RiseUp Ethiopia

RiseUp Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from RiseUp Ethiopia, News & Media Website, Kazanchis, Addis Ababa.

https://www.youtube.com/watch?v=DJDV66R5Ras
28/02/2026

https://www.youtube.com/watch?v=DJDV66R5Ras

ይህ ዘገባ፣ ከሰሞኑ ኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስመልክቶ፣ የኩባንያውን ቴክኒካዊ የአሰራር ዘዴዎችና እውነተኛ ምስጢሮች፣ በግልጽ የሚያብራራ ነው፡፡

look how this people put their venom inside their children
20/02/2026

look how this people put their venom inside their children

Explore this post and more from the Eritrea community

15/02/2026
አጭር ማጠቃለያ – የIMF ግምገማ ስለ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ1. የሪፎርሙ አጠቃላይ ትዕይንትየኢትዮጵያ “ሀገር በቀል” የተባለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ በተግባር የIMF መዋቅራዊ ሽግግር (SA...
09/02/2026

አጭር ማጠቃለያ – የIMF ግምገማ ስለ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ
1. የሪፎርሙ አጠቃላይ ትዕይንት

የኢትዮጵያ “ሀገር በቀል” የተባለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ በተግባር የIMF መዋቅራዊ ሽግግር (SAP) ነው።

መጀመሪያ 2019 ተጀምሮ፣ በጦርነት ተጓቶ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ግን July 2024 ጀምሯል።

ዓላማው፡ ከመንግሥት-መር ኢኮኖሚ → ወደ የግል-መር (Free Market) ሽግግር።

2. የፕሮግራሙ መጠን እና ገንዘብ

የ4 ዓመት ፕሮግራም (እስከ 2028)

ጠቅላላ ወጪ፡ 10.6 ቢሊዮን ዶላር

IMF: 3.4 ቢሊዮን

World Bank: 3.7 ቢሊዮን

ቀሪው፡ በዕዳ ሽግሽግ

3. እስካሁን የተገኙ ውጤቶች (IMF ግምገማ)

❌ የዕዳ ጫና ተባብሷል

Debt-to-GDP ከ 35.4% → 50.3%

ዋና ምክንያት፡ የብር ፍሎቲንግ (currency floating)

❌ የበጀት ጉድለት

መቀነስ ተብሎ ታቅዶ → 3% ደርሷል

ምክንያት፡ ኮሪደር፣ ሪዞርት፣ የመንግሥት ወጪዎች

⚠️ የኑሮ ውድነት

ነጠላ አሃዝ (9.7%) ተብሏል

ግን IMF ራሱ አጥጋቢ ማብራሪያ አልሰጠም

❌ ድህነት ጨምሯል

ድጐማ መነሳት + ከፍተኛ ታክስ → የሕዝብ ኑሮ ተጫንቋል

4. ድጐማዎች እና ታክስ

February 2026 ጀምሮ የነዳጅ ድጐማ ሙሉ በሙሉ ይነሳ

የኤሌክትሪክ ታሪፍ በየQuarter ይጨምራል

የማዳበሪያ ድጐማ ቀስ በቀስ ይነሳ

ታክስ/GDP ከ 6% → 10.2% ለማድረስ እቅድ

አዲስ ታክሶች (ለምሳሌ የመኪና ባለቤትነት ግብር) በመጪው ጊዜ

5. ብሔራዊ ባንክ እና ፋይናንስ

በ2026 መጨረሻ፡

ብሔራዊ ባንክ ከወርቅ ንግድ ይወጣል

የግል ባንኮች ወርቅ ንግድ ይገባሉ

የባንኮች የብድር ገደብ (24%) ይነሳ

የውጭ ምንዛሬ ገደቦች በዓመቱ መጨረሻ ይነሳሉ

ላኪዎች “50% ዶላር ለመንግሥት” የሚለው ግዴታ ይቀራል

6. ባንኮች እና ፕራይቬታይዜሽን

5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያልሞሉ ባንኮች፡

ወይ merger

ወይ acquisition

ቴሌ 40% ሽያጭ፣ የስኳር ፕሮጀክቶች ፕራይቬታይዜሽን

7. አደጋዎች እና ስጋቶች

የዕዳ ጫና አሁንም ከፍተኛ

ግጭቶች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ) ኢኮኖሚውን ሊያናጋ ይችላሉ

ከኤርትራ ጋር የግጭት ስጋት

FDI እና የውጭ ገንዘብ ፍሰት ቀንሷል

8. ዋና መደምደሚያ

👉 የIMF ፕሮግራሙ መዋቅራዊ ለውጦችን ቢያስገባም
👉 የሕዝብ ኑሮን አጨንቋል፣ ዕዳን አባብሷል፣ ኢኮኖሚውን አደጋ ውስጥ አስገብቷል
👉 እስከ 2028 ድረስ ከፍተኛ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጫና ይጠበቃል።

ጋሽ IMF፡ “ኪሳችሁን ለግብር አዘጋጁ!” እያሉ ነው 😊​IMF የበጀት ጉድለትን ለመሙላትና ልማትን ለማፋጠን ግብር መሰብሰብ ግድ ነው ብሏል። ነገር ግን ነገሩ "እሳትና ጭድ" እንዳይሆን ጥን...
01/02/2026

ጋሽ IMF፡ “ኪሳችሁን ለግብር አዘጋጁ!” እያሉ ነው 😊
​IMF የበጀት ጉድለትን ለመሙላትና ልማትን ለማፋጠን ግብር መሰብሰብ ግድ ነው ብሏል። ነገር ግን ነገሩ "እሳትና ጭድ" እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ያለአቅም የሚጫን ግብር ንግድን ሊያቀዘቅዝ አልፎ ተርፎም ማህበራዊ ውጥረት ሊፈጥር ስለሚችል፣ ፖሊሲው የህዝቡን ኑሮና መረጋጋት ያገናዘበ እንዲሆን መክረዋል። ባጭሩ ገቢውም ይደግ፣ ሰላሙም ይጠበቅ!

1. Framing starts from Egypt’s needs, not equality“we understand the deep significance of the Nile River to Egypt and it...
17/01/2026

1. Framing starts from Egypt’s needs, not equality

“we understand the deep significance of the Nile River to Egypt and its people”
“assures the water needs of Egypt…”

The statement centers Egypt first, emotionally and politically.

Ethiopia’s needs are mentioned later and conditionally, which signals priority hierarchy, not parity.

Ethiopia has always rejected any framing that treats Egypt’s water needs as superior or pre-existing rights.

2. Implied validation of Egypt’s historical claims

“assures the water needs of Egypt, the Republic of the Sudan, and Ethiopia”

Ethiopia’s position is the opposite:
👉 No country has guaranteed historical quotas over a river that originates in another sovereign state.

3. U.S. mediation positioned as protector of Egypt’s interests

“I am ready to restart U.S. mediation…”

Ethiopia explicitly rejected U.S.-led mediation in the past (especially after the 2020 Washington talks).

The U.S. is widely viewed in Addis Ababa as aligned with Egypt, not neutral.

4. Power generation framed as a concession, not a right

“allowing Ethiopia to generate very substantial amounts of electricity”

This wording suggests Ethiopia’s hydropower use is something granted if others agree.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔን ማንሳቱን ተከትሎ ምን ሊፈጠር ይችላል?------የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለረዥም ጊዜ ጥሎት የነበረውን የ7% ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ አንስቶ የ...
06/01/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔን ማንሳቱን ተከትሎ ምን ሊፈጠር ይችላል?
------
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለረዥም ጊዜ ጥሎት የነበረውን የ7% ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ አንስቶ የቁጠባ ወለድ በገበያ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲወስን ፈቅዷል።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የOpen market operation ፖሊሲ ከተገበረ እና የፖሊሲ ወለድ ተመንን /Policy Rate/ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር እንደ ገንዘብ ፖሊሲ መሳሪያ መጠቀም ከጀመረ በኋላ የዝቅተኛ የወለድ ምጣኔን እንደሚያነሳ በብዙ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ሲጠበቅ ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ ምጣኔ ፖሊሲ መቅረትን ተከትሎ የሚጠበቁ ኩነቶች፣

፩. ከገንዘብ አስቀማጮች ጋር በተያያዘ፣

💰 ባንኮች ቁጠባ ለመሰብሰብ በሚያደርጉት ፉክክር በተለይም ከፍተኛ የተቀማጭ ገንዘብ አስቀማጮች የድርድር አቅም ስለሚኖራቸው ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ሊከፈላቸው ይችላል።

💰 በባንኮች ቋት ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ክምችት ሲኖር እና የብድር ፍላጎት ሲቀዛቀዝ እንደ ገበያው ሁኔታ የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ ዝቅ ሊል ይችላል።

💰 በገበያው ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ካለና ባንኮች የሚከፍሉት ወለድ ከዋጋ ንረቱ በታች ከሆነ የቆጣቢዎች ትክክለኛ የሀብት መጠን ሊቀንስ ይችላል።

፪. ከገንዘብ ተበዳሪዎች ጋር በተያያዘ

💵 ባንኮች የተቀማጭ ገንዘብ ክምችታቸው ለማሻሻልና ቁጠባን ለመሳብ በቁጠባ ሒሳብ ላይ የሚከፈል ወለድ ከፍ ካደረጉ ያንን ተከትሎ የሚፈጥርባቸውን የወለድ ወጪ ለማካካስ ተበዳሪዎች ላይ የብድር ወለድ ሊጨምሩ ይችላል። (ኢትዮጵያ ውስጥ fixed interest ብድር ስለሌለ አብዛኛው ተበዳሪ የእዚህ ፖሊሲ ሰለባ ሊሆን ይችላል)

💵 በተቃራኒው ባንኮች በቋታቸው የሚይዙት የቁጠባ ገንዘብ እጅግ ከበዛና የብድር ፍላጎት ከተቀዛቀዘ በቁጠባ ሒሳብ ላይ የሚከፍሉትን ወለድ ዝቅ ያደርጋሉ። ለተበዳሪዎቻቸውም የብድር ወለድ ሊቀንሱ ይችላሉ።

፫. በባንኮች መካከል የሚፈጠር ውድድር፣

🏦 ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ችግራቸውን ለመቅረፍና ላብድር የሚውል የገንዘብ ክምችታቸውን ለማሻሻል የቁጠባ ወለድ በመጨመር ደንበኛን ለመሳብ መወዳደር ይጀምራሉ፤ ውድድሩ በቅጡ ካልተገራ ወዳልተፈለገ የወለድ ጦርነት ሊያመራ ይችላል።

🏦 ባንኮች አስቀማጮችን ለመሳብ አዳዲስ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶችን ሊያስተዋውቁ ይችላሉ። (ከእዚህ ቀደምም የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የልጆች፣ የትምህርት፣ ፕሪሚየም ምናምን በሚሉ የቁጠባ ሒሳቦችን በማስተዋወቅ ከ 7% የበለጠ ወለድ ሲከፍሉ የነበሩ ባንኮች ነበሩ)

፬. ከባንክ ውጪ የሚዘዋወር ገንዘብ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ፣

💵 ባንኮች ሳቢ የሆነና እንደ ኢንቨስትመንት ሊቆጠር የሚችል የወለድ ምጣኔ ካስተዋወቁ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከባንክ ውጪ ያስቀመጧቸውን ገንዘቦች ወደ ባንክ ማምጣት ይጀምራሉ፣ ከባንክ ውጪ ያለ የገንዘብ መጠን ይቀንሳል።

💵 የወለድ መጠን በጣም ዝቅተኛ ከሆነ እና የአስቀማጮች ገንዘብ በዋጋ ንረት ትክክለኛ ዋጋው የሚቀንስ ከሆነ ሰዎች ገንዘባቸውን በእጃቸው መያዝን፣ አሊያም ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ሊያውሉ ይችላሉ።

፭. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በOpen Market Operation ፖሊሲው የሚያወጣውን የፖሊሲ የወለድ ምጣኔ ጋር በተያያዘ፣

ሀ. ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አማላይ የሆነ የፖሊሲ የወለድ ምጣኔን /Policy Rate/ በማውጣትና Treasury Bill በመሸጥ ከገበያ ላይ ያለውን ገንዘብ በመሰብሰብ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲን ሊተገብር ይችላል። ይህ ፖሊሲ ሰዎች ገንዘባቸውን በቢል ግዢ ላይ የማዋል አማራጭ ስለሚኖራቸው ባንኮች የተቀማጭ ገንዘብ ላይ የሚከፈሉትን ወለድ ከፍ ሊያደርገው ይችላል።

ለ. ልል የገንዘብ ፖሊሲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በገበያው ላይ የዋጋ ንረት በሚፈለገው ልክ ከቀነሰ የፖሊሲ የወለድ ምጣኔውን ሊቀንስ ይችላል። ከእዚህ በተጨማሪ ሌሎች ተቋማት የሚያወጧቸውን የtreasury Bills በመግዛት በገበያው ላይ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን ይጨምራል። ይህ በሚሆን ሰዓት ባንኮች ወለድ መቀነስ ይጀምራሉ።

እንደመውጫ፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔን አነሳ ማለት በእጅ አዙር የባንኮችን የቁጠባ ወለድ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ የገንዘብ ፖሊሲን አይጠቅምም ማለት አይደለም። ኢብባ የዋጋ መረጋጋትን ለመፍጠር በየጊዜው የፖሊሲ የወለድ ምጣኔውን ከፍና ዝቅ ያደርጋል። ይሄ ደግሞ በተዘዋዋሪ ባንኮች የወለድ ክፍያቸውን ከፍና ዝቅ እንዲያደርጉ ማስገደዱ አይቀሬ ይሆናል።
------------
በሚቀጥለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣው የፖሊሲ የወለድ ምጣኔ ከባንኮች አንጻር ብቻ ሳይሆን በካፒታል ገበያው ውስጥ የሚሸጡ ሰነድ መዋእለ ነዋዮች ላይ ያለውን ተጽእኖ በተመለከተ የምለው ይኖረኛል።

መልካም የገና በዓል ዋዜማ!🎄

በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከሆኑት የቢራ አምራቾች አንዱ የሆነው የሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማኅበር፣ በኢንዱስትሪው ላይ የተጣለው የ40% ኤክሳይዝ ታክስ እና አዲሱ የዲጂታል ኤክሳይዝ ታክስ ስታምፕ አሠራር...
06/01/2026

በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከሆኑት የቢራ አምራቾች አንዱ የሆነው የሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማኅበር፣ በኢንዱስትሪው ላይ የተጣለው የ40% ኤክሳይዝ ታክስ እና አዲሱ የዲጂታል ኤክሳይዝ ታክስ ስታምፕ አሠራር በኩባንያው የፋይናንስና የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑን አስጠነቀቀ።

ኩባንያው እንደሚገልጸው፣ ይህ 40 በመቶ የታክስ ተመን ታክሱ ምርቱ ከፋብሪካ ቅጥር ግቢ በወጣ ቅጽበት የሚታሰብና የሚከፈል በመሆኑ፣ ተቋሙ ገና ምርቱን ለገበያ አቅርቦ ገቢ ሳያገኝ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለመንግሥት እንዲያስረክብ ይገደዳል።

ይህ አሠራር በተለይ እንደ ሐበሻ ቢራ ላሉ በማስፋፊያና በከፍተኛ የሥራ ማስኬጃ ወጪ ውስጥ ላሉ ኩባንያዎች ትልቅ የፋይናንስ ጫና ፈጥሯል።

ከነባሩ የታክስ ጫና በተጨማሪ፣ መንግሥት የንግድ ቁጥጥርን ለማጥበቅ ያስተዋወቀው የዲጂታል ኤክሳይዝ ታክስ ስታምፕ ሥርዓት ለኢንዱስትሪው ሌላው ትልቅ ስጋት ሆኗል። ሐበሻ ቢራ እንደገለፀው ፤ ይህ ሥርዓት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ወደ 372.3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ቀጥተኛ ወጪ ያስከትላል።

ይህ በአዲስ አበባ ሰፈር በአንድ ምግብ ቤት ላይ የደረሰው አነስተኛ የእሳት አደጋ፣ በግርግሩ መሀል የታየው አስቂኝ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።​በምግብ ቤቱ ላይ ...
05/01/2026

ይህ በአዲስ አበባ ሰፈር በአንድ ምግብ ቤት ላይ የደረሰው አነስተኛ የእሳት አደጋ፣ በግርግሩ መሀል የታየው አስቂኝ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
​በምግብ ቤቱ ላይ እሳት ተነስቶ አካባቢው በጭስና በግርግር ሲታመስ፣ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋትና ንብረት ለማዳን ይረባረባሉ፤ ሌላው ደግሞ በድንጋጤ ይሮጣል። በዚህ ሁሉ መሀል ግን አንድ አስገራሚ ኢትዮጵያዊ የታዘዘውን ምግብ ይዞ በሰላም ሲወጣ ታይቷል። የሚገርመው ግን በሰላም መውጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ እሳቱ ሲጠፋና ግርግር በበዛበት በዚያ ቅጽበት በሰው መሃል ቆሞ በኩራት ምግቡን እየበላ ትዕይንቱን መመልከቱ ነው።
​ይህንን ቪዲዮ በኢንተርኔት የተመለከቱ ሰዎች ግለሰቡ ላሳየው "ግርግር የማይበግረው" ሆድ እና ፍጹም ግድየለሽነት (Unserious behavior) በመገረም በሳቅ ተሞልተዋል። "ምግብ አይቀለድበትም" የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየው ይህ ሰው፣ በዛ አስፈሪና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ምግቡን ጥሎ ላለመውጣቱ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትንና ሳቅን አትርፏል።
​በእውነት በግርግር መሀል እንዲህ አይነት ዘና ያለ ስሜት ማሳየት ከባድ ቢሆንም፣ ይህ ግለሰብ ግን ለሆዱ ቅድሚያ በመስጠት የዕለቱ የሳቅ ምንጭ ሆኗል።

Address

Kazanchis
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when RiseUp Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share