ቀዘባ ኪነ-ጥበባት

ቀዘባ ኪነ-ጥበባት 127k Ateronos Ethiopia followers

With Ateronos Ethiopia – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
15/04/2025

With Ateronos Ethiopia – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች በዚህ ሊንክ https://ethiocoders.et/ ይገኛሉ።Ethi...
12/02/2025

በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች በዚህ ሊንክ https://ethiocoders.et/ ይገኛሉ።Ethiopia TVET Community Network መሰረታዊ እውቀት ክህሎት እና አመለካከት https://t.me/dillpoly

08/02/2025
08/02/2025
08/02/2025
08/02/2025

የ2017 ዓ/ም የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ 'ዳራሮ' በዓል በሠላም መከበሩን ተከትሎ የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል

የ'ዳራሮ' በዓል ከምንም በላይ ፈጣሪ ምስጋናውን የሚቀበልበት በመሆኑ ከሁሉ በፊት ማንኛውንም በዓሉን የተመለከተ ነገር ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥተን ነበርና ሳያሳፍረን መሻታችንን የሞላልን ፈጣሪ እግዚአብሔር ምስጋናውን ይውሰደው።

በመቀጠል ለበዓሉ ስኬት ኃላፊነታቸውን የተወጡ አካላት፣ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና ተቋማትን ማመስገን አስፈላጊ ነውና ምንም እንኳን ሁሉንም መጥቀስ ከባድ ቢሆንም እንዲሁ በደፈና ምስጋናችንን ለመስጠት ያህል ነው።

በዓሉ ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከናወን የጌዴኦ ብሔር መሪ አባ ጋዳ ቢፎም ዋቆና ካቢኔያቸው ከወርሃ ጥቅምት መግቢያ አንስቶ ቀላል የማይባል ሚና መወጣታቸው ቱባ ባህላችን ሳይበረዝ ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር ከማድረግም ባሻገር የዳራሮ በዓላችንን በጉጉትና በመደነቅ እንድንጠብቀው ያደርጋልና አባ ጋዳና ካቢኔያቸው ለተወጡት ኃላፊነት ምስጋናዬ ከልብ ነው።

በወረዳና ከተማ አስተዳደሮች እንደየ ሶንጎአቸው በተከታታይ ተከብሮ የመጣ የዳራሮ በዓል ስኬት የእያንዳንዱ ወረዳ አመራሮችና ሃይቻዎች እንዲሁም ሰክቴር መስሪያ ቤቶችና ሌሎችም እውቅና ልሰጣቸው ይገባል።

የዲላ ከተማ አስተዳደር የበዓሉ ደስታ እጥፍ ድርብ እንዲሆን የተጀመሩትን የልማት ፕሮጀክቶችን በማስመረቅና የከተማ ኮሪዴር ልማቱን በአጭር ጊዜ ውጤታማ በማድረግ ላበረከታችሁ አስተዋጽኦ ምስጋናዬ ወደር የለውም በርቱ ለማለት እፈልጋለሁ።

በተለያዩ መንግስታዊ ተልዕኮዎች መካከል በተጣበበ ሁኔታ ዝግጅት ተደርጎ የተከበረው የዞኑ ማጠቃለያ በዓል እንዲሳካ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ኃላፊነታቸውን የተወጡ በተለያየ ዘርፍ የተመደቡ የኮሚቴ አባል አመራሮችና ባለሚያዎችን ከልብ በመነጬ ምስጋና ላከብራቸው እወዳለሁ።

የዞኑን ብሎም የዲላ ከተማን ሠላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ሌሊት ከቀን የሚደክሙ የጸጥታ አካላት፣ ፖሊሶች፣ ህዝባዊ ሰራዊቶች፣ ሚሊሻዎች ያደረጋችሁት አስተዋጽ እንግዶችን ጨምሮ ህዝብ የመሰከረ ነውና እኔም ከልብ አመሠግናለሁ።

በትራንስፖርት ዘርፍ ወደ በዓሉ የመጣውን ህዝብ በማጓጓዝ ጉልህ ሚና የተጫወታችሁ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የትራፊክ ፖልስ አባላት አድናቆቴና ምስጋናዬ እነሆ።

እንቁ የሆናችሁ የዞናችንና የዲላ ከተማ ወጣቶች ዳራሮ በዓላችን ተጨማሪ እሴት እንዲኖረው የሚደነቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ሶሻል ሚዲያውን ጭምር ለበጎ አላማ በመጠቀም ሀብት በማሰባሰብ አቅመ ደካማ ወገኖችን ምግባና ልብስ ማልበስ መቻል ትልቅነታችሁንና የሀገር ባለቤትነታችሁን ያሳያልና በዚሁ ቀጥሉ ምስጋናዬም ከልብ ነው።

በዓሉ ብቻ ሳይሆን ባህላችን ለሀገርና ለዓለም እንድታወቅ የበኩላችሁን ሚና የወጣችሁ ሀገር አቀፍና የአካባቢ የሚዲያ ባለሙያዎችና ተቋማት እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባለውለታዎቻችን ናችሁና እናመሠግናለን።

ክቡር ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልልና ከተለያዩ ዞኖች ጥሪ የደረገላችሁ እንግዶቻችን ጥሪያችንን በማክበር ተገኝታችሁ የዳራሮን በዓል ስላደመቃችሁና ለሰጣችሁን ውድ ስጦታ እጅግ አድርጌ አመሠግናለሁ።

በመጨረሻም የበዓሉ ድምቀት የሆናችሁ የዞናችንና የዲላ ከተማ ህዝብ ላደረጋችሁትና ለምታደርጉት ሁሉ ምስጋናዬ ወደር የለውም በቀጣይም ሁላችሁም ለዞኑ ልማት አብረን ተባብረን እንድንሰራ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ
አቶ አበባየሁ ኢሳያስ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቀዘባ ኪነ-ጥበባት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቀዘባ ኪነ-ጥበባት:

Share