራዋ ስላ የምትሰብካቸው ብቸኛዋ የሀገር ተቋም ቤተክርስትያን ነች! ያውም ሀገር እየገፋቻት፣ እያሳደደቻት፣ ተይኝ እያለቻት በጽኑ ፍቅር ባንዲራዋን ይዛ ለትውልድ የሀገርን ጥቅምና አስፈላጊነት የምትናገር ታላቅ ተቋም ....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ነች! በእውነት ለዚህች የሀገር ካስማ እናት ክብር ይገባታል!!

10/10/2025

I have a dream. የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የተጣባው ተውሳክ ሰማያዊ ኮከብ ከላዩ ተፍቆ የምናይበት ቀን ቀርቧል

'እኔ እንግዲህ ከሀገሬም አልፌ በመላው አለም በደንብ የታወቅሁ ሰው ነኝ። በአለም ደረጃ ዝነኛ ነኝ። ይሁን እንጂ ከሀገሬ ወጥቼ ሰው ሀገር ስሄድና አውሮፕላን ልሳፈር ስሰለፍ " ኢትዮጵያ " ...
09/10/2025

'እኔ እንግዲህ ከሀገሬም አልፌ በመላው አለም በደንብ የታወቅሁ ሰው ነኝ። በአለም ደረጃ ዝነኛ ነኝ። ይሁን እንጂ ከሀገሬ ወጥቼ ሰው ሀገር ስሄድና አውሮፕላን ልሳፈር ስሰለፍ " ኢትዮጵያ " የሚለውን ፓስፓርቴን አውጥቼ ሳሳይ ወደ መጨረሻው ረድፍ ሂድ ነው የሚሉኝ። መጀመርያ አሜሪካኖቹን፣ እንግሊዞቹን፣ የበለጸጉትን ሀገራት ዜጎች አስገብተው ሲጨርሱ ነው እኔ ምገባው። ድሮ ከመጀመሪያው ሰልፍ የነበረችው ሀገራችን አሁን መጨረሻ ቀርታለች። ከሀገር ስንወጣ ያው የዚችው የደሀዋ ሀገር ዜጎች ነን። የኛ አማራ ነኝ፣ ኦሮሞ ነኝ ወላይታ ነኝ ፉክክር ምንም አይፈይደንም። ይህን የሚያውቅልንም የለም። ይልቅ ቶሎ ቶሎ በርትተን ሰርተን ተለውጠን በአለም ፊት የቆሸሸውን የሀገራችንን ስም ብናጸዳ ነው የሚጠቅመን።'

© ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ

07/10/2025

የሰላማዊ ትግል ሁሌም አስፈላኂ ነዉ:: በልደቱ አና በጃዋር የሚመራ ሰላማዊ ትኅል ግን የትም አይኖርም:: እሱ ኮዳ ሲንጠለጠልበት አንተ ከወያኔ ጋር ስታሽቃብጥ የሚያዉቅህ ትዉልድ እስከ ቀራንዬ ቀርቶ እስከ ቀበሌም አይከተልህም:: ሁለት መንግስት አለ እያልክ ሳያነግሱህ ነግሰህበት ጫንቃዉ ላይ ቁጢጥ ልትል ስትቋምጥ ተመልክቶ ዳግም የሚመከተልህ ተስፈኛ አይኖርም:: ትግል ያስፈልጋል:: ሊያሰቅል ሳይሆን ሊሰቀልም የወሰነ መሪ ሁሌም ያስፈልጋል::ከኤርትራና ወያኔ ጋር አብሬ ኢትዮጵያን እወጋለሁ ብሎ ቂልነቱን በአደባባይ ከገለፀዉ ይልቃል ጀምሮ የተዋቡ ቃላትን እና ታሪክን በመደርደር ከተካነዉ የትግራይ ትለምልም አፈ ቀላጤዎች ኢትዮ ፎረምና ርዕዬት ሚዲያም ጋር በመሰለፍ ለኢትዮጵያ የሚበጅ ትግል አይኖርም:: ጋንዲንም ሆነ ማርቲን ሉተርን ፈፅሞ እስካልተረዱት ልደቱ እና ጄዋር ጋር በመተባበርም ሆነ የኢትዮጵያን ግባዕተ መሬት ከሚቋምጡ ሻብያና ስታሊን በኩል ሀገር ይፈርሳል እንጂ ዲሞክራሲ አይወለድም::ለኢትዮጵያ አዲስ ደም እና ቆራጥ ኢትዮጵያዉያን ያስፈልጋሉ:: አባይን ብቻ ብለዉ የሚቆሙ ሳይሆን ሳይሆን ሃሰብን ሊያስመልሱ የሚምቱ ኢትዮጵያዉያን ያስፈልጋሉ;; ጎጠኞች ሳይሆኑ ናሽናሊስቶች ያስፈልጋሉ;; ያኔም ብልፅግና ይንኮታኮታል... ወይም መስመር ይይዛል::
እኔ አይደለሁም ይህን ያልኩት ዶ/ር መኮንን ብሩ ናቸው

07/10/2025

የጦርነቱ ባለቤት ማን ነው? ይህ ቪድዮ ፍንጭ ይሰጣል

05/10/2025

ማንም የማያተርፍበት የእርስ በእርስ ጦርነት ይቁም! በወንበር ዙርያ በግማሽ ቀን ንግግር ሊፈታ በሚችል የፖለቲካ ልዩነት ዜጎቻችንን አናስጨርስ! ይልቅ በጋራ ቆመን የሀገራችንን መጻኢ እድል ፈንታ የሚወስነውን የአሰብ ወደብ በእጃችን በማስገባት የአለም ሀገራት ወደ ተረባረቡበት የቀይ ባህር እናምራ! ኢትዮጵያን እንደ ታሪኳ ታላቅ እናድርጋት! ሀገር አክለን እንደ ሀገር እናስብ!!!!!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yetneberk Tadele posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yetneberk Tadele:

Share

Yetneberk Tadele Page

Yetneberk Tadele is an Ethiopian journalist who worked for several media houses since 2010. He created this page along with www.yeahun.com website to share news information about Ethiopia and Eastern Africa.