07/02/2021
የፌስቡክ አካውንታችን ሌላ ሰው ሲጠቀም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ሞባይችሁ ላይ እንዲደርሳችሁ ይፈልጋሉ?
እንግደውስ ይህን ይከተሉ።
1.የፌስቡክ አካውንችሁ ውስጥ በተለመደው ሁኔታ ከገቡ በኋላ ሴቲንግ የሚለውን አማራጭ ይጫናሉ ሴቲንግ የሚለው ቦታ እንደ ምትጠቀሙት ብሮዘራችሁ ሰለሚለያይ ፈልጉት
2. በመቀጠልም ከሚመጡት አማራጮች ሴኪዩሪቲ
ሴቲንግ የሚለውን አማራጭ እንመርጣለን ከዚህ በኋላ ሎግ ኢን አለርት የሚለውን አማራጭ እንጫናለን።
3. ከዚህ በኋላም ከተቀመጡት ሶስት አማራጮች ውስጥ ቴክስት ሜሴጅ የሚለው አማራጭን በመጫን የሞባይል ቁጥሮን ያስገባሉ፡፡
4. በመቀጠልም ሴቭ የሚለውን ቁልፍ ሲጫኑ ወደ ሞባይሎ የማረጋገጫ ኮድ ይልክሎታል ይህ ኮድ ሞባይሉ የእርሶ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚላክ ሲሆን ያንን ኮድ ኮምፒተሩ ላይ በተቀመጠው ክፍት ቦታ በማስገባት ሴቭ ማለት በመጨረሻም ቁጥሮ የገባበትን ምርጫ በመጫን ሴቭ ቼንጅስ የሚለውን ስትጫኑ አክቲቭ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ
ይሄን እስቴፕ ተጠቅመን ቤርፊኬሽን አክቲብ ከማድረጋችን በፊት ማወቅ ያለብን
# ምንሞላው ስልክ ቁጥር የራሳችን ሁሌም ከኛጋር የሆነ መሆን አለበት አለበለዚያ ፌስቡካችን ሌላ ስልክ ላይ ወይም ኮምፒውተር ላይ መጠቀም ብንፈልግ በዚያ ስልክ ሚላክልንን ቁጥር ካላስገባን መቸውም መጠቀም አንችልም