ተአምኖ ሚዲያ Teamno media

ተአምኖ ሚዲያ Teamno media ይህ ቻናል የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችና ቪዲዮዎች የሚለቀቁበት ነው የዩቲዩብ ቻናላችንንም ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ለመታደግ ጥሪ ቀረበ  | ከኦክስፎርድ ይልቃል፤ ከሀርቫርድ ይቀድማል፤ ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም ከሁሉም ይበልጣል፤ የአእላፍ ኢት...
03/07/2025

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ለመታደግ ጥሪ ቀረበ

| ከኦክስፎርድ ይልቃል፤ ከሀርቫርድ ይቀድማል፤ ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም ከሁሉም ይበልጣል፤ የአእላፍ ኢትዮጵያን ቅዱሳን መገኛ ፈለገ ቅድስና፣ ጥንታዊውና የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ በመባል የሚታወቀው ሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም፣ የዕውቀትና የጥበብ ማአከል፣ የሊቃውንት መፍለቂያ፣ የድርሰትና የትርጓሜ ከፍተኛ ጉባኤ ቤት፣ የአሠረ ምንኵስና አስኬማ መላእክት መገኛ ነው፡፡

ቅዱስ አቡነ ሰላማ የባረኩት፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳሙን የመሠረቱትና ያሳደጉት፣ አቡነ ተክለሃይማኖት የመነኰሱበት፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተማሩበት፣ የእነ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፣ የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ የአቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የአቡነ ሠረቀ ብርሃን፣ የአቡነ በግዑ፣ የአቡነ ብስጣውሮስ እና አእላፍ ጻድቃን በረከትና ቃልኪዳን መካነ ጽድቅ፣ የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የቅኔና የሥነ ጽሑፍ፣ የትርጓሜ፣ የሥነ ጥበብ፣ የዜማና የቅዳሴ ሁለንተናዊ የዕውቀት ምሰሶ፣ መዝገበ አእምሮ፣ መካነ ቅርስ፣ ባህረ ጥበብ፣ ፍኖተ አሚንና የእምነት ምስክር ነው።

ያለማቋረጥ ከ1400 ዓመታት በላይ ተጠብቆ የቆየውን ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ ለመላው ዓለም ማስተዋወቅ ስለሚገባ "በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ ወደ ቀደመ ክብሩ እንመልሰው!" በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 27 እስከ 29 እዚያው ከገዳሙ በቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ ይደረጋል።

ብፁዐን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምህራን፣ ዘማርያን እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የገቢ ማሰባሰቡን ይመሩታል።

ሰኔ 27_29 ቀጠሯችሁን ከእኛ ጋር ያድርጉ የተባለ ሲሆን ለድጋፍ የተዘጋጁ አካውንቶች
• ንግድ ባንክ 1000 294 93 09 26
• አቢሲኒያ ባንክ 262 26 26 26
• ዓባይ ባንክ 26 26
• አማራ ባንክ 26 21 26
• አሐዱ ባንክ 17 17 17 17 10 901

ለበለጠ መረጃ
09 38 22 78 28
09 34 47 80 50
09 39 09 38 03

"እኔ በሰከንድ ሚሊዮኖችን እንዳገኘሁ ሁሉ በሰከንድም ብዙ ሚሊዮን የሚያወጣ ሀብት አጥቻለሁ! ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በመሆኔ ሁሌም አሸንፋለሁ። እንጦጦ ኪዳነ ምህረት በየወሩ አልቀርም!...
23/06/2025

"እኔ በሰከንድ ሚሊዮኖችን እንዳገኘሁ ሁሉ በሰከንድም ብዙ ሚሊዮን የሚያወጣ ሀብት አጥቻለሁ! ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በመሆኔ ሁሌም አሸንፋለሁ። እንጦጦ ኪዳነ ምህረት በየወሩ አልቀርም! "

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ

(MK TV ሰኔ 16 2017 ዓ.ም)

በማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ትናንት ሰኔ 15 2017 ዓ.ም በተዘጋጀው የድህረ ግቢ ጉባኤ ምሩቃን መርሐ ግብር ላይ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተገኝተው ያላቸውን ልምድ እና ተሞክሯቸውን ለወጣቶች ባጋሩበት ወቅት “ከልጅነቴ ጀምሮ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በፈሪሐ እግዚአብሔር ያደግሁ መሆኔ ለስኬቴ መሰረት ነው ብለዋል።

የሁለት ኦሎምፒክ የድል ወርቆቼን የሰጠሁት ለእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ነው። በየወሩም አልቀርም። እሷ ለእኔ ብዙ ነገሬ ናት፤ ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ሰው ሁሌም አሸናፊ እና ጠንካራ ነው ያሉት አትሌት ኃይሌ በተለይም ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ ያገዘኝ በእግዚአብሔር ላይ ባለኝ ከፍተኛ እምነት እንዲሁም ጠንክሬ በመሥራቴ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እኔ በሰከንድ ሚሊዮኖችን እንዳገኘሁ ሁሉ በሰከንድም ብዙ ሚሊዮን የሚያወጣ ሀብት አጥቻለሁ! ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በመሆኔ ሁሌም አሸንፋለሁ ሲሉም አከረለዋል።

አክለውም “እናንተ ወጣቶች በውስጣችሁ ባለው አቅም እና ኃይል ልተሠሩበት ይገባል፤ ለዚህም በመጀመሪያ ራሳችሁን ማሸነፍ ይጠበቅባችኋል፤ ለሥራችሁ ዲሲፕሊንም መታመንና መታገል አለባችሁ። ይህም በሕይወቴ ላሳካኋቸው ስኬቶችና ላስመዘገብኳቸው ተጨባጭ ውጤቶች ጠቅሞኛል በማለት ተሞክሯቸውን አጋርተዋል፡፡

ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን 10ቱ ትእዛዛትን በማክበር እንዲሁም ራሳችንን በማወቅ የምንፈልገውን ስኬት እና ዓላማ ማሳካት እንችላለን በማለት ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ከማኅበረ ቅዱሳን የተበረከተላቸውን የፍቅርና አክብሮት ማስታወሻ ከማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መ/ር ዋሲሁን በላይ ተቀብለዋል፡፡

ከማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

20/06/2025

እጃችን ለገጠሪቱ ቤተክርስቲያን

19/06/2025

ሰኔ 12 አውቶብስ ተራ ደብረ መዊዕ አዲሱ ቅዱስ ሚካኤል እንኳን አደረሳችሁ።

⭕️ሰበር  👉"ትዝታው ሳሙኤል ተከሰሰ"👈የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትየሕግ አገልግሎት መምሪያው ከሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ጋር...
17/06/2025

⭕️ሰበር 👉"ትዝታው ሳሙኤል ተከሰሰ"👈
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
የሕግ አገልግሎት መምሪያው ከሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ
ኮሚቴ ጋር በመሆን አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተ።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ሰኔ ፲ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
********************
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
"""""""""""""""""""""""""""

የቤተክርስቲያናችን ሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐ/ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍለፍ ጠይቋል።

በወንጀል ተጠርጣሪ /ተከሳሽ - አቶ ትዝታው ሳሙኤል
ተጠርጣሪ /ተከሳሹ ነዋሪነቱን በውጪ ሃገር በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣
ለመስደብ እና የምዕመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣ በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን በማለት፣እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በማለት፣ሲቀሰቅስ የቆየ መሆኑን የገለጸው መምሪያው ግለሰቡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የፀሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን ማለቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅድስናየምታ
ከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን > ናቸው በማለት ግለሰቡ የፈጸመውን የወንጀል አድራጎት በመጥቀስም ክስ መስርቶበታል።

መምሪያውና የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴው በአጠቃላይ ሰባት ነጥቦችን ያካተቱ የወንጀል ዝርዘርሮችን በመግለጽም ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ግለሰቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረግ ባቀረበው አቤቱታ ገልጿል።በተያያዘም መምሪያውና የሕግ ባሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴው ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ክትትል በማድረግ ለፍጻሜ እንደሚያበቁት ገልጸዋል።

ከኢ/ኦ/ተ/ሕዝብ ግንኙነት የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

ሎዛ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ልዩ እና ተቀዳሚ ምርጫችንከተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ፕሮግራሞች ጀርባ ያል ትልቅ ስም  ✝️ ሎዛዎች የሚሰሯቸው ስራዎች✝️ልደቶችን✝️ጥምቀተ ክርስትናዎች✝️የቁርባንና የተ...
28/05/2025

ሎዛ ለመንፈሳዊ ህይወታችን
ልዩ እና ተቀዳሚ ምርጫችን

ከተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ፕሮግራሞች ጀርባ ያል ትልቅ ስም ✝️

ሎዛዎች የሚሰሯቸው ስራዎች
✝️ልደቶችን
✝️ጥምቀተ ክርስትናዎች
✝️የቁርባንና የተክሊል ስርጎች
✝️የሽምግልናና የቀለበት ስነስርዓቶች
✝️ኦርቶዶክሳዊ የሚድያ ንቅናቄዎችን
✝️የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሮችን

እና ሌሎች ኦርቶዶክሳዊ ዝግጅቶችን

በማዘጋጀትና በማማከር ከ8 ዓመት በላይ ልምድ ያለው ትልቅ ተቋም ነው✝️

እርስዎም እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች ካለዎት ምርጫዎ ይሁን ሀሳብዎት ያቀልሎታል

ለበለጠ መረጃ 👉🏻0939111115


የማርያምወርቅ ተሻገር

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫበመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶ...
28/05/2025

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ አካሂዷል፡፡
የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና እድገት፣ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋትና ለመንፈሳዊ ልዕልና ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ መስጠት፣ምትክ ለሌለው የሰው ልጅ ሕይወት ባለአደራ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላም ያለማቋረጥ መጸለይ፣ ጸሎተ ምሕላ ማወጅ፣ የሰላምና የአንድነት ጥሪ ማስተላለፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሰላምና ለአንድነት ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሁሉን አቀፍ ሥራ የሚሠሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ” በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
ኮሚቴውም ዘላቂ ሰላምንና አንድነትን ለማስፈን፣ የዜጎችን ሕይወት እየነጠቀ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥረት እንዲያደርግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ባካተተ መልኩ በየደረጃው የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና፣ ውይይቶችንና የጥናት መድረኮችን እንዲያዘጋጅ፤ አፈጻጸሙንም በየሦስት ወሩ ለቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
2. ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የትርጓሜ መጻሕፍትና የሴሚናሪ ደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ዲግሪ እንዲሆን በተወሰነው መሠረት በመማር ላይ ያሉትና በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው በመመረቅ ቤተ ክርስቲያናችንን በማገልገል ላይ የሚገኙት ምሩቃን ተጓዳኝ ትምህርቱን ተምረው ዲግሪያቸውን ማግኘት እንዲችሉ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እንዲደረግ፣በኮሌጁ የተጀመረው ሁለገብ ሕንፃም በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲጠናቀቅ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3. በገዳማት አስተዳደር መምሪያ አስፈጻሚነት የተደረገው የአንድነት ገዳማት ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ በየዓመቱ እንዲካሄድና የአቋም መግለጫው ላይ የቀረቡት ሐሳቦች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በኩል እየታዩ በቅደም ተከተል እንዲፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስልፏል፡፡
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን እድገትና ሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ በመሆን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ጉልህነት ያለው ሲሆን፣ አሁንም እየተሠራ ባለው የኮሪደር ልማት መርሐ ግብር ላይ ኃላፊነቷን እየተወጣች ትገኛለች፡፡
ይኽን ቋሚ ታሪክ ያልዘነጋው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለግንባታ በሚያመች ሁኔታ አሰባስቦ በመስጠት ለፈረሱ ቤቶች ካሣ በመክፈል፣ በጽርሐ ምኒልክ ሕንጻ ምትክ በነባሩ ቦታ ላይ B+G+4+ቴራስ በመንግሥት በጀት መልሶ እንዲገነባ በማድረጋቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

በይዞታዎቻችንም ላይ ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ለማካሄድ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተሰይሞ ገቢ የማሰባሰብ ሥራው በሕጋዊ መንገድ እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም በፈረሱት ቤቶች ምትክ የተረከብናቸውን ክፍት ቦታዎች በአጭር ጊዜ ማልማት ግዴታ ስለሆነ በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እንደ አባቶቻችሁ የታሪክ ባለቤቶች ትሆኑ ዘንድ ልማቱን በገንዘብና በእውቀት እንድታግዙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
5. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተፈጠረውን የአስተዳደር ችግር አስመልክቶ በብፁዓን አባቶች የሚመራው አጣሪ ልዑክ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ውይይት በማድረግና የሥራ ኃላፊዎቹን በማንሣት ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
ወደፊትም በየደረጃው ያለውን ችግር ማስተካከል ይቻል ዘንድ ችግሩን እያጠና የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

6. ዝክረ ኒቅያ በሚል መሪ ቃል ከመላው ሀገራችን በተወከሉ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መምህራን በተካሄደው ጉባኤና የጥናት ውይይት የቀረበው ምክረ ሐሳብ እጅግ የሚጠቅም የሊቃውንት ድምጽ በመሆኑ፣በነገረ ማርያም፣ በነገረ ክርስቶስና በሌሎችም አስተምህሮዎች ዙሪያ የተሰጡት ሐሳቦች የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜን መሠረት በማድረግ ተብራርቶና ተስተካክሎ፣ የጎደለው ሞልቶ፣ የጠመመው ተቃንቶ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በመጽሐፍ መልክ እንዲታተም፣በሚዲያ ሊተላለፍ የሚገባው አስተምህሮ ደግሞ በሊቃውንት ጉባኤ ብቻ እንዲተላለፍ፣
የሊቃውንት ጉባኤውም በተሟላ የሰው ኃይልና በጀት ተጠናክሮ እንዲደራጅ፣ሀገር አቀፍ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲደረግና የጉባኤው መዋቅር በየአህጉረ ስብከቱ እንዲጠናከር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

7. የመናገሻ አምባ ማርያምና የጋራው ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ጥንታዊ የሆነ ሰፊ ታሪክ ያለው በመሆኑ ሁለቱ ገዳማት በአንድ አበምኔት በአንድነት ገዳም ሥርዓት በጋራ እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

8. በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት መነኰሳትን ከመላክ ጀምሮ፣በአስተዳደራዊና ቀኖናዊ አሠራር ክፍተት ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን በማረምና ሊቀ ጳጳሱን በማዛወር ማእከላዊ መዋቅር እንዲጠበቅ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፣ነባሩ መተዳደሪያ ደንብ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ሰይሟል፤

9. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ልቡና፣በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያገኘቻቸው ዶግማዊ፣ ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሀብቶቿ የሕግ ጥበቃና ከለላ አግኝተው ሃይማኖታዊ፣ታሪካዊና ሁለንተናዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ተከብረውና ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
10. የ2018 ዓ.ም የመደበኛ እና የካፒታል ዓመታዊ በጀት ብር 5,407,415,607.25/አምስት ቢሊየን አራት መቶ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ዐሥራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም/እንዲሆንና የበጀት አርዕስቱ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሕንጻ በተመለከተ የተፈጠረው የአሠራር ግድፈት እንዲታረም፣ዩኒቨርስቲው ከባንክ ጋር የገባው የብድር ውል እንዲቋረጥና የተጀመረውን ሕንፃ በራሱ አቅም እንዲገነባ ሆኖ፤ የቤተ ክርስቲያናችንን አንጡራ ሀብት ማለትም ሕንጻዎችን፣መሬቶችንና ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን በማስያዝ የሚደረጉ ብድሮች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ የሚያደርግ መመሪያ ለሁሉም አህጉረ ስብከት እንዲተላለፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12. የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅትን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት የሥራ ክፍተቱን በማረም በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች እንደየጥፋታቸው እንዲጠየቁና እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
13. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫን አስመልክቶ በሥራ ላይ የነበሩት ብፁዓን አባቶች የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚሠሩ ብፁዓን አባቶችን ለመምረጥ ዕጩዎችን የሚያቀርቡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመሰየም ምልዓተ ጉባኤው ተገቢውን ምርጫ አከናውኗል፡፡
በዚሁም መሠረት ፡-
*. ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ በደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን መርጦ ሰይሟል

*. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪጅነት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣የሸገር ከተማ እና የምስካዬ ኀዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስን መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ሰብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሜኖሶታና የኮሎራዶ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መድቧል፡፡

14. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካልፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚዲያ ያስተላለፏቸው ትምህርቶች ስሕተትና ነቀፋ ያለባቸው መሆናቸውን አምነው ቅዱስ ሲኖዶስንና መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታ በመጠየቅ ሊቃውንት ጉባኤ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቅስ ያቀረበውን አስተምህሮ የተማሩት የሚያምኑትና የሚያስተምሩት መሆኑን በመግለጻቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስቱን አባቶች ይቅርታ ተቀብሎ ወደፊት እንዲህ ዐይነት የስሕተት ትምህርት ውስጥ እንዳይገኙና ነቀፋ ያለበትን ትምህርታቸውን በማረምና በማስተካከል ርቱዕ የሆነውን የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ሥርጭት ድርጅት በመቅረብ ትምህርት እንዲሰጡ በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
15. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ በግልና በቡድን ተደራጅተው ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመክፈት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር በወጣ መልኩ የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር የሚጋፋ ፣የአባቶችንና የአገልጋዮችን ተልእኮ የሚያደናቀፍ ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴየና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታየው ግጭትና መፈናቀል ተወግዶ፣የሰው ልጅ የመኖርና የመዘዋወር መብት ተከብሮ፣ ሰብዓዊ ክብሩ ተጠብቆ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በጋራ እንዲኖር፤ አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

ግጭት፣ ጥላቻና ደም መፋሰስ፣ አካል ከማጉደልና ንብረት ከማጥፋት በቀር የሚያመጡት ክብርና ዘላቂ ሰላም ስለሌለ ልጆቻችን ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንድትፈቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋግሞ ጥሪውን በማቅረብ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላምና ዕርቅ እንዲሰፍን በመጸለይ ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ዓመታዊ ጉባኤውን በጸሎት አጠናቋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሕ/ ግንኙነት የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

❗️❗️ሰበር ዜና❗️❗️ብፁዕ አቡነ  ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳ...
23/05/2025

❗️❗️ሰበር ዜና❗️❗️ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ሕዝብ ግንኙነት facebook ገጽ የተወሰደ

እንኳን ደኅና መጡ።
15/05/2025

እንኳን ደኅና መጡ።

❗️❗️ሰበር❗️❗️ሦስቱ ብፁዐን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገቡ።ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር)ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ(ዶ/ር)ብፁዕ አቡነ ያዕቆ...
15/05/2025

❗️❗️ሰበር❗️❗️ሦስቱ ብፁዐን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገቡ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር)
ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ(ዶ/ር)
ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የ2017 ዓ.ም ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ግንቦት 6 በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ...
14/05/2025

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የ2017 ዓ.ም ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ግንቦት 6 በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመክፈቻ መልእክት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
ተአምኖ ሚዲያ
ፎቶ: አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሚዲያ

Address

Addis Ababa
0000

Telephone

+251903149262

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ተአምኖ ሚዲያ Teamno media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ተአምኖ ሚዲያ Teamno media:

Share