
18/07/2025
በአቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ የተከፈተው ክስ ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም ለምን ሆነ???
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መመስረቷ ይታወቃል። አቶ ትዝታው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለዓመታት 365/6 ቀናት በተለያየ ርእስ ሲሳደብ እንደኖረ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። ከ50 ሚሊዮን በላይ አማኝ አላት ተብሎ የሚነገርላትን ቤተክርስቲያን ለዓመታት ሲሰድብ የኖረን ግለሰብ ቤተክርስቲያን "በሕግ ይጠየቅልኝ" ብትልም ሕጉ የሚሰራው ግን ተቋምን ለሚሳደብ ሳይሆን በተለያየ ምክንያት መንግሥትን ለሚወቅስ ለሚተች ብቻ ነው።
ከወር በፊት አንዲት ህጻን ገና በአስተሳሰብ ያልበሰለች በቲክቶክ በጫወታ መሀል የድሬ ደዋን ንዋሪ አለባበስ የሚያጎድፍ ቃላት ተናገረች ተብሎ ከድሬ ደዋ አ/አ ድረስ ለሕግ መከበር ብዙ የደከመ የጸጥታ አካል ከ50 ሚሊዮን በላይ አማኝ የሚከተላትን ቤተክርስቲያን ከፍ ዝቅ እያደረገ ሲሳደብ የነበረን ግለሰብ በሕግ ከመጠየቅም በላይ በሰፊው ቤተክርስቲያንን ይሳደብ ዘንድ በሚልንየም አዳራሽ ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ ፍቃድ ተሰጥቶታል።
እንዲህ ያለ ግለሰብ የትኛውንም ተቋማት ሲሳደብ ሲያንቋሽሽ ህዝብ ከህዝብ ያራርቃል ፣በሀገሪቱ ፍትህ ስርአት ላይም እምነት ያሳጣል።ተበዳይ በሕግ ያላገኘውን ፍትህ በጉልበት ለማግኘት ወደ መሞከር ያሸጋግራል። ይሄ ደግሞ እንደ ሀገር ሰላም ያሳጣል። ህዝብ ከህዝብ ያራርቃል። ተቋም ከተቋም ያናንቃል። ትዝታውን በሕግ አግባብ እንዲጠየቅ ማድረግ ጥቅሙ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ነው። ማንም ተነስቶ የትኛውም ተቋም ላይ የጥላቻ ንግግር እንዳይናገር ያስተምራል።
አቶ ትዝታው ሳሙኤል ቤተክርስቲያንን ለዓመታት እንዴት ሲሳደብ እንደነበር በማስረጃ የተደገፈ ክስ የደረሳችሁ የፍትህ አካላት የቀረበላችሁን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ፍትህን እንድታሰፍኑ እንጠይቃለን ። ይሄን ባታደርጉ ግን ነገ በየ ሚዲያው እየወጣ ተቋማትን የሚሳደብ ትውልድ እንዲበረክት እያመቻቻችሁ እንደሆነ መታወቅ አለበት። ከየትኛውም የሃይማኖት ተቋም ይሁን በአስተምሮት ላይ ከመወያየት በዘለለ የጥላቻ እና የማጥላላት ሀሳብ በሚዲያ ቢያስተላልፍ በሕግ አግባብ መጠየቅ አለበት።
በዚህ የዘገየ የፍትህ ስርአት ላይ ሊጠየቁ የሚገባቸው አካላት
1ኛ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕግ ክፍል ጉዳዩን ምእመኑ ደስ እንዲለው ብቻ ነው የጀመራችሁት ወይስ እውነት ቤተክርስቲያን መሰደቧ አሳስቧችሁ መብቷን ለማስከበር?
2ኛ,በፖለቲካው ሜዳ ላይ ውሃ ቀጠነ የሚለው የሀገሪቱ የፍትህ ስርአት ሃይማኖት ሲነካ ሲሰደብ ሲንቋሸሽ አይመለከተውምን?
3, ፕሮቴስታንታዊ ሃይማኖት ተቋማት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሰድቦ አንቋሾ ዛሬ እንደገና አብራችሁ አምልኮ ለመፈፀም በሚልንየም አዳራሽ ትገኙ ይሆን? ከተገኛችሁ ነገ የእናንተን ተቋም የሚሳደብ ትውልድ ሲመጣ በየትኛው የፍትህ ስርአት ትጠይቁት ይሆን? እና ዛሬ በጋራ ሆኖ ስርአት አልባን ሰው ለፍትህ ማቆም አይሻልምን?
4ኛ, የዚህን ግለሰብ በሕግ መጠየቅ ስታበስሩን የነበራችሁ የቤተክርስቲያኒቱ ሚዲያዎች አሁን ያለበትን የክስ ሂደት ለምን ለምእመኑ እየተከታተላችሁ አታደርሱም?
እኛ ግን እንደ ጀመርን ዛሬም ቤተክርስቲያንን የደፈረ ግለሰብ በሕግ እንዲጠይቅ ደጋግመን እንጠይቃለን ።
መንክር ሚዲያ-Menker Media
መንክር ሚዲያ-Menker Mediaን በተለያዩ የSocial Media Platform ላይ ለመከታተል ከታች የተቀመጠውን Link ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ።
በYou Tube👇👇👇
http://www.youtube.com/
በFacebook 👇👇👇👇
https://www.facebook.com/MenkerMedia21?mibextid=ZbWKwL
በTiktok👇👇👇
tiktok.com/
በTelegram👇👇👇👇
https://t.me/MenkerMedia21
በWhatsApp👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4xtde1NCrPbBLUZA1O