11/11/2025
የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ጸድቆ በስራ ላይ የዋለ ቢሆንም የአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ያልጸደቀ መሆኑን በመጥቀስ በአዋጁ አንዳንድ አንቀጾች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ማብራሪያው የተሰጠው የገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች በማሰብሰብ በአዋጁ አንዳንድ አንቀጾች ላይ የገንዘብ ሚንስቴር ማብራሪያ እንዲሰጥበት በጠየቀው መሰረት ነው።
- የገንዘብ ሚንስቴር የአማራጭ አነስተኛ ግብር አፈጻጸምን በተመለከተ
- ቀደም ሲል በሌላ ህግ ነጻ የተደረጉ ግብር ከፋዮች የ2017 በጀት አመት የንግድ ትርፍ ግብር ተጠያቂነትን በተመለከተ
- የትርፍ ድርሻ ላይ ተፈጻሚ ስለሚሆን ታክስ
- የተጠቃለለ የሂሳብ ሰነድ ተግባራዊ ስለሚሆንበት አሰራር
- የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ አማራጭ አነስተኛ ግብር እና ቅድሚያ ታክስ ክፍያ የሚኖረው ተፈጻሚነት
- አማራጭ አነስተኛ ግብር እና የገቢ ግብር እፎይታ
- ሃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር እና የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድን በተመለከተ
- የጥሬ ገንዝብ ግብይት ገደብን በተመለከተ
- የተርን ኦቨር ታክስ አዋጁ መሻርን በተመለከተ ባለ ዘጠኝ ነጥብ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቷል።
(የማብራሪያውን ሙሉ ቃል ከላይ ይመልከቱ)
ማለዳ Post