Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት SMS : ስልጤ ላይ ስለተከናወኑ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ክንዋኔዎች እና ሀገራዊና አለምዓቀፍዊ ጉዳዮች መዘገብና የበጎ ስራዎችን መደገፍ ነው ።

''በመትከል ማንሰራራት'' ስልጤ🤩Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት
16/07/2025

''በመትከል ማንሰራራት'' ስልጤ🤩
Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

📍📍📍
16/07/2025

📍📍📍

📍404 ሺህ በላይ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በአፋር ክልል…በአፋር ክልል የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋት የዘርፉን እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ባሕ...
16/07/2025

📍404 ሺህ በላይ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በአፋር ክልል…

በአፋር ክልል የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋት የዘርፉን እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ፡፡

የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ አብዱ መሃመድ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ያለውን እምቅ የቱሪስት መስህብ ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስተዋወቅ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

የክልሉ ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ የሆኑትን ዳሎል፣ ኤርታሌ፣ አፍዴራ ሐይቅ፣ አላሎ ባድ ፈል፣ አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፣ የአብዬ ሐይቅና ሌሎችን በማልማት ረገድ አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

በተለይም በቱሪስት መዳረሻዎች አቅራቢያ ለጎብኚዎች ማረፊያ የሚሆኑ ባሕላዊ የመዝናኛ ቤቶችንና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን የመገንባት ሥራ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዘርፉ በተለያዩ አካባቢዎች ባለሃብቶች በሆቴሎች እና ሎጂዎች ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ትኩረት መደረጉን ነው ያስረዱት፡፡

በክልሉ የሚገኘውን እምቅ የቱሪዝም ሃብት በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ለማስተዋወቅና ከዘርፉ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትብብር መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ይበልጥ በማልማት የውጭ እና የሀገር ውስጥ ቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር መደረጉን አብራርተዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 4 ሺህ 300 የውጪ ቱሪስቶች በክልሉ የሚገኙ መስህቦችን እንደጎበኙ ጠቅሰው÷ በዚህም 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ከመግቢያ ክፍያ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል 400 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ዜጎች ክልሉን የጎበኙ ሲሆን÷ በዚህም በቱሪዝም ኮንፈረንስና ሌሎች አገልግሎቶች የክልሉን ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማነቃቃት መቻሉን አመልክተዋል፡፡

በክልሉ ያለው ሰላም የቱሪስት ፍሰቱ ከባለፉት ዓመትታ በተሻለ ሁኔታ እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አቶ አብዱ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

📍የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ የሚከናወንበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ::የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ምርጫ የሚከናወንባቸውን ቀናት ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡...
16/07/2025

📍የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ የሚከናወንበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ::

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ምርጫ የሚከናወንባቸውን ቀናት ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡

የምርጫ አስፈፃሚ ቦርዱ ባለፉት ጊዜያት የሰራቸውን እና ቀጣይ ስራዎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የቦርዱ ሰብሳቢ አብዱልአዚዝ ኢብራሂም (ዶ/ር) የመራጮች ምዝገባ ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ እና ምርጫው የሚከናወንባቸው ቀናትን ይፋ አድርገዋል።

የመራጮች ምዝገባው እንደተጠናቀቀ ከነሐሴ 9 እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ የመጀመሪያ ለወረዳ ምክርቤት ለመመስረት በየመስጂዶች ምርጫ ይካሄዳል ብለዋል።

ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ደረስ ለመጅሊስ ምርጫ የሹራ (ምክክር) ሳምንትና የተመራጭ እጩዎች ግምገማና መለያ ይሆናል ነው ያሉት ሰብሳቢው።

በዑለማ በምሁር ወጣት ሴቶች እና የስራ ማህበረሰብ ደረጃ የሚመረጡ ተመራጮች ከተለዩ በኋላ ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የዑለማዎች ምርጫ ይካሄዳል።

ቀጥሎ ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናት ምሁራን፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና የስራ ማህበረሰብን የሚወክሉ ይመረጣሉ።

ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት የስራ አስፈፃሚ ፕሬዚደንትና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተመርጠው፣ ቀጥለው ባሉ 2 ቀናት ተመራጩ አመራር ለአዲሱ ያስረክባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው ሰብሳቢው የገለጹት።

📍እስቲ ሀሳብ አስተያየቶን ያኑሩላቸው በዞናችን ልማት ጉዳይ !ለስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ✍️✍️✍️📍''በመትከል ማንሰራራት'' በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ...
16/07/2025

📍እስቲ ሀሳብ አስተያየቶን ያኑሩላቸው በዞናችን ልማት ጉዳይ !ለስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ✍️✍️✍️

📍''በመትከል ማንሰራራት'' በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራው ልዑክ በላንፉሮ ወረዳ ሻንቃ ጡፋ ቀበሌ በቡናና ፍራፍሬ ክላስተር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ፡፡

📍ቀጣይ ለወረዳና ለከተማ አስተዳዳሪዎች መልካም አስተያያቶችን ታኖራላችሁ ተዘጋጁ !

✍️ዘወትር ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

📍የውጭ ሃገር የሥራ ዕድል...በሥራና ክህሎት ሚንስቴር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት ትልቅ ...
16/07/2025

📍የውጭ ሃገር የሥራ ዕድል...

በሥራና ክህሎት ሚንስቴር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል።

አሁንም ህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ የሰው ሃይል በተለያዩ የሞያ ዘርፎች በቁጥር ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል ይፈለጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች መሰማራት የምትፈልጉ በሙሉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት ፎርሙን ሞልታችሁ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ስንል እናሳውቃለን።

Driving & Transportation
1. Light Vehicle Driver
2. Heavy Vehicle Driver (e.g., Grader Operator)
3. House Driver
4. Trolley Operator

Security & Safety
5. Security Guard
6. CCTV Surveillance Operator
7. Office Security Personnel
8. Plumber
9. Electrician
10. HVAC Technician
11. AC Technician
12. Pumper

Domestic & Facility Services
13. Housekeeper
14. House Maid
15. House Cleaner
16. Housekeeping Supervisor
17. Houseman
18. Caretaker
19. Steward
20. Laundry Attendant
21. Bellman

Hospitality & Food Services
22. Receptionist
23. Waiter/Waitress
24. Barista
25. Sous Chef
26. Pastry Chef / Dessert Chef
27. Garde Manger Chef
28. Arabica Cuisine Chef
29. Kitchen Assistant
30. Private Cook
31. Room Attendant
32. Hotel Assistant Manager

Healthcare & Caregiving
33. Nurse
34. Junior Nurse
35. Home Care Nurse
36. Private Nurse
37. Junior Midwife / Clinical Nurse
38. Elderly Care Assistant
39. Live-in Support Assistant
40. Neonatal Intensive Care Unit (NICU) Nurse
41. Junior Physiotherapist

Childcare Services
42. Babysitter
43. Childcare Worker

Beauty & Salon Services
44. Hairdresser
45. Hairstylist
46. Beauty Therapist
47. Salon Manager
48. Nail Technician
49. Nail Art Instructor
50. Massage Therapist
51. Makeup Artist

Agriculture & Farming
52. Indoor Farmer
53. General Farm Worker

Administrative & Marketing
54. Junior Administrative Assistant
55. Junior Marketing Assistant
56. Junior Account Manager
57. Sales Representative
58. Purchaser

Skilled Labor
59. Construction Worker
60. Laborer
61. Tailor
62. Storekeeper
63. Supervisor

Retail & Customer Services
64. Cashier
65. Promoter

https://forms.gle/TF5BcYBtrhwkyjR59

መልካም ዕድል!

የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

ፈያ ሀንደሬን! ኒባረታሙ አይኔን? ከረሚ! አዝመራይ!ዝልዛሎይ! የመንጊስት ቢል! ያልቡይ ሀል አይነኮን?likeFollow ShareSilte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግ...
16/07/2025

ፈያ ሀንደሬን! ኒባረታሙ አይኔን? ከረሚ! አዝመራይ!ዝልዛሎይ! የመንጊስት ቢል! ያልቡይ ሀል አይነኮን?

like
Follow
Share

Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

📍ስልጤ ተሀላባ ሙሃባምኒሙ ሉሌ🥰📍ቃል በተግባር  የስልጤ ዞን አስተዳደር 🤩      በአስገራሚ ፍጥነት ከስልጤ ወንድሞቻ ለሀላባ ወንድሞች የዞኑ አስተዳደር   አማካኝነት የሱና ዩንቨርስቲ ግን...
15/07/2025

📍ስልጤ ተሀላባ ሙሃባምኒሙ ሉሌ🥰
📍ቃል በተግባር የስልጤ ዞን አስተዳደር 🤩




በአስገራሚ ፍጥነት ከስልጤ ወንድሞቻ ለሀላባ ወንድሞች የዞኑ አስተዳደር አማካኝነት የሱና ዩንቨርስቲ ግንባታን እንቅስቃሴ ተጀመረ።

የስልጤ ዞን አስተዳደር ቃል የገባውን የግንባታ እቃዎች ማስገባት ጀምሯል።

Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

📌 የአሁን የኢትዮጵያ ትምህርት ስረሀት፡ ፈተናዎች እና የትውልድ ግንባታ ( ክፍል 2)የኢትዮጵያ ራዕይ (vision) ዘላቂ ሰላምን፣ ብልጽግናን እና ልማትን ማስፈን ነው። ይህ ራዕይ እውን እ...
15/07/2025

📌 የአሁን የኢትዮጵያ ትምህርት ስረሀት፡ ፈተናዎች እና የትውልድ ግንባታ ( ክፍል 2)

የኢትዮጵያ ራዕይ (vision) ዘላቂ ሰላምን፣ ብልጽግናን እና ልማትን ማስፈን ነው። ይህ ራዕይ እውን እንዲሆን፣ በዕውቀትና በክህሎት የበለፀገ፣ ችግር ፈቺና ፈጣሪ የሆነ ትውልድ መፍጠር ወሳኝ ነው። አሁን ባለው የትምህርት ሥርዓት የምንፈጥረው ትውልድ ለዚህ ራዕይ መሳካት የሚያበቃ አይደለም የሚለው ስጋት ከፍ ያለ ነው።

በመሆኑም የመንግሥት አካላት ለዚህ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት መስጠት አለባቸው። ኩረጃን (cheating) ማስቆም ትልቅ ነገር ቢሆንም፣ ተማሪዎች በመሰረታዊ እውቀትና ክህሎት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ከሰራን፣ ለፈተና ብቻ የሚያጠና ሳይሆን፣ ለችግሮች መፍትሄ የሚፈጥር ትውልድ መፍጠር ይቻላል። የማንኛውም ሀገር የተማሪ ውጤት መቀነስ ለትምህርት ሚኒስቴርም ይሁን ለማንኛውም የትምህርት ቤት እንደ ውርደት እንጂ እንደ ጀብድ ሊታይ አይገባም።

📌 የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት የአሁን ነባራዊ ችግሮች:

"ፍኖተ ካርታውን የቀረፅነው ከበለፀጉ ሀገራት ነው" እያልን ከሆነ፣ ይህ ፍኖተ ካርታ መሬት ወርዶ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊሰሩበት ይገባል እላለሁ። እኛ ሀገር ግን፣ በቅርብ ጊዜ የምናየው የፈተና ፖሊሲ በፈተና ዙሪያ ላይ ብቻ ያተኮረ (exam-centric) እና ትምህርት "ፖሊስ ጠብቆ ፈተና እንደመፈተን" ዓይነት ሆኗል። ይህ የሚያሳየው፣ በትምህርት ጥራት (quality of education)፣ በመምህራን ብቃት (teacher competency)፣ በምቹ የመማር ማስተማር ሂደት (conducive learning environment)፣ በቁሳቁስ አቅርቦት ላይ በቂ ትኩረት አለመደረጉን ነው።

📍 በይዘት ላይ ያተኮረ ትምህርት (Content-focused learning): ተማሪዎች ትምህርትን በመረዳት ፋንታ ለፈተና አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን በቃላቸው እንዲይዙ ይገደዳሉ። ይህ ደግሞ የፈተና ውጤትን ብቻ በማሳደድ እውነተኛ እውቀትን ከመገንባት ያግዳል::

📍 የትንተናና የፈጠራ ክህሎት ማጣት (Lack of analytical and creative skills): የፈተና አካሄዱ በአብዛኛው የትምህርት ይዘትን በቃላቸው የመያዝ (rote learning) ችሎታ ላይ ያተኩራል። ይህም የተማሪዎችን የትንተና፣ የፈጠራ እና የችግር ፈቺ ክህሎቶችን እንዳያዳብሩ ይገዳል::

📍 የተማሪውን ብቸኛ ተጠያቂነት (Sole student accountability): አንድ ተማሪ ጥሩ ውጤት ሳያመጣ ሲቀር፣ የጥፋቱ ሙሉ ሃላፊነት በተማሪው ላይ ይወድቃል። የመምህራን ብቃት፣ የትምህርት ግብዓቶች (educational resources) እጥረት ወይም የቤተሰብ ችግሮች እንደ ትልቅ ችግር አይታዩም።

📍 የትምህርት ተቋማት እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን መሙላት ላይ ትኩረት አለመደረግ: የገጠርና የግል ትምህርት ቤቶች መካከል ያለው የትምህርት ግብዓት ልዩነት ሰፊ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ትልቅ የፍትሃዊነት ችግር (equity issue) ይፈጥራል።
መፍትሄዎች ለኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት:
ወደድንም ጠላንም ይችን ሀገር ተረክቦ ለቀጣይ ጀነሬሽን የሚያስረክብ ትውልድ ያስፈልጋል። ስለዚህ ትምህርት ለአንድ ሀገር የእድገት እና የወደፊት እጣ ፈንታ ይህ ነው የማይባል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።

📍 ሥርዓተ ትምህርቱን ማሻሻል: ከተማሪዎች ፍላጎት፣ የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታና የዓለም የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ተማሪ ተኮር (student-centered) እና ተግባር ተኮር (practical-oriented) ሥርዓተ ትምህርት መዘርጋት።

📍 የመምህራን ብቃት ማሻሻል: የመምህራንን የደመወዝ እና የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል፣ የማያቋርጥ የክህሎት ማበልፀጊያ ስልጠናዎችን መስጠት እና ለሙያቸው ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ማበረታታት።

📍 የመማር ማስተማር ግብዓቶችን ማሟላት: በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት (infrastructure)፣ ዘመናዊ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ ቤተ መፃህፍት እና የላቦራቶሪዎች አቅርቦት ላይ ትኩረት መስጠት።

📍 የፈተና ሥርዓቱን ማሻሻል: የፈተና ሥርዓቱ የተማሪዎችን እውነተኛ እውቀት፣ የትንተና እና የችግር ፈቺ ክህሎት የሚለካ እንዲሆን ማሻሻል፤ የቃላቸውን የመያዝ ችሎታ ላይ ብቻ ያተኮረ እንዳይሆን ማድረግ።

📍 የባለድርሻ አካላት ተጠያቂነት: የተማሪው ውጤት ሲቀንስ የመንግስት ተቋማት፣ የትምህርት ቤቶች አመራሮች፣ መምህራን፣ ወላጆች እና ማህበረሰቡ በጋራ ሃላፊነት ወስደው መፍትሄ እንዲፈልጉ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት።

📍 ቴክኖሎጂን በትምህርት ውስጥ ማካተት: ዲጂታል የመማሪያ ዘዴዎችን (digital learning methods)፣ ኢ-ለርኒንግ (e-learning) እና የርቀት ትምህርትን (distance learning) ማበረታታት እና አስፈለጊውን ነገር ለሁሉም ትምህርት ቤቶች መቅረብ::

"የተገነባ ትውልድ (Built generation)" ማለት እውቀትን የተሸከመ ብቻ ሳይሆን፣ ያገኘውን እውቀት በመጠቀም ለራሱ፣ ለቤተሰቡና ለሀገሩ ችግሮች መፍትሄ የሚፈጥር ትውልድ ማለት ነው።

በረዲ ከድር ✍️
Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት

📍አፍሪካ ቀስ በቀስ እየተሰነጠቀች አዲስ ውቅያኖስ የመፍጠር ሁኔታዋ እየሰፋ ነው ተባለለዓመታት የሳይንስ ሊቃውንትን ትኩረት ሲስብ የቆየው የአፍሪካ ቀጣናዊ ለውጥ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ...
15/07/2025

📍አፍሪካ ቀስ በቀስ እየተሰነጠቀች አዲስ ውቅያኖስ የመፍጠር ሁኔታዋ እየሰፋ ነው ተባለ

ለዓመታት የሳይንስ ሊቃውንትን ትኩረት ሲስብ የቆየው የአፍሪካ ቀጣናዊ ለውጥ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

አፍሪካ አህጉር ቀስ በቀስ እየተሰነጠቀችና በመካከሏ አዲስ ውቅያኖስ የመፍጠር ሂደት ላይ እንደምትገኝ የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ጥልቅ ስምጥ ሸለቆዎች በምስራቅ አፍሪካ በኩል ተፈጥረው እየሰፉ ይገኛሉ ተብሏል።

ይህ ስምጥ ሸለቆ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመሄድ በምስራቅ አፍሪካ በኩል የሚገኘውን ክፍል ከቀሪው አህጉር የመለየት አዝማሚያ እያሳየ መሆኑ እየተዘገበ ነው።

ጂኦሎጂስቶች እንደሚሉት፣ ይህ ሂደት የሚሊዮኖች ዓመታት የሚወስድ ሲሆን፣ በመጨረሻም ሁለቱን የአፍሪካ ክፍሎች የሚለይ አዲስ ውቅያኖስ ይፈጥራል ነው የተባለው።

ይህ ተፈጥሯዊ ሂደት በምድር ንጣፍ (tectonic plates) እንቅስቃሴ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን፣ የአፍሪካ ታርጋ (African Plate) ከሌሎች ታርጋዎች ጋር በሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚፈጠር መሆኑ ተመላክቷል።

በምስራቅ አፍሪካ ያለው ስምጥ ሸለቆ ከቀይ ባህር ወደ ደቡብ እየተጓዘ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ የመሰንጠቅ ሂደት በአካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥና የእሳተ ገሞራ እንቅስቃሴ እንዲበዛም አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው የተባለው።

ይህ አዲስ ውቅያኖስ ሲፈጠር፣ የአፍሪካ ካርታ በአዲስ መልክ እንደሚቀየርና በርካታ ተፈጥሯዊና ጂኦግራፊያዊ ለውጦች እንደሚከሰቱም የሳይንስ ሊቃውንት ይገልጻሉ።

ይህ ክስተት ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር፣ የአየር ንብረት እና ለሰው ልጅ ሰፈራ አዲስ ተጽእኖዎች ሊኖሩት እንደሚችሉም ይጠበቃል ተብሏል።

ይህን ሂደት ለመከታተል እና ሳይንሳዊ ምርምሮችን ለማካሄድ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ሳይንቲስቶች በትኩረት እየሰሩ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

📍ዞኑ ላይ እያመጣችሁት ያለውን ለውጥ እንደግፋለን !አሸማሙ👏የሚሰራ ሰው ክፍተት አይጠፋውምና ክፍተቶች ሲፈጠሩ ምክናያታዊ ትችቶችን እናነሳለን !
15/07/2025

📍ዞኑ ላይ እያመጣችሁት ያለውን ለውጥ እንደግፋለን !አሸማሙ👏

የሚሰራ ሰው ክፍተት አይጠፋውምና ክፍተቶች ሲፈጠሩ ምክናያታዊ ትችቶችን እናነሳለን !

📍ጣና ነሽ-2 በዓባይ በረሃጣና ነሽ-2 ጉዞዋን ቀጥላ ዓባይ በረሃ ደርሳ እያለፈች ነው!
15/07/2025

📍ጣና ነሽ-2 በዓባይ በረሃ

ጣና ነሽ-2 ጉዞዋን ቀጥላ ዓባይ በረሃ ደርሳ እያለፈች ነው!

Address

Addis Ababa

Telephone

+251915969474

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Silte Media Service - SMS /ስልጤ ሚድያ አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share