Sajeroch TV

Sajeroch TV Sajeroch በኢትዮጵያ 100% ይዘትን በአማርኛ ስርጭት በማስተላለፍ የመጀመሪያው የሬዲዮ-ቴሌቭዥን ስርጭት ነው።

23/12/2022

የአፍሪካ ኅብረት ቡድን በጥቂት ቀናት ውስጥ መቀሌ እንደሚገባ ተገለፀ

▶ የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት የሚገመግመውና የሚከታተለው የአፍሪካ ኅብረት ቡድን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መቀሌ እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪዎች ቡድን ጠቆመ።

👉 የዓለም ዋንጫ ባልተፈቀደለት ሰው የመነካቱን ጉዳይ ፊፋ ሊመረምር ነውባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አንድ የታዋቂ ሰዎች ምግብ አብሳይ ዋንጫውን ይዞ የመታየቱን ጉዳይ...
23/12/2022

👉 የዓለም ዋንጫ ባልተፈቀደለት ሰው የመነካቱን ጉዳይ ፊፋ ሊመረምር ነው
ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አንድ የታዋቂ ሰዎች ምግብ አብሳይ ዋንጫውን ይዞ የመታየቱን ጉዳይ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በመመርመር ላይ መሆኑን አስታወቀ።

ታዋቂው ቱርካዊ ምግብ አብሳይ ኑስረት ጉክቸ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት በሚታወቅበት ስሙ ‘ሳልት ቤ’ ባለፈው እሁድ ከፍጻሜ ጨዋታው በኋላ እንዴት ወደ ሜዳው እንደገባና ዋንጫውን ለመያዝ እንደበቃ ምርመራ ይደረጋል ሲል ፊፋ አስታውቋል።

በዚህ ሰሞን በSajeroch TV የሚመጡ አዳዲስ ካርቶኖች 😀በየእለቱ ምርጥ በሆኑ የልጆች መዝናኛዎች በልዩ የልጆች ፕሮግራማችን ይደሰቱ።Sajeroch TV በመመልከት ይቆዩ! 🧸
23/12/2022

በዚህ ሰሞን በSajeroch TV የሚመጡ አዳዲስ ካርቶኖች 😀
በየእለቱ ምርጥ በሆኑ የልጆች መዝናኛዎች በልዩ የልጆች ፕሮግራማችን ይደሰቱ።
Sajeroch TV በመመልከት ይቆዩ! 🧸

አዲስ ወቅት: አእምሮ አንባቢ 🕵️‍♂️ከሰኞ 14፡30 ጀምሮበSajeroch TV ላይ ብቻ!
06/11/2022

አዲስ ወቅት: አእምሮ አንባቢ 🕵️‍♂️
ከሰኞ 14፡30 ጀምሮ
በSajeroch TV ላይ ብቻ!

ለሁሉም ቤተሰብ የሚሆን ምርጥ መዝናኛየአማርኛ ምርጥ ካርቱኖች ምርጫ ቅዳሜና እሁድ በSajeroch TV!
06/11/2022

ለሁሉም ቤተሰብ የሚሆን ምርጥ መዝናኛ
የአማርኛ ምርጥ ካርቱኖች ምርጫ ቅዳሜና እሁድ በSajeroch TV!

🔘: የትናንቱ የእስራኤል ምርጫ ቤንጃሚን ናታኒያሁ እየመሩ መሆኑን የመራጮች አስተያየት አመለከተበትናንቱ የእስራኤል ብሄራዊ ምርጫ ድምጽ ሰጥተው ከሚወጡ መራጮች የተሰበሰበ አስተያየት የቀድሞ ...
06/11/2022

🔘: የትናንቱ የእስራኤል ምርጫ ቤንጃሚን ናታኒያሁ እየመሩ መሆኑን የመራጮች አስተያየት አመለከተ

በትናንቱ የእስራኤል ብሄራዊ ምርጫ ድምጽ ሰጥተው ከሚወጡ መራጮች የተሰበሰበ አስተያየት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ የሚቀጥለውን መንግሥት ለመመስረት የሚያበቃቸውን ውጤት ሳያገኙ እንደማይቀር ይጠቁማል መባሉን ተከትሎ የእስራኤል ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ “መጨረሻው የታወቀ ነገረ የለም” ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል፡፡

31/10/2022

🔘፡ የሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ተፈናቃዮች ዛሬም ድጋፍ ጥበቃ ላይ ነን አሉ
ከኦሮምያ ክልል ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች ውስጥ በጸጥታ ችግር ተፈናቅለው

በአሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማና ኪረሙ ወረዳ ውስጥ በተለያዩ ስፍራዎች መጠለላቸውን የሚናገሩ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንዳልሆነ አስታወቁ።

መንግሥት በአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው እነዚሁ ተፈናቃዮች ጠይቀዋል፡፡

▶️፡ በኢራን ለሳምንታት የቀጠለው የጎዳና ተቃውሞ እንዲያበቃ የአብዮታዊ ዘብ አዛዥ አስጠንቀቁበጎዳና ላይ የተቃውሞ ሰልፍ የዛሬ ቅዳሜ የመጨረሻው ቀን እንደሚሆን የኢራን ሃያል አብዮታዊ ዘቦች...
31/10/2022

▶️፡ በኢራን ለሳምንታት የቀጠለው የጎዳና ተቃውሞ እንዲያበቃ የአብዮታዊ ዘብ አዛዥ አስጠንቀቁ

በጎዳና ላይ የተቃውሞ ሰልፍ የዛሬ ቅዳሜ የመጨረሻው ቀን እንደሚሆን የኢራን ሃያል አብዮታዊ ዘቦች አስጠነቀቁ። ይህም ይመንግስቱ የጸጥታ አካላት ሃገሪቱን እየናጣት ያለውን ተቃውሞ ለማስቆም ኃይል ለመጠቀም መወሰናቸውን አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

ሞስኮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አደራዳሪነት ስምምነት ከተደረሰበት ከዩክሬን ወደ ሌሎች ሀገራት እህል የመላኩን ትግበራ መቋረጧ ተሰምቷል። ይህ ስምምነት የዓለምን የምግብ ቀውስ እና ዋጋ ...
31/10/2022

ሞስኮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አደራዳሪነት ስምምነት ከተደረሰበት ከዩክሬን ወደ ሌሎች ሀገራት እህል የመላኩን ትግበራ መቋረጧ ተሰምቷል። ይህ ስምምነት የዓለምን የምግብ ቀውስ እና ዋጋ ለመቀነስ የሚያስችል ከ9 ሚሊየን ቶን በላይ እህል ከዩክሬን ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲላክ ይፈቅድ ነበር ።

🔘፡ በሶማሊያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናት በቸነፈር ሊያልቁ ይችላሉ ተባለበሶማሊያ ከዚህ በፊት ባልታየ ቁጥር የገዘፈ የህፃናት ሞት ሊከሰት ይችላል ሲል የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት አድን...
22/10/2022

🔘፡ በሶማሊያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናት በቸነፈር ሊያልቁ ይችላሉ ተባለ

በሶማሊያ ከዚህ በፊት ባልታየ ቁጥር የገዘፈ የህፃናት ሞት ሊከሰት ይችላል ሲል የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ዛሬ አስጠንቅቋል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጄምስ ኤልደር ከጄኔቭ በሰጡት መግለጫ በሶማሊያ በየቀኑ፣ በእያንዳንዷ ደቂቃ አንድ ህፃን በከባድ የተመጣጠነ ምግብ ዕጦት ምክንያት ደክሞ ወደ ጤና ጣቢያ ይወሰዳል ብለዋል።

የቅርብ አሃዞች እንደሚያመለክቱት፣ ባለፈው ነሐሴ ወር ብቻ 44 ሺህ ህፃናት ከተመጣጠነ ምግብ ዕጦት ጋር በተየያዘ ወደ ጤና ጣቢያ ለህክምና ተወስደዋል ሲሉ ቃል አቀባዩ ጨምረው ተናግረዋል። ይህም በእያንዳንዱ ደቂቃ አንድ ህፃን መሆኑ ነው ብለዋል።

🔘፡ በቻድ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ 60 ሰዎች ተገደሉበቻድ የሃገሪቱ ግዜያዊ መሪ የሥልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት ማሥረዘማቸውን ተከትሎ በሁለት ታላላቅ ከተሞች በተደረገ የተቃውሞ ልፍ የፀ...
22/10/2022

🔘፡ በቻድ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ 60 ሰዎች ተገደሉ

በቻድ የሃገሪቱ ግዜያዊ መሪ የሥልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት ማሥረዘማቸውን ተከትሎ በሁለት ታላላቅ ከተሞች በተደረገ የተቃውሞ ልፍ የፀጥታ ኃይሎች ተኩስ ከፍተው 60 ሠዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ከመንግሥት ቃል አቀባይ እንዲሁም ከአስከሬን ማቆያ ሥፍራዎች የተገኘው መረጃ ያሳያል።
እንደ አሶሲዬትድ ፕረስ ዘገባ ከሆነ ሁከቱን ተከትሎም ባለሥልጣናት የሰዓት እላፊ ገደብ ደንግገዋል።

የማዕከላዊቷ አፍሪካ ሀገር ግዜያዊ መሪ ማሃማት እድሪስ ዴቢ በሁለት ዓመት ሥልጣናቸውን ማራዘማቸውን ተከትሎ ነው ተቃዋሚዎች ወደ ጎዳና የወጡት።
የማሃማት እድሪስ ዴቢ አባት ለሦስት አስርት ዓመታት ከገዙ በኋላ ባለፈው ዓመት በነፍሰ ገዳይ ጥይት ህይወታቸው እሲኪያልፍ፣ በቻድ ብዙም ተቃውሞ አይሰማም ነበር።

22/10/2022

🧚‍♀️ የዊንክስ ክለብ

በአስማታዊ ኃይላቸው አጽናፈ ዓለሙን ለመከላከል የመረጡበት የአምስት ጎረምሶች ቡድን። የዊንክስ ክለብ ናቸው.
አዲስ ክፍሎች ቅዳሜና እሁድ 10:00 ላይ

📷፡ የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን እለቃለሁ አሉየእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ በተሾሙ በስድስት ሳምንታቸው ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት አስታወቁ። የምጣኔ...
20/10/2022

📷፡ የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን እለቃለሁ አሉ

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ በተሾሙ በስድስት ሳምንታቸው ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት አስታወቁ። የምጣኔ ሃብት ፕሮግራማቸው ገበያው ላይ በፈጠረው ቀውስና የወግ አጥባቂ ፓርቲያቸውን በመከፋፈሉ ነው ተብሏል።

14/10/2022

🔘፡ ማሊ ውስጥ በደረሰ የአውቶብስ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሞቱ
በማዕከላዊ ማሊ ግዛት የተቀበረ ፈንጂ ላይ የወጣ አንድ አውቶብስ ባስከተለው አደጋ ቢያንስ 11 ሰዎች ሲሞቱ 53 የሚደርሱት ቆስለዋል ሲል የሆስፒታል ምንጮችን የጠቀሰው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ትናንት ዘግቧል፡፡

ፍንዳታው የደረሰው ሞፕቲ በተባለው አካባቢ ባንዲያጋራ እና ጎንዳካ ተብሎ በሚታውቁ ሥፍራዎች መካከል ባለ መንገድ ላይ መሆኑን ተዘግቧል፡፡

13/10/2022

አዲስ ተከታታይ: ሃይዲ 🌸
ሄዲ ተራራ ላይ ከአያቱ እና ከውሻዋ ጋር የምትኖር ቆንጆ ልጅ ነች።
ቅዳሜ በ9፡00 ሳ Sajeroch TV ላይ!

13/10/2022

📰 የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የኦሮምያ ክልል 7.5 ሚሊዮን ተማሪዎችን መመገብ መጀመሩን ሲያስታውቅ የድሬዳዋ አስተዳደርም በሰማኒያ ዘጠኙም የመንግሥት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚመግብበት ፕሮግራም ሊጀምር ማቀዱን አስታውቋል።

12/10/2022

💥 የሸረሪት ሰው ወደ ቤት ይመለሳል
ጊዜው ደርሷል! ፕሪሚየር ነገ 20:00 ላይ
በSajeroch TV ላይ።

Address

Chirkos 04
Addis Ababa
1230

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sajeroch TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category