Arat ayin Media አራት ዓይን

Arat ayin Media አራት ዓይን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arat ayin Media አራት ዓይን, Media/News Company, Addis Ababa.

ወቅታዊና ትኩስ ሁሉን አቀፍ ዜና ይቀርብበታል
👉 ትኩረት የሚሹ ነጥቦች
🔴 ተደማጭ ጉዳዮች
🕘 ወቅታዊ
⚽ስፖርታዊ ጉዳይ
🌎አለም አቀፍ ዜና
🎭መዝናኛ
👉በተጨማሪም📻 በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ማክሰኞ ከ8:00 እስከ 9:00 እሁድ ከ3:00 እስከ 4:00 ይደመጣል።🚨
አራት አይን በሁሉም ቦታ

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚያቀርቧቸው የመዝናኛ ፕሮግራሞች በስፋት የሚታወቁት ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ እና ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማ፣  የኢትዮፒካር የተሰኘው የመኪና አስመጪ ድርጅት አዲስ ለሚያስገባው ...
19/09/2025

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚያቀርቧቸው የመዝናኛ ፕሮግራሞች በስፋት የሚታወቁት ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ እና ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማ፣ የኢትዮፒካር የተሰኘው የመኪና አስመጪ ድርጅት አዲስ ለሚያስገባው የኤሌክትሪክ መኪና ብራንድ አምባሳደር ሆነው መመረጣቸው ተገለጸ።ዝርዝሩን በሊንኩ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/icNmSf8tAQc
https://youtu.be/icNmSf8tAQc

19/09/2025

ታሪክን የኋሊት

የጠፋው የፈርዖን አምባር ለወርቅነት ቀልጦ ተገኘ+++++++++++++ #ከግብጽ ሙዚየም የጠፋውና ከሀገር እንዳይወጣ በአየር መንገዶች ቁጥጥር ሲደረግበት የቆየው የፈርዖን አምባር ለወርቅነት ቀ...
19/09/2025

የጠፋው የፈርዖን አምባር ለወርቅነት ቀልጦ ተገኘ
+++++++++++++

#ከግብጽ ሙዚየም የጠፋውና ከሀገር እንዳይወጣ በአየር መንገዶች ቁጥጥር ሲደረግበት የቆየው የፈርዖን አምባር ለወርቅነት ቀልጦ ተገኘ መገኘቱን የሀገሪቱ የቅርሶችና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከግብጽ ሙዚየም የጠፋው የሶስት ሺህ ዓመት ዕድሜ ያለው የወርቅ አምባር ተሰርቆ ለወርቅነት መቅለጡ ተገልጿል።

ቅርሱ ከክርስቶስ ልደት በፊት ግብጽን ያስተዳድሩ የነበሩት የንጉሥ አሜነሞፔ ንብረት ነበር ተብሏል።

ቅርሱ ከተሰረቀ በኋላ ከሀገር ሊወጣ ይችላል በሚል በአየርመንገዶች ላይ ቁጥጥር ሲደረግ ቢቆይም ስርቆቱን ያደረገው ግን አንድ የሙዚየም እድሳት ባለሙያ ሆኖ ተገኝቷል።

ባለሙያው ቅርሱን ወስዶ ለብር ነጋዴ የሸጠዉ ሲሆን ይህ ነጋዴም ለወርቅ አቅላጭ ሽጦታል። አቅላጩም ብረቱን ከሌሎች ነገሮች ጋር አጣምሮ እንዳቀለጠው ሚኒስቴሩ መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል።

Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
#ግብጽ #ፈርኦን

19/09/2025

የልጅቷ ፈጣን ምላሽ

19/09/2025

አለማሁ እሸቴ ዘና በሉ ሸጋ ቀን

የመሬት መሰንጠቅ አደጋው ውጤት ይፋ ሆነ   | በሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም አካባቢ በተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ አደጋ ዙሪያ ጥናት ሲያደርጉ የነበሩ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች የጥናቱ ዉጤቱን ይ...
19/09/2025

የመሬት መሰንጠቅ አደጋው ውጤት ይፋ ሆነ

| በሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም አካባቢ በተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ አደጋ ዙሪያ ጥናት ሲያደርጉ የነበሩ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች የጥናቱ ዉጤቱን ይፋ አደረጉ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ሚኪሊላንድ ኮንዶሚንየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተውን የመሬት መሰንጠቅ ተከትሎ የተከሰተዉ አደጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጂ ሳይንስ ባለሙያዎች ቡድን ጥናት አስጠንቷል፡፡

የጥናት ቡድኑም የደረሰበትን የጥናት ውጤት በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ነገሰ ሞላ በአካባቢው የደረሰው የመሬት መሰንጠቅ መንስኤ ኮንዶሚኒየሞቹ ሲገነቡ የተቆፈረ ምልስ አፈር በአካባቢው መኖሩና፣ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርቶችም የተደፉበት ስፍራ እንደሆነ በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡

እንደ ተመራማሪው ገለፃ፣ በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎችን ከአደጋው ለመከላከል የሚያስችሉ ጊዜያዊና ዘላቂ የመፍትሄ ሀሳቦችም በጥናቱ ተመላክተዋል፡፡

የመሬት መሰንጠቅ ከደረሰበት በቅርብ እርቀት የሚኖሩ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ ማዛዎር ጊዚያዊ መፍትሄ መሆኑን የጠቆሙት ከፍተኛ ተመራማሪው፣ የአካባቢውን የፍሳሽ አወጋገድ በአግባቡ ማስተካል ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ እንደሆነ በጥናቱ መረጋገጡና ተናግረዋል፡፡

አሁን የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ አደጋ የበለጠ እንዳይስፋፋ አካባቢውን ከተሸከርካሪም ሆነ ከሰዎች እንቅስቃሴ መገደብ ተገቢ መሆኑንም ከፍተኛ ተመራማሪው ነገሰ ሞላ አሳስበዋል።

ኔታንያሆ ቻርሊ ኪርክን በተመለከተ "እኛ አል*ገደልነውም" የሚል መግለጫ አውጥቷል። ከሰሞኑ ለሚዲያ ከሰጠው ምልልስ በተለየ ይህኛው ለሁለተኛ ጊዜ በሳምንት ውስጥ ማስተባበል ያደረገበት መሆኑ ...
18/09/2025

ኔታንያሆ ቻርሊ ኪርክን በተመለከተ "እኛ አል*ገደልነውም" የሚል መግለጫ አውጥቷል።
ከሰሞኑ ለሚዲያ ከሰጠው ምልልስ በተለየ ይህኛው ለሁለተኛ ጊዜ በሳምንት ውስጥ ማስተባበል ያደረገበት መሆኑ አስገርሟል።

ይህ ሰው ታዲያ "እንዴት በዚህ ትጠረጥሩናላችሁ?" አይነት ንግግሩን ሲያሰማ ነበር።

ጃራ‼️በአማራ ክልል በሠልጣኝ ሚሊሻዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት "ቢያንስ 39 ሰዎች" መገደላቸውን ተነገረ‼️በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ታጣቂዎች በማሠልጠኛ ካምፕ ውስጥ በነበሩ የሚሊሻ አባላት...
18/09/2025

ጃራ‼️
በአማራ ክልል በሠልጣኝ ሚሊሻዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት "ቢያንስ 39 ሰዎች" መገደላቸውን ተነገረ‼️
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ታጣቂዎች በማሠልጠኛ ካምፕ ውስጥ በነበሩ የሚሊሻ አባላት ላይ በፈጸሙት ጥቃት "ቢያንስ 39 ሰዎች" መገደላቸውን የዓይን እማኞቹን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ጥቃቱ የተፈጸመው ሰኞ መስከረም 5/2018 ዓ.ም. ለማክሰኞ አጥቢያ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አንድ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊ በሠልጣኝ የሚሊሻ አባላት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ቢቢሲ ምንጮቹን ጠቅሶ ማረጋገጡንና የደረሰውን የጉዳት መጠን በተመለከተ መረጃ "እየተሰበሰበ" መሆኑን አክሏል።

ጥቃት የተፈጸመበት የሥልጠና ስፍራ፤ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከሰፈሩበት ጃራ መጠለያ ጣቢያ አጠገብ የሚገኝ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በመጠለያ ጣቢያው ነዋሪ የሆኑት ሦስት ግለሰቦች እንደገለጹት የሥልጠና ስፍራው ከዚህ ቀደም የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሥልጠና የወሰዱበት ነው ተብሏል።
አብዛኞቹ የሞቱት ከራያ አላማጣ ዙሪያ የመጡ ናቸው ተብሏል።
#አዩዘሀበሻ
==============

አሳዛኝ አሟሟት 💔 ይህች ሴት ከእንግሊዝ አገር ወደ አዲስ አበባ ከመጣች በኋላ ያረፈችበት ሆቴል ውስጥ ሞታ ተገኝታለች። ዘመዶቿ ከሆናችሁ ወይንም የምታውቋት ካላችሁአዲስ አበባ እንግሊዝ ኤምባ...
18/09/2025

አሳዛኝ አሟሟት 💔

ይህች ሴት ከእንግሊዝ አገር ወደ አዲስ አበባ ከመጣች በኋላ ያረፈችበት ሆቴል ውስጥ ሞታ ተገኝታለች። ዘመዶቿ ከሆናችሁ ወይንም የምታውቋት ካላችሁአዲስ አበባ እንግሊዝ ኤምባሲ በመሔድ ንብረቷንና ልጇን እንድትረከቡ እናሳስባለን።
ሼር በማድረግ ቤተሰቧን እናፈላልግ 🙏
sunney semere

የዶ/ር ሀውለት አህመድ ልጅ የ12ኛ ክፍል መውጫ ፈተና በከፍተኛ ነጥብ አምጥቷል! እንኳን ደስ አለሽ/አለ🌟🌟   እናትም እንዲህ ብላ ፅፋለች✍️  *የመጀመሪያ ልጄ ነው። ዘንድሮ ከፍተኛ ውጤት...
18/09/2025

የዶ/ር ሀውለት አህመድ ልጅ የ12ኛ ክፍል መውጫ ፈተና በከፍተኛ ነጥብ አምጥቷል! እንኳን ደስ አለሽ/አለ🌟🌟

እናትም እንዲህ ብላ ፅፋለች✍️

*የመጀመሪያ ልጄ ነው። ዘንድሮ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ይገኛል። ወደፊት የተማረ ትልቅ ሥም ያለው እግር ኳስ ተጫዋች መሆን ነው የሚፈልገው። ላለፉት 3 ዓመታት ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት የእግር ኳስ አካዳሚ ውስጥ ይሰለጥናል። እንደ እውነቱ ከሆነ ለኳስ 70% ለትምህርት 30% ብቻ የሚሰጥ ቢሆንም በጣም ዲሲፕሊንድ የሆነ ልጅ ነው። በብዙዎች የተደነቀ የመሐል ተጫዋች (Midfielder) ነው። እኔም ፍላጎቱን መጫን ስለማልፈልግ ኳስ ተጫዋች የመሆን ፍላጎቱን እደግፋለሁ። በዚህ ጉዳይ guide የሚያደርገን ወይም የሚደግፈን ሰው/ተቋም ካለ በደስታ እንጠብቃለን።

የኔ ልጅ 18 ዓመት ሞልቶት ለዚህ እስኪበቃ በምንም የማይተመን አስተዋጽዖ ያደረጉ 2 ግለሰቦችን እና አንድ ተቋምን ላመሰግን እፈልጋለሁ።

1ኛ. ዶ/ር አብዱልናስር አብዱላሂ - የሕፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም።
(3S የሕፃናት እና ወጣቶች ስፔሻላይዝድ ክሊኒክ)

በቃ አለ አይደል? ልምድ፣ እውቀት፣ ብቃት፣ ዲሲፕሊን አንድ ላይ ሲገኙ?! .... ማሻአላህ!!! ዶ/ር አብዱልናስር ለሐኪሞች የምሰጠውን ክብር በጣም እንድጨምር ያደረገኝ ሁሌም የምገረምበት ሐኪም ነው። ልጄ የ14 ቀን infant እያለ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ጤንነቱ ሳይጓደል በሕክምና እና የምክር አገልግሎት በመስጠት እዚህ ስላደረሰልኝ አላህ የምኞቱን ይሙላለት። ሐያቱንም ያርዝመው።

2ኛ. ከተማ ተሊላ - ሾፌር

ሾፌርነት ትልቅ ኃላፊነት ያለበት ሞያ ነው። ከተማ ከሚጠበቅበት ኃላፊነት በላይ የሚወጣ የሚገርም ሾፌር ነው። ለበርካታ ዓመታት የኔን ልጅ ጨምሮ ሌሎች በርካታ ልጆችን በከፍተኛ ኃላፊነት አድርሶ መመለስ ብቻ ሳይሆን እየመከረ፣ እየተቆጣ እንዲሁም እያጫወተ ልጆችን የሚያንጽ ዲሲፕሊኑ የሚገርም ሰው ነው። አላህ እርዚቁን ይጨምርለት።

3ኛ. ጊብሰን ዩዝ አካዳሚ

በተለይ በልጆች ስነ-ምግባር በኩል ምንም ቀልድ የማያውቅ ት/ቤት ነው። ጥብቅ መሆናቸውን እወደዋለሁ። ከPre-KG ጀምሮ የልጄን የትምህርት ይዞታ የምከታተል እንደመሆኔ ስለትምህርት ቤቱ በቂ ግንዛቤ አለኝ። በእውነት ብዙ ልጆች ቢኖሩኝ ሁሉንም ልጆቼን አይኔን ሳላሽ ላስተምርበት የምመርጠው ት/ቤት ነው። ጥቃቅን ጉድለቶቻቸውን አርመው ሁሌም የተሻለ እንደሚያደርጉት አምናለሁ። ት/ቤቱን በጣም አመሰግናለሁ!

ለልጆቻችን እድገትና ውጤት ብቻችንን አልለፋንም! በዙሪያችን አሻራቸውን ያኖሩ መልካም ሰዎችና ተቋማት አሉ! ይመስገኑ!
❤️🙏

የፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሚስት "ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ" ለፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰማ።የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ለጉብኝት ወደ ደ...
18/09/2025

የፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሚስት "ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ" ለፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰማ።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ለጉብኝት ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያዊቱ ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ከአውሮፕላን ሊወርዱ ሲሉ የባለቤታቸውን ቀዳማዊት እመቤት ብሪጄት ማክሮን "ጥፊ ሲቀምሱ" በካሜራ ዕይታ ውስጥ ከገቡ ወዲህ በርካታ የሴራ ተንታኞች "የማክሮን ሚስት ዓለም ያወቀውን የአገር መሪ በአደባባይ የሚደበድቡት ወንድ ቢሆኑ ነው ፤ ፊታቸውም የሚያሳብቀው ይሄንኑ ነው" በማለት ውንጀላ ማቅረብ መጀመራቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ እና ባለቤታቸው የስም ማጥፋት ክስ መስርተው ጉዳዩ በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ይሁንና ክሱ የተመሠረተው በአሜሪካ በመሆኑ ፤ በአገሪቱ ሕግ መሠረት በታዋቂ ሰዎች ላይ የስም ማጥፋት ተፈጽሟል የሚል ውንጀላ ሲቀርብ ከሳሽ ወገን ተከሳሹ "ሆን ብሎ ጉዳት ለማድረስ ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱን" ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ሲሆን ይህንን ተከትሎም የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለቤታቸው ብሪጄት ማክሮን ፣ ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፎቶግራፍ እና ሳይንሳዊ ማስረጃ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰምቷል።

ከቢቢሲ ፌም አንደር ፋየር ፖድካስት ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀዳማዊት እመቤት ብሪጄት ማክሮን ጠበቃ ቶም ክሌር ፣ ይህ የስም ማጥፋት ዘመቻ "በከፍተኛ ሁኔታ የሚያበሳጭ" እና በፕሬዝዳንቱ ላይም ተጽዕኖ ያሳደረ ነው ብለው ቀዳማዊት እመቤቷ እርጉዝ ሳሉ እና ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ጨምሮ ሌሎች ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርበን በሐሰት የጠፋው ስማችንን ለማደስ ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል።

ፆታ ሊያስፈትሹ‼️የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የባለቤታቸውን ጾታ ሴትነት ለማረጋገጥ ሊያስፈትሹ ወስነዋል ተባለ!!የትዳር አጋራቸው ቀዳማዊት እመቤት ብሪጂት በተደጋጋሚ ጾታቸውን የቀ...
18/09/2025

ፆታ ሊያስፈትሹ‼️
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የባለቤታቸውን ጾታ ሴትነት ለማረጋገጥ ሊያስፈትሹ ወስነዋል ተባለ!!

የትዳር አጋራቸው ቀዳማዊት እመቤት ብሪጂት በተደጋጋሚ ጾታቸውን የቀየሩ ወንድ እንጂ ሲወለዱ ሴት አልነበሩም የሚለውን ወቀሳ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ሊያስፈትሿቸው ነው።

ከፍተሻው በኋላም ፕሬዝዳንት ማክሮን ሚስታቸውን በፎቶ እና በሳይንሳዊ ማስረጃ ሴት መሆኗን ለአለም ያሳያሉ ተብሏል።

ቀዳማዊት እመቤት ብሪጂት በወርሃ ግንቦት በቬትናም ጉብኝታቸው ወቅት የባለቤታቸውን ፊት ጥፊ በሚመስል መልኩ ሲገፈትሩ መታየታቸውን ተክትሎ በጾታቸው ጉዳይ እውነቱ እንዲታወቅ ግፊት እየተደረገባቸው ይገኛል።
#ቢቢሲ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251938668562

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arat ayin Media አራት ዓይን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Arat ayin Media አራት ዓይን:

Share