HBC news

HBC news News

ይህ የሙከራ ስርጭት ነው፡፡HBC news
09/12/2020

ይህ የሙከራ ስርጭት ነው፡፡
HBC news

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።‼️ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ገልጾ በነበረው መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ ሲሰጥ በሌሎች ...
03/12/2020

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።‼️

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ገልጾ በነበረው መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ ሲሰጥ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችም እስከ ታህሳስ አጋማሸ ድረስ የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህም መሰረት በኦሮሚያ ክልል ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 2/2013 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን በአማራ ክልልም እንዲሁ የሚሰጥ ከታህሳስ 12 እስከ 14/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

የዚህ ፈተና ተፈታኝ ለሆናችሁ ተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ እየተመኘ የመፈተኛ ቀናችሁ ላልደረሰ ተፈታኞች ደግሞ መልካም የጥናት ጊዜ ይሁንላችሁ ይላል፡፡


03/12/2020

የዩኒቨርስቲዎች ጥሪ እስካሁን ድረስ ለተመራቂ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ‼️

1. AASTU ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 26 - 27

2. ASTU ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 10 (ምረቃ)

3. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 1 - 2

4. አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከህደር 24 - 25

5. ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 23

6. መቱ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 28 - 29

7. ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26

8. ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26

9. ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 3 - 4

10. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 3 - 4

11. ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26

12. ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 21 - 23

13. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 24 - 25

14. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 29 - ታህሳስ 01

15. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 24 - 27

16. ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 30 - ታህሳስ 1

17. ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 29 - 30

18. መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 5 - 6

19. ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 26 - 28

20. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 3 - 4

21. ሰላሌ ዩንቨርሲቲ ህዳር 23

22. ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 28 - 30

23. ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 25 - 26

24. ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከታህሳስ 1 - 2

የሌሎች ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡


02/12/2020

በመቐለ ከተማ መከላከያ የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኘ‼️

የልዩ ዘመቻ 2ኛ ብርጌድ 3ኛ ሬጅመንት አዛዥ. ሌተናል ጀነራል ሳድቅ አህመድ እንዳሉት መቐለ ከተማ ላይ መከላከያ የማያወቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኝቷል።የጁንታው ቡድን ውጊያውን መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እያራገፈ ፈርጥጧል ያሉት አዛዡ ከዚህ ውስጥ ሰራዊቱ የማያውቀው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹበት ዲፖ ተገኝቷል ብለዋል።የሰሜን እዝ አመራሮችን ጠይቀን ስለዲፖው እንደማያውቁ ገልጸውልናል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፤ በቀጣይም ተመሳሳይ የመሳሪያ ማከማቻወችም ሊገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል።በመሆኑም እነዚህ ከቀላል እስከ ቡድን መሳሪያዎች ወንጀል እዳይፈጸምባቸው የፍተሻ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።


02/12/2020

የተሳሳተ መረጃ ማስተካከያ‼️

የኢፌዲሪ ፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ በርካታ የከሀዲው ጁንታ ህዋሀት ቡድን አባላት የሆኑ ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛና የመስመር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱንና እነዚህን ህገወጦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ከትትል መጀመሩን ለህዝብ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።

ኮሚሽኑ የክትትል ስራውን አጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል በሚል 38 የህዋሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ስል ያስተላለፈው መረጃ በም/ኮሚሽነር ጀነራሉ ያልተላለፈ መሆኑን እየጠቆምን ተያዙ በሚል ሃላፊው የገለፁት መከላከያ ውስጥ የግንኙነት መስመር ያቋረጡና ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዱን (ወዲ ነጮን) ጨምሮ 38 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው መሆኑን እየጠቆምን ከጁንታው ቡድን አባላት እስከአሁን የተያዙ አለመኖራቸው እንገልፃለን ።
©ፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን


Address

Addis Ababa
15842222

Telephone

+251921499722

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HBC news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to HBC news:

Share