Dolos Ethiopia - News

Dolos Ethiopia - News Dolos News - Ethiopia

አገራችን በአፍሪካ የእንስሳት ሀብት ቁንጮ እንድትሆን ያደረጋት ቅንና ትጉ ሕዝብ ፣ ዛሬ ያለውንና የምንኮራበትን፣ ሕይወቱንም ጭምር ሊያጣ በረሃብ ከሚቀስፍ የመልዐከ ሞት ሠራዊት ጋር ተጋፍጦ ...
24/02/2023

አገራችን በአፍሪካ የእንስሳት ሀብት ቁንጮ እንድትሆን ያደረጋት ቅንና ትጉ ሕዝብ ፣ ዛሬ ያለውንና የምንኮራበትን፣ ሕይወቱንም ጭምር ሊያጣ በረሃብ ከሚቀስፍ የመልዐከ ሞት ሠራዊት ጋር ተጋፍጦ መድረሳችንን የሚጠብቅ ሕዝብ ሆኗል ቦረና፡፡

ይህ በዚች ምድር ተወልዶ ላደገ ሁሉ የእናት ጡት የሆነ ማኅበረሰብ ዛሬ የእንዳንዳችንን አነስተኛ ግን ፈጣን ድጋፍ ይሻል፡፡ አትሌቶች፣ አርቲስቶች ፣ፖለቲከኞች መንግሥታዊና መመንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሁሉ ከሞት መንጋጋ ሊታደጉት ካልተረባረቡ በኅሊና፣ በታሪክና በፈጣሪ የፍርድ ሚዛን ፊት የሚቆሙበት ሠዓት ነው፡፡

ሁሉም ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ዕውቀት ያለው በሀሳቡ፣ ጉልበት ያለውም በጉልበቱ የድርሻውን ለማበርከት ይንቀሳቀስ፡፡ ከፊት ቀድመው በግል፣ በቡድንም ሆነ በድርጅት ለአፋጣኝ ምላሽ ለማስተባበር ጥሪ ከሚያቀርቡልን እውነተኞች ጎን እንሰለፍ፡፡
ወርቃለማሁ ንጋቱ

" የተሰራጨው ሀሰተኛ ወሬ ነው " - የሶማሌ ክልል መንግስትየሶማሌ ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ  በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ላይ " የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው...
18/08/2022

" የተሰራጨው ሀሰተኛ ወሬ ነው " - የሶማሌ ክልል መንግስት

የሶማሌ ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ላይ " የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው " በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል።

የክልሉ መንግስት " በትላንትናው እለት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ ተብሎ የተሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ ወሬ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። " ብሏል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ መቼ ነው የሚወጣው ?ከሳምንታት በፊት " በቅርቡ ዕጣው እንደገና ይወጣል " የተባለው የተሰረዘው  የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የሚወጣበት እካሁን አልታወቀም።በአዲስ አበ...
17/08/2022

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ መቼ ነው የሚወጣው ?

ከሳምንታት በፊት " በቅርቡ ዕጣው እንደገና ይወጣል " የተባለው የተሰረዘው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የሚወጣበት እካሁን አልታወቀም።

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ሐምሌ 1 ወጥቶ ውድቅ የተደረገው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በቅርቡ ይወጣል ከተባለ ሳምንታት ያለፉ ሲሆን የቤቶቹ ዕጣ መቼ እንደሚወጣ አልታወቀም።

ዕጣውን የሚጠባበቁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከተማ አስተዳደሩ በገባው ቃል መሰረት በፍጥነት ፤ ታማኝነት እና ግልፅነት ባለው መልኩ ዕጣውን በድጋሚ እንዲያወጣ / የሚወጣበትን ቀን እንዲሳውቅ ጠይቀዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ምንም እንኳን ትክክለኛውን ቀን አስረግጠው ባይናገሩም " የተሰረዘውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በቅርብ ለማውጣት እየተሰራ ነው ሲሉ ከገለፁ ወደ አንድ ወር እየተጠጋ ይገኛል።

ከንቲባዋ ሀምሌ 15 ቀን 2014 ላይ በኤፍ ኤም አዲስ በቀረቡበት ወቅት የጋራ ቤቶች እጣ ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ እና ጥቅም ላይ እንደሚውል ገልፀው ነበር።

ይህንን ካሉ ሳምንታት ያለፉ ቢሆንም እስካሁን የቤቶቹን ዕጣ በተመለከተ አዲስ ነገር የለም/ያለውን/የደረሰበትን ሂደት የሚገልፅ መረጃ ይፋ አልሆነም።

ከንቲባዋ ሬድዮ ላይ በቀረቡበት ሰሞን አንድንድ ሚዲያዎች " ዕጣው በሁለት ሳምንት ይወጣል ብለዋል " ሲሉ አሰራጭተው የነበረው መረጃም ትክክል ያልሆነ ነው። በወቅቱ ከንቲባዋ ቀን ሆነ በዚህ ሳምንት ብለው አልተናገሩም ነበር።

በሌላ በኩል ፤ የ2005 የ20/80 የባለ ሶስት መኝታ ቆጣቢዎች ከዚህ ቀደም ላቀረቡት ጥያቄ እስካሁን ድረስ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጣቸውን ባለማግኘታቸው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ግፊት እያደረጉ ሲሆን በቀጣዩ ዕጣ እነሱም ሊካተቱ እንደሚገባ እየገለፁ ናቸው።

ብዙዎችን ያጭበረበረው የፊያስ 777 አካውንት ታግዶ ምርመራ እየተካሄደ ነውብዙዎችን ያጭበረበረው ፊያስ 777 አካውንት ታግዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ለአዲስ...
01/08/2022

ብዙዎችን ያጭበረበረው የፊያስ 777 አካውንት ታግዶ ምርመራ እየተካሄደ ነው

ብዙዎችን ያጭበረበረው ፊያስ 777 አካውንት ታግዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት የፋይናንስ ወንጀሎች ትንተና ኃላፊ ዮናስ ማሞ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በፒራሚድ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማራው ፊያስ 777 ድርጅት ከ26 ሺሕ በላይ የውጭ አገር እና ኢትዮጵያዊያን ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን፣ ብዙ ሰዎች ላይ የማጭበርበር ወንጀል መፈፀሙን ጠቁመዋል።

ይህ ፊያስ 777 የተሰኘው ድርጅት እንደ ፋይናንስ ተቋም ተመዝግቦ እና እውቅና ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ ያልነበረ ተቋም መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።

አዲስ ማለዳ

ኢትዮጵያ ሦስተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት አከናውና አልጨረሰችም!   | ውሃውም በግድቡ አናት ላይ አልፈሰሰምከሁለት ዓመት በፊት ግድባችን የመጀመሪያ ዙር ዉሃን መያዙ እውን ሲሆን ታሪክ ላይመለስ...
01/08/2022

ኢትዮጵያ ሦስተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት አከናውና አልጨረሰችም!

| ውሃውም በግድቡ አናት ላይ አልፈሰሰም

ከሁለት ዓመት በፊት ግድባችን የመጀመሪያ ዙር ዉሃን መያዙ እውን ሲሆን ታሪክ ላይመለስ ተቀይሯል ብለናል።

ዘመናት ግብፅ በውሃው ላይ የነበራት ፍፁም የበላይነት ላይመለስ ባለበት አስቁመነዋል። ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንጂ ተመልካች ፣ ሰጪ እንጂ ተቀባይ ፣ ተፈላጊ እንጂ ተገፊ የማትሆንበት አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል!

አዲስ መንገድ ተቀይሷል ፤
የሚድያዎቻችንም በተለይም የማህበራዊ ሚድያ ዘማች እና አዝማቾችም አካሄድ ይህን አውዱን ማዕከል አድርጎ መቃኘት አለበት።
በዋናነትም እኛ አጀንዳ ሰጪ እንጂ ተቀባይ አይደለንም። ያ ጊዜ በመሰረታዊነት አብቅቷል። ይህን በዉል ባለመገንዘባችን ዛሬም ከሁለት አመት በፊት ስንከተል በነበረው መንገድ እየተጓዝን ነው።

ከሰሞኑ ግብፆውያን እያደረጉት ባለው ስልታዊ ፕሮፓጋንዳ ተስበን ብዙዎቻችን እየገባን ነው።

ግብፃውያን የህዳሴ ግድብ ጉዳይን ልክ ላለፉት ሁለት አመታት እንዳደረጉት ሁሉ አሁን ሶስተኛው ሙሌት ከመከናወኑ በፊት አለምአቀፍ አጀንዳ ለማድረግ ጥረቱን ከጀመሩት ሰንብተዋል። ሆኖም ባሰቡት ልክ መሆኑ ይቅርና በትንሹም ጉዳዩን በአለም መድረክ ሊሸጡት አልቻሉም።
አለም ይበልጥ ወዳጅ የሚሏቸው ሃገራት በተለያዩ 'የራሳችን' በሚሏቸው ጉዳዮች ( ሩሲያ ዩክሬንን) በመሰሉ እና ሌሎች ጉዳዮች ተወጥረዋል ። ዘንድሮ ሰሚ የለም!!

በተወሰነ መጠንም ቢሆን አጀንዳነቱን እንዳያጣ ታዲያ በራሳቸው እና በቅጥረኛ ሚድያዎቻቸው ሁኔታውን ለማጦዝ የተሰለቹ እና ገዢ ያጡ መልዕክቶችን እያሰራጩ የግድቡን ፋይል ለማነቃነቅ እርብርብ ከማድረግ አልቦዘኑም።
ይበልጥ የኢትዮጵያን መንግስት እና የማህበራዊ ሚዲያ ማህበረሰቡን ስቦ ወደ ሜዳ ሊያስገቡ ይችላሉ የሚሏቸውን አጀንዳዎች በየእለቱ በተለያዩ ስልቶች እንዲደርሰን እያደረጉ ነው።

ይህን የማድረጉ ፋይዳ፤ አጀንዳዎቻቸው በሁለቱ መንግስታት እንዲሁም በሁለቱ ሃገራት የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ ህዝቦች ምልልስ የሚያገኙ ከሆነ ነገሩን ለማጦዝ ያስችላል። አለም አቀፍ ማህበሰሰብን እንደ አምና እና ካቻምናው ግጭት ሊፈጠር ነው በሚል ፈጠራ ለግድቡ ጉዳይ ጆሮ እንዲሰጡ እና ጫና እንዲያሳርፉ ለማስገደድ እድልን ይፈጥራል።

ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ ኢትዮጵያ ሶስተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት አከናውና ሳትጨርስ ነው ። ከጨረሰችማ እንደገና አራተኛውን አመት መጠበቅ ነው !! ስለዚህም ይበልጥ ባለፉት ሶስት ሳምንታት በልዪ ሁኔታ በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚድያ በአዲስ መልክ ለዚሁ አላማ እየሰሩ ነው።

የእኛ ሰዎችም በአለማወቅ በየዕለቱ የእነርሱን ሚድያዎች በመከተል ለሚያሰራጩት መልዕክት እና ዘገባ በበጎነት ምላሽ በመስጠት በሚፈልጉት መልኩ የህዳሴ ግድብ አጀንዳን ከፍ እያረግንላቸው ነው።

አጀንዳነቱ ህይወት የሚኖረው ሦስተኛው ሙሌት ከመጠናቀቁ በፊት በመሆኑ ሆንብለው ስልታዊ በሆነ ኘሮፓጋንዳ ሙሌቱ ተጠናቀቀ የሚል መረጃ በስፋት እንዲሰራጭ አድርገዋል። ይህንንም የእኛ ሰዎች ተቀብለው አንዳች የሚመለከተው የመንግስት አካል መረጃ ሳይሰጥ ግብፃውያኑ ባሰቡት መልኩ አጀንዳውን ወደ ከፍታ እንዲወጣ እየሆነ ነው።

በዝምታ ውስጥ በብርቱ ስራ ለዚያውም በፈተና ወቅት ባለድል እየሆን ባለንበት ወቅት እውነተኛ ባልሆነ እና እኛን በማይጠቅም መልኩ አደባባይ መውጣት ተገቢ አይደለም።

በእርግጥ የሙሌቱ መጠናቀቅ ሃገር ወዳዶች ሁሉ መስማት የምንፈልገው ዜና ቢሆንም የሚነግረን ባለቤት፣ የሚነገርበትም ጊዜ አለው።

ሙሌቱ ሳይጠናቀቅ ተጠናቀቀ ተብሎ የተሰራጨው ስልታዊው የግብፃውያን መረጃ አጀንዳውን በዚህ አመት ከነበረው መቀዛቀዝ ከፍ ስለሚያደርገው አጯጩሆ ከወዲሁ አለም አቀፍ ማህበረሰቡ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እንዲያሳርፍ ለማድረግ ነው።
አሁን ግድባችን በተቻለ መጠን የሚድያ አጀንዳ እንዳይሆን ማድረግ ነው ከእኛ የሚጠበቀው፤ ለሃገራችን የሚጠቅመውም እርሱ ነው።

አለምአቀፍ ሁኔታውም ቢሆን ጊዜ ከግብፅ ጋር እንዳይሆን አድርጓል ፤ የታላላቅ ሃገራት መንግስታትም ይሁኑ ሚዲያዎቻቸው በብዙ ክስተቶች ተወጥረዋል። ይህ ለእኛ ዕድል ነው።
ግድባችን ሆነ ድርድሩ አሁን ባለበት ሁኔታ እኛ እነርሱን ልንከተል አይገባም። አጀንዳም ካስፈለገ ሰጪዎች እንጂ አጀንዳ ተቀባዮች የመሆኛ ጊዜያችን አብቅቷል!!

ሶስተኛ ዙር ሙሌት ላይ ደርሰን ሳለ ድሮ የጣልናቸውን አጀንዳዎች ሰጥተው ወደ ኋላ ሲስቡን አንሳብ። ወደ ፊት የሚያራምዱን ይበልጥ አሸናፊ የሚያደርጉንን

የቻይና ጦር ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ!የቻይና የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ያደረጉት የስልክ ውይይት ያለመግባባት ተጠናቋል!የቻይና ጦር ዌቦ በተሰኘው የሀገሪቱ ማህበራዊ ትስስር ገጹ እንሳሳወ...
30/07/2022

የቻይና ጦር ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ!

የቻይና የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ያደረጉት የስልክ ውይይት ያለመግባባት ተጠናቋል!

የቻይና ጦር ዌቦ በተሰኘው የሀገሪቱ ማህበራዊ ትስስር ገጹ እንሳሳወቀው ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። የሀገሪቱ 80ኛ ጦር ያወጣውን መገለጫ ዋቢ አድርጎ የሩሲያው አርቲ እንደዘገበው ከሆነ ወደ ጦርነት ለመግባት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የጦሩ ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን ማስታወቁ የአሜሪካ አፈ ጉባኤ የታይዋን ጉብኝት ምላሽ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ከቀናት በኋላ በሚገባው ነሀሴ ወር ላይ ታይዋንን እንደሚጎበኙ መግለጻቸው ይታወሳል። የአፈ ጉባኤውን የታይዋን ጉብኝት ተከትሎም ቻይና ወታሰራዊ እርምጃዎችን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል መናገሯ አይዘነጋም።

አሜሪካ እና ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከፍተኛ ያለመግባባት ችግር ያለባቸው ሲሆን አሜሪካ ታይዋን የቻይና አካል አይደለችም ስትል ቻይና በበኩሏ ታይዋን የግዛቴ አንድ አካል ናት የሚል ዕምነት አላት።የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች በዛሬው ዕለት በስልክ የተወያዩ ሲሆን ውይይቱ ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል።

የቻይናው ፕሬዚዳንት “በታይዋን የውስጥ ጉዳይ  ጣልቃ መግባት በእሳት እንደመጫወት ይቆጠራል” ሲሉ ጆ ባይደንን አስጠነቀቁአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳን ሺ...
29/07/2022

የቻይናው ፕሬዚዳንት “በታይዋን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት በእሳት እንደመጫወት ይቆጠራል” ሲሉ ጆ ባይደንን አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳን ሺ ጂንፒንግ በታይዋን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት በእሳት እንደመጫወት ይቆጠራል ሲሉ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን አስጠነቀቁ፡፡

የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ታይዋን ለማቅናት እቅድ መያዛቸውን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል የተፈጠረው ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይድን በታይዋን ጉዳይ ዙሪያ ለሁለት ሰዓት የዘለቀ የስልክ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ሺ አሜሪካ የቤጂንግን “የአንድ ቻይና መርህ” ማክበር እንዳለባት ነው በጥብቅ ያሳሰቡት፡፡

የታይዋን ነፃ አገር የመመስረት ሂደት የማይታሰብ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ÷በጉዳዩ ላይ የውጭ ኃይሎች የሚያሳዩትን ጣልቃ ገብነት ኮንነዋል፡፡

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ጆ ባደን በታይዋን የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያሳዩት አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት ”በእሳት እንደመጫዎት ይቆጠራል፤ በእሳት የሚጫወትም መቃጠሉ አይቀርም” ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው፥ አሜሪካ የታይዋንን የነፃነት ጥያቄ የሚገዳደር እና አሁን ያለውን ሰላም እና መረጋጋት ለማደፍረስ በአንድ ወገን የሚወሰድን የተናጠል እርምጃ አጥብቃ እንደምትቃወም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ዋሽንግተን በታይዋን ጉዳይ ላይ ያላት አቋም እና ፖሊስ አሁንም ያልተለወጠ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡

በሌላ በኩል ፔሎሲ በእቅዳቸው መሰረት ለስራ ጉብኝት ወደ ታይዋን የሚጓዙ ከሆነ ቻይና ጠንካራ አጸፋዊ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹን አልጀዚራ ዘግቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ በታይዋን የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት መሰል ግጭት-ቀስቃሽ ድርጊቶች ከመፈጸም እንድትቆጠብም አሳስቧል፡፡

ቻይና ታይዋንን እንደ አንድ የተገነጠለች የራሷ ግዛት አድርጋ የምታያት ሲሆን÷ ታይዋን ግን ራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ነው የምትቆጥረው።

ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎች የተላለፉበት ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲ...
28/07/2022

ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎች የተላለፉበት ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎች የተላለፉበት እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፥ የአሁኑ ጉብኝት ያስገኘው አንዱ ውጤት፥ ከሶቪየት ህብረት አስተዳደር ጀምሮ ሲንከባለል የቆየ ብድርን የሚመለከት ነው ብለዋል ።

ብድሩን ለማስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስት በመረጣቸው ፕሮጀክቶች ላይ የሩሲያ ኩባንያዎች ተሰማርተው እንዲሰሩ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል።

በዚህም 162 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያላቸው ፕሮጀክቶች በጋራ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነት ምክክር ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

በምክክራቸውም ሁለቱ ሀገራት በፓለቲካው መድረክ ያላቸው ጠንካራ ትስስር በኢኮኖሚ በንግድ በባህልና በኢንቨስትመንት ላይ እንዲደገም ተስማምተዋል።

ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ።ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎ...
28/07/2022

ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ።

ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል።

በዚህም፦

- 1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

- 45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

- 100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

- የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።

ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።

ማስታወሻ: ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው።

share ሼር በማድረግ ሌሎች እናድርስ

28/07/2022
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ አረንጓዴ ዐሻራ አኖሩ*****************(ኢ ፕ ድ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚ...
27/07/2022

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ አረንጓዴ ዐሻራ አኖሩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በመኾን በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ አረንጓዴ ዐሻራ አኖሩ።

ኢትዮጵያና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
27/07/2022

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

Address

Dolos News/
Addis Ababa

Telephone

+251912630392

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dolos Ethiopia - News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share