Taytu Media - ጣይቱ ሚዲያ

ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ*************************በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነውየአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከ...
31/08/2025

ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
*************************

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም ምርጫ በታላቅ ስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ፣ የ2017 የከተማውን መጅሊስ የማዋቀር ሂደትና የምርጫ መርሃ ግብር በሰላማዊና ኢስላማዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት ማጠናቀቁን በታላቅ ደስታ ይገልፃል። መንግሥት የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም፣ የፌደራል መጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ በወሰነው መሰረት “ምርጫ ለፅኑ ተቋም” በሚል መሪ ቃል ህዝብ መሪውን በመስጂዱ በነፃነት ሊመርጥ ችሏል።

ቦርዱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አምስት ወራት ከ 5 ሺ በላይ የምርጫ ግብረ ሀይል አባላት በበጎ ፈቃደኝነት በማሳተፍ ፣ የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም እና የሀገራችንን ጥንታዊ የእስልምና ታሪክ የሚያንፀባርቅ ኢስላማዊ ስነ ስርዓቱን የጠበቀ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ሌት ተቀን ሲሰራ ቆይቷል። ይህንንም የተቀደሰ ዓላማ ለማሳካት በየደረጃው ማለትም በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ እና በመስጂድ ደረጃ የምርጫ አስፈጻሚዎችን በመሾም እና ግብረ ኃይሎችን በማደራጀት እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የመጅሊስ ስራ አስፈፃሚዎችን በማስመረጥ ሰፊ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

የዚህ የተቀናጀ ጥረት ፍፃሜ የሆነው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምሥረታ ጉባኤ፣ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወከሉ የዑለማዎች፣ የምሁራን፣ የሰራተኛ ማህበረሰብ፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። የምርጫው ሂደት ኢስላማዊ ሂደቱን የጠበቀ ግልጽ፣ ሰላማዊ እና ሁሉንም ያሳተፈ ሆኖ በላቀ ስኬት ተጠናቋል።

በዚህም መሰረት የምርጫው ውጤት እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

1. አዲስ አበባን በፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሚወክሉ ተመራጮች

ከዑለማ ዘርፍ፡
1. ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ
2. ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
3. ሸይኽ ሑሴን በሽር
4. ሸይኽ ማሕመድ ሑሴን
5. ሸይኽ አሕመድ ዛኪር

ከምሁራን ዘርፍ፡
1. ኤልያስ አወል
2. አምባሳደር ሸሪፍ ኸይሬ

ከሰራተኛ ማኅበረሰብ ዘርፍ፡
1. አብድልቃድር ማሂ

ከወጣት ዘርፍ፡
1. ኢብራሂም ሙሰማ

ከሴቶች ዘርፍ፡
1. ዘይነብ ነሩ
2. የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ተመራጮች

ከዑለማ ዘርፍ፡
1. ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ
2. ሸይኽ ሙሐመድ ሸሪፍ
3. ኡስታዝ ጋሊ አባቦር
4. ሸይኽ ዙበይር ሬድዋን
5. ሸይኽ ሑሴን ሰዒድ
6. ኡስታዝ ሰልሃዲን መለሰ
7. ሸይኽ ኑርሑሴን ሙስጠፋ

ከምሁራን ዘርፍ፡
1. ሺሃቡዲን ኑራ
2. ሼህ መሐመድ አሊ

ከማኅበረሰብ ዘርፍ፡
1. ኡስታዝ ኣዩብ ደርባቸው

ከወጣቶች ዘርፍ፡
1. መንሱር ኸድር

ከሴቶች ዘርፍ፡
1. ፈትህያ ሙሐመድ
2. ኑርያ ሙሐመድ

በኦዲትና ኢንስፔክሽን
1. ዶ/ር ዘይኑ ዙበይር
2. አቲ ሙሐመድ አብዶሽ
3. አቶ በረከት አብደላ

በተጨማሪም ጉባኤው የከፍተኛ ምክር ቤቱን ቁልፍ አመራሮች የሰየመ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት፡-
1. ሸይኽ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባየከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት፣
2. ሸይኽ ሙሐመድ ሸሪፍምክትል ፕሬዝዳንት፣
3. ሺሃቡዲን ኑራዋና ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል።

የገቢ ግብር አዋጅ ዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋዮችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው - የምጣኔ ሀብት መምህር እና ተመራማሪ*************የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው በዝቅተኛ ደምወዝ ያሉ ዜጎችን በይበል...
30/08/2025

የገቢ ግብር አዋጅ ዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋዮችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው - የምጣኔ ሀብት መምህር እና ተመራማሪ
*************

የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው በዝቅተኛ ደምወዝ ያሉ ዜጎችን በይበልጥ ተጠቃሚ ያደረገ እና የዜጎች የኑሮ ጫና ለማቃለል ያለመ ነው ሲሉ የምጣኔ ሀብት መምህር እና ተመራማሪ ገለጹ፡፡

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር እና ተመራማሪው መሀመድ ኢሳ (ዶ/ር) ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ አንድ አካል የሆነው የገቢ ግብር አዋጅ አነስተኛ ደመወዝ ያላቸው ዜጎች ጫና ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ለዚህም ማሳያ ብለው ያቀረቡት ከዚህ ቀደም የነበረው ከ6 መቶ ብር በላይ የሆኑ ተከፋይ ሠራተኞች ግብር የሚቆረጥባቸው የነበረ ሲሆን በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ግን ከ2 ሺህ ብር በላይ ደመወዝ ተከፋይ የሆኑ ዜጎችን እንዲያካትት መደረጉን አንስተዋል፡፡

ይህም አነስተኛ ደመወዝ ያላቸው ዜጎች ጫና ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ የታሰበ ስለመሆኑ የጠቀሱት መምህሩ፤ ይህ ሲሆን መንግሥት የሚያጣው ነገር ቢኖርም ለዜጎቹ ያለውን ቁርጠኝነት ግን እንደሚያሳም ነው የጠቀሱት፡፡

የኢትዮጴያ ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ስርአት ጠላት የሚያመርት ይመስላል። የዚህ ደብተር ምስክርነት ህያው ማሳያ ነው። ___________________________________________ የገቢ ግብር አዋጅ ሁሉንም የመንግስት ደሞዝ ተከፋዮችን ያማከል ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

በአዋጁ መሰረት የገቢ መክፈያ ጊዜ ወደ ሩብ አመታት ተከፋፍሎ እንዲከፈል መደረጉ ለግብር ከፋዩ ሆነ ለመንግስት እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአከፋፈል ስርዓቱ ቀላል እና ለነጋዴው ለመክፈል አንዲያመቸው፣ ውዝፍ እንዳይመጣ እንዲሁም ለመንግስት ለግብር አሰባሰብ ምቹ እንደሚሆንለትም ተናግረዋል፡፡

አዋጁ መንግስት ታማኝ የግብር ከፋዩን በቀላሉ ለመለየትም እንደሚያግዘው የገለጹት መሀመድ ኢሳ (ዶ/ር)፤ ይህም የታክስ መጭበርበርን እንደሚቀነስና የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

EBC

ቅድሚያ ለሰብዓዊነት ከሙያዊ ኃላፊነት ያፈነገጠ እና የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ መርህን ያልተከተለ ድርጊት የፈጸሙት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ በአዲስ አበባ ከተማ ባልቻ ት...
30/08/2025

ቅድሚያ ለሰብዓዊነት

ከሙያዊ ኃላፊነት ያፈነገጠ እና የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ መርህን ያልተከተለ ድርጊት የፈጸሙት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ ባልቻ ትምህርት ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሙያዊ ኃላፊነት ያፈነገጠ እና የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ መርህን ያልተከተለ ድርጊት የፈጸሙት የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው የሚገኙት ምክትል ሳጅን አሸብር ግምጃው እና ረዳት ሳጅን ናትናኤል በላይ የተባሉ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡

የፖሊስ አባላቱ ነሐሴ 21 ቀን 2017 መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ በነበረበት ወቅት በግምት ከቀኑ 10 ሠዓት ገደማ ባልቻ ትምህርት ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፤ በአንድ ተሽከርካሪ ውስጥ ተቀምጠው ጫት ሲቅሙ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦችን አግኝተው በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረጉት እንቅስቃሴ ድርጊቱ ሊፈፀም መቻሉንም አመላክቷል፡፡

በወቅቱ ጫት ከሚቅሙት ግለሰቦች ጋር አብሮ የነበረው የአብስራ ሳሙኤል የተባለው የግል ተበዳይ ከስፍራው ለማምለጥ በማሰብ ሲሮጥ የፖሊስ አባላቱ ተከታትለው እንደያዙት የገለጸው ፖሊስ ነገር ግን፤ መሬት ላይ እየጎተቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ለመውሰድ የሞከሩበት መንገድ ግን ከሙያዊ ኃላፊነት ያፈነገጠ እና የሰብአዊ መብት አጠባበቅ መርህን ያልተከተለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ሁለቱ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ያስታወቀው ጠቅላይ መምሪያው፤ የፖሊስ አመራርና አባላት የተጣለባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት ሲወጡ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት ባከበረ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

በሥነ ምግባር ጥሰት ውስጥ በሚገኙ ፖሊሶች ላይ የሚወሰደው ሕጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡
(አሐዱ)

ክላሽን በወርቅ የቀየሩ ... ። Recorded
30/08/2025

ክላሽን በወርቅ የቀየሩ ... ። Recorded

የገቢ ግብርን አስመልክቶ በተመረጡ አንቀጾች ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ
27/08/2025

የገቢ ግብርን አስመልክቶ በተመረጡ አንቀጾች ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ “የምግብ ድጎማ” ማሻሺያ ማድረጉን አስታወቀበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአንድ ሠራተኛ  በቀን 20 ብር ሲያደርግ የነበረውን የምግብ ድጎማ ወደ ...
26/08/2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ “የምግብ ድጎማ” ማሻሺያ ማድረጉን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአንድ ሠራተኛ በቀን 20 ብር ሲያደርግ የነበረውን የምግብ ድጎማ ወደ 40 ብር ከፍ ማድረጉን አስታውቋል።

በ 2018 በጀት ዓመት የመንግሥት ሠራተኛውን ኑሮ ጫና ለመቀነስ ሲባል የምግብ ድጎማ ማሻሺያ መደረጉን ኢትቲዮቲዩብ የተመለከተው “የምግብ ድጎማ ማሻሺያ” ሰርኩላር ያስረዳል። ይህ ውሳኔ በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተጠሪ ተቋማት ወጥ በሆነ አሰራር ይፈጸማል ተብሏል።

“ለመንግሥት ሰራተኛው የሚያገለግል ካፍቴሪያ በመንግሥት በጀት በማቋቋም ተገቢውን ግብአት በማሟላት በቀን ለአንድ ሠራተኛ 20 ብር በነፍስ ወከፍ የሚሰጠው [የምግብ] ድጎማ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኑን” በከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሐብት ቢሮ የተጻፈው ደብዳቤ ይገልጻል። በድጎማ ማሻሺያው የአንድ የመንግሥት ሰራተኛ የምግብ ድጎማ 20 ብር ተጨምሮለት ወደ 40 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

በዚህ መሠረት የድጎማው አፈፃጸም በሁለት መንገድ ይከናወናል ተብሏል። የመጀመሪያው በተቋማቱ የሚገኘው የሠራተኞች ካፍቴሪያ የሚተዳደረው “በሠራተኛው ሶሻል ኮሚቴ” ከሆነ 10 ብር በሠራተኛው በሥራ ቀናት ተሰልቶ የፍጆታ እቃ ግዢ መፈፀም እንዲችሉ በቀጥታ የበጀት ድጎማው ለሠራተኛ ማኀበራቱ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

ሁለተኛው መንገድ ደግሞ፤በተቋማቱ ያለው ካፍቴሪያ “በሦስተኛ ወገን” የተላለፈ ከሆነ፤ ድጎማው ካፍቴሪያውን ለሚያስተዳደረው አካል የሚተላለፍ ይሆናል ተብሏል። ደብዳቤው አክሎም ካፍቴሪያው በአንድ የምግብ ዓይነት ለሠራተኛው በነፍስ ወከፍ 10 ብር ዋጋ ተቀናሽ ማድረግ እንደሚኖርበት ገልጿል። የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሐብት ቢሮ “በከተማ አስተዳደሩ ለሠራተኛው የተደረገው 20 ብር የምግብ በጀት ድጎማ ውጤታማ በሆነ አግባብ ተፈጻሚ እንዲሆን” ጠንካራ ክትትል እንዲደረግ በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

የእለቱ ምንዛሬዎች
26/08/2025

የእለቱ ምንዛሬዎች

እግዚኦ ...200 in a few Months
26/08/2025

እግዚኦ ...200 in a few Months

26/08/2025

ጓደኛህን ባቡር መንገድ ላይ ቆመህ አትጠብቀው።

የአቶ ሰይድ አይነት ታማኝ : ትሁት: አመለ ሸጋ : ቅን አገልጋይ ሰው ናቸው ።  በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ "አገልጋይነት" ፕሮግራም አንድ ካድሬ ጋዜጠኛ እያፋጠጠ ሲያጉረጠርጥባቸው ተመልክቻለሁ...
25/08/2025

የአቶ ሰይድ አይነት ታማኝ : ትሁት: አመለ ሸጋ : ቅን አገልጋይ ሰው ናቸው ። በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ "አገልጋይነት" ፕሮግራም አንድ ካድሬ ጋዜጠኛ እያፋጠጠ ሲያጉረጠርጥባቸው ተመልክቻለሁ ። የመለሱት የበሰለና የሰከነ ምላሽ አስደምሞኝ ነበር። ነገር ግን የተደራጁ ሰዎች ሊወነጅሉትና ሊከሱት ከአመራርነት ሊያነሱት እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጪ ድርጊት ነበር። ጊዜ ጠብቀው ግን ነክሰውበታል ። ስርቆት የተባለው ነገር እውነት ነው ብሎ መቀበል የማይቻል ዲስኩር ሊሆን ይችላል።

23/08/2025

Address

Gafat
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Taytu Media - ጣይቱ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Taytu Media - ጣይቱ ሚዲያ:

Share

Category