Zoe Inspiration word.

  • Home
  • Zoe Inspiration word.

Zoe Inspiration word. This page is established to inspire spiritually through out motivating a power inside him/her.

30/09/2023
08/09/2022

“Of Naphtali he said. O Naphtali, satisfied with favor and full of the blessing of the Lord, possess the Sea and the south.”
— Deu 33:23 (AMP)

08/09/2022

Dream big and start small!!

22/04/2022

ኢሳይያስ 61
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
² የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤
³ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።

ይህ ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ትንቢት ስሆን በእርሱ ለሚያምኑ ሕይወት አካል የያዘው ግን ከሙታን ሞትን ድል አድርጎ በትንሳኤ መንፈስ ስነሳ ነው። ትንሳኤው መንፈስ ልውውጡን ያረጋገጠ ማህተማችን ነው። የጽድቅ ዛፍ ተብለን እንድንጠራ፣ ሰው ሲመለከተን እግዚአብሔር የባረከው ሕዝብ ተብለን እንድንጠራ የትንሳኤው መንፈስ፣ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ ፥ በበሽታ ፋንታ መለኮታዊ ጤንነትን ፥ በድህነት ፋንታ ባለጠግነትን ፥ በመጠላት ፋንታ ተቀባይነትን ወይም ሞገስን ፥ በሞት ፋንታ ዘላለማዊ ሕይወትን ፥ በዕርግማን ፋንታ በረከትን ሕይወት ልውውጥ በመለኮታዊ አሰራር እና ስርዓት በትንሳኤው ሆኖልናል። ዛሬ ያው ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው መንፈስ በእኛ ውስጥ ይኖራል። አሜን!!!

ማሳሰቢያ:- ማንም ቢሆን ከየትም ኃይማኖት ቢሆን የትንሳኤን በዓል እንጂ ሕይወቱን ያልቀመሳችሁ የምስራች ለእናንተ "ሕይወትም ፥ ትንሳኤ እኔ ነኝ" ብሎ በተናገረው ክርስቶስ ኢየሱስ እመኑ እርሱም የዘላለም ሕይወትና ትንሳኤን ይሰጣችኃል። የእርሱ ወደ ምድር መምጣት እና ትንሳኤ ዋና ዓላማው በዓሉን እንድናከብር ሳይሆን በእርሱ ለሚያምኑ የዘላለም ሕይወት ሊሰጥ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና ነው። ስለዚህ በእርሱ እመኑ።

ተባረኩ!

መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ። 2014/2022.

14/03/2022

ጸሎት
ጸሎት በሰውና እግዚአብሔር መካከል ነግግር ፣ መነካካት እንዲሆን የሚረደን ወሳኝ መሳሪያ ነው። ለአንድ ክርስቲያን ጸሎት በችግር ጊዜ የሚደረግ ሳይሆን የሁል ጊዜ ተግባሩ መሆን አለበት። በጊዜውም ሆነ አለጊዜውም እንዲንጸልይ የእግዚአብሔር ፊቃድ ነው። የምክንያት ባለጠግነታችን ባለመጸለያችን በቂ መልስ አይደለም።
" አንድ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው ጸልይ የሚል ድምጽ ለመንፈሱ ይናገራል ይሁን ይህ ሰው በጣም ሥራ ስለሚበዛበት በተለምዶ busy ነኝ የሚንለውን በቂ መልስ ነው ለጌታ ብሎ busy ነኝ በማለት ለእግዚአብሔር መልስ ይሰጣል ነገር ግን እግዚአብሔር በምንም ሁኔታ ውስጥ ቢትሆን ባለመጸለይ ምክንያት አልሰማም አለው። ይህ ሰው ፈርቶ መጸለይ ጀመረ።" ስለዚህ ጳውሎስ ሲናገር ሳታቋሮጡ ጸልዩ ይላል። ጸሎት የዕለት ግብራችን እንጂ ሲሞቀን ወይም ሲበርደን የሚንተገብረው ተግባር አይደለም።
ጸሎትን ለሕይወታችን ልማድ ሊሆነን ይገባል ምክንያቱም ጸሎት ከመሎኮት ጋር የሚንነጋገርበት ፣ የሚንገኝበት tool መሳሪያ ስለሆነ ነው።

ጸሎት ከባድ ሥራ ሳይሆን በመንፈስ ነው።

በፍቅር ለመጸለይ:-

# በመንፈስ ቅዱስ በመደገፍ ነው።

በራስህ ማስተዋል አትደገፍ ። በመንፈስ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም። እንዲሁም እንዴት እንደሚንጸልይ አታውቁም መንፈስ ቅዱስ ግን በማይነጠር መቃተት ስለእናንቴ ይቃትትላቸዋል ስለሚል ራሳችንን በመንፈስ ቅዱስ ላይ በመልቀቅ መጸለይ።

#ከሚቾታችን በመልቀቅ

Confort zone ትተን ካልወጣን፣ ሰው በባህርው አምላኩን የሚፈልገው የሚቾት ቦታውን ስለቅ ነው ። ሚቾት አምላኩን እንዳያስረሳው ሚቾቱን በመልቀቅ ለአዲስ ነገር ራሱን ማዘጋጀት አለበት።

# ዋጋ መክፈል (sacrification) መወሰን

ሁሉ ነገር ዋጋ አለው። እግዚአብሔር የሚያስከፊለን ዋጋ ጸሎት ነው። ትልቅ ነገርን ለማግኘት ዋጋ መክፈል ግዴታ ነው።

ተባረኩ። አሜን!!!

14/03/2022

ሊነጋ ስል ጨለማው ይበረታል።
ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር እይታ ውስጥ ናቸው ፣ ደግሞም በአይኑ ፊት ሁሉ ቀላል ነው። የከበደ ነገር ሲገጥምህ ክብደቱ መፍቴው እስክመጣ ብቻ እንጂ እንደ ከበደ የሚቀጥል የለም። የጨለመ የመሰላቹ እስክ ነጋ ብቻ ነው የሚያስፈራው። ሕይወት እንቆቅልሽ የሆነባችሁ መልሱ እስክ መጣ እንጂ ሕይወታችሁ በእንቆቅልሽ አያበቃም። ለሁሉም አይነት ችግር መፍቴው ኢየሱስ ነው። ስለሚባል ሳይሆን እውነትን ተረድቸው ነው። ታውቃላችሁ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ባርነት ከ430 ዓመት በኃላ ነጻ ሊያወጣቸው ሙሴን ባስነሳ ጊዜ ነጻነታቸው በቀረበ ሰዓት የግብፅ ንጉስ ከነጻነት ሀሳባቸው ትኩረትን ለመምታት ከዚህ በፊት በቀን ከሚሰሩት ጡብ ሥራ በእጥፍ ጨመረባቸው ። ምክንያቱም ትኩረታቸውን ከነጻነት ሀሳብ አንስቶ ዘላለም በባርነት ሊገዛቸው። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በጸና ክንዱ ሕዝቡን ነጻ አውጥቷአል። ዛሬም በቃ ቃል መቶልኛል ነጻ ወጥቻለው ብላችሁ ከእንቅልፋችሁ ስትነቁ በሕይወት ያልጠበቃችሁት በአገልግሎት፣ በሥራ፣ በትዳር በተለያዬ መንገድ ያልጠበቃችሁ ነገር ቢገጥማችሁ ግድ የለም ማለፊያችሁ እንጂ መሞቻችሁ አይሆንም። ሚናልባት ያልተፈተነ እምነት በሥራ ስለማይገለጥ ፣ የተፈተነ እምነት ሊሰጣችሁ እንጂ ማልቀሻችሁ አይደለም። በእውነት ሲመሽ ለመንጋቱ የተፈጥሮ ምልክት እንደ ሆነ፣ ስደምን ለመዝነቡ ምልክት እንደ ሆነ ሁሉ ዛሬ ይህን ጽሑፍ ለሚታነቡ ሁሉ ያላችሁበት ሁኔታ ሊትሆኑት ለተፈጠራችሁበት ዓላማ ጋር ለመገናኘት ምልክት ይሆናቸዋል እንጂ የሚያጠፋችሁ አይደለምና አትፍሩ። ታላቅ ሰው ያለበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ሳይሆን ከፊት ለፊቱ ሊሆንለት ያለውን መልካም ነገር አሻግሮ ይመለከታል። ኢየሱስ የመስቀልን ሞት ጣር ለእርሱ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም አሻግሮ በእርሱ አምኖ የፊቱን መልክ የሚመስሉትን ልጆቹን ስመለከት የሞት ጽዋ ጠጣ። እንዲሁ ጠቢብ ሰው ሁል ጊዜ ማየት ያለበት የዛሬውን ሳይሆን ነገን ነው፣ ችግሩን ሳይሆን መፍቴውን፣ ማጣቱን ሳይሆን ማግኘቱን፣ መዉደቁን ሳይሆን ስኬቱን ፣ ስሜቱን ሳይሆን የቃሉን እውነት ፣ አይዕምሮአችን የሚወደውን ማሰላሰል ሳይሆን የጌታን ቃል ሀሳብ ማሰላሰል ነው።

በመጨረሻም ሰይጣን ኃይሉ ተስፋ ማስቆረጥ፣ ማናደድ፣ የሀዘን መንፈስ ፣ ከግብ ማዘግየት ፣ የፍርሃት መንፈስ መልቀቅና አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በማስገባት ትኩረቱንና እምነቱን በማስለቀቅ የተፈጠረበትን ዓላማ እንዳይኖር ማድረግ ነው። ጳውሎስ ስናገር የዲያብሎስን ሀሳብ አንስተውም እንዳለ እኛም ይህን ሀሳቡን በመገንዘብ ከላይ ያሉት መሳሪዎቹን ስለቅ ሥራውን ለማፍረስ ለተገለጠው በኢየሱስ ስም ኃይል ማፍረስ ነው።

ስለዚህ የዛሬ ሁኔታን አይታችሁ እጃችሁን ሰብስባችሁ አትቀመጡ። ምክንያቱም ሁሉም የዓለማችን ታላላቅ ሰዎች ጅማሬያቸው ትንሽ ነው። BIG DREAM START SMALL. በማጠቃለያም ወደ አያችሁት ሕይወት፣ ስኬት፣ ታላቅነት፣ የሚወስዳችሁን ተግባር በትንሹ ጀምሩ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነገራችሁን ያሰፋል።

ተባርካቸዋል። አሜን አሜን!!!!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zoe Inspiration word. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zoe Inspiration word.:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share