28/11/2025
#ምክረ #አበው
ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡
ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡
እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡
ይኑርህ፡፡ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና
ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡
ወደ ጠብ አትግባ፡፡
Fíŕěŵ Těŵâĥďő ለወዳጅዎ ሼር ያርጉላቸው
ከቅዱስ ገብርኤል በረከት ያሳትፈን
19/03/2018 ዓ ም 🙏