Sololo News

Sololo News Social media is the ultimate equalizer. It gives a voice and a platform to anyone willing to engage.

 #ዜናመሠረት የመጠቀሚያ ግዜው አልፎበት ወደ ሀገር እንዳይገባ ታግዶ የነበረ የቱርክ የስንዴ ዱቄት በቅርቡ በድብቅ መግባት መጀመሩ ተደረሰበት (ይህ ዜና ግንቦት 1/2017 ዓ/ም ቀን ለመሠረ...
19/05/2025

#ዜናመሠረት የመጠቀሚያ ግዜው አልፎበት ወደ ሀገር እንዳይገባ ታግዶ የነበረ የቱርክ የስንዴ ዱቄት በቅርቡ በድብቅ መግባት መጀመሩ ተደረሰበት

(ይህ ዜና ግንቦት 1/2017 ዓ/ም ቀን ለመሠረት ሚድያ ከፋይ አባሎች 'paid subscribers' ቀርቦ የነበረ ነው)

(መሠረት ሚድያ)- የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሁለት ግዜ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ አግዶት የነበረ ቱርክ የተመረተ የስንዴ ዱቄት በድብቅ በድጋሚ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑን ሚድያችን ያደረገው ክትትል ያሳያል።

ሚያዝያ 3/2017 ዓ/ም 210 ሜትሪክ ቶን እንዲሁም ታህሳስ 10/2017 ዓ/ም 40 ሜትሪክ ቶን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ የታገደበትን ደብዳቤ ሚድያችን የተመለከተ ሲሆን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊው አቶ ተስፋዬ ሀድጉ ፈርመውበታል።

ለጉምሩክ የተፃፈው ይህ ደብዳቤው "በመርከቦ ደራር አላሌ ተመዝግቦ እና ተጭኖ የመጣው ይህ ዱቄት በምርቱ ላይ በተደረገ ፍተሻ የኢትዮጵያን አስገዳጅ ደረጃ ያላሟላ ስለሆነ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ" የሚል ሲሆን ጉምሩክ አፈፃፀሙ ላይ ክትትል እንዲያደርግ ይጠይቃል።

መሠረት ሚድያ የተመለከታቸው ምስሎች እንደሚያሳዩት እነዚህ የስንዴ ዱቄት ከረጢቶች ከወራት በፊት የመጠቀሚያ ግዜያቸው አልፎባቸዋል፣ ስለዚህ እንዲህ አይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ የመጠቀሚያ ግዜያቸው ቢያንስ ስድስት ወር የሚቀረው መሆን አለበት የሚለውን አሰራር አያሟላም።

ያደረግነው ክትትል እንደሚያሳየው ዱቄቱ ከወራት በፊት እንዲመለስ ቢደረግም አሁን ላይ ከጅቡቲ በድጋሜ እየተጫነ እና የጉምሩክን አሰራር በማስቀረት በህገወጥ መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው።

"አሁን ድረስ ይህን ዱቄት የጫኑ መኪናዎች ስንዴውን እያጓጓዙ ነው፣ ለዚህ ስራ ደዋሌ ላይ ያሉ ተሳቢ መኪናዎች አሉ" ያሉን አንድ ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ምንጫችን ድርጊቱ የህዝብ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል የሚመለከው አካል ክትትል እንዲያደርግ ጠቁመዋል።

ስንዴውን እያስገባ ያለው ድሬዳዋ መቀመጫውን ያደረገ፣ በጫት ንግድ የሚታወቅ እና በአዳማ የአልፋ ዱቄት ፋብሪካ ባለቤት የሆነ ግለሰብ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

መረጃን ከመሠረት!

*የምናወጣቸውን መረጃዎች በእለቱ ለማግኘት ከፋይ አባል (paid subscriber) ይሁኑ ⤵️

https://substack.com/

እሄ እርካብና፡መንበር የሚለው የአብይ መጽሃፍ ላይ የጻፈው ነው ።ለሱ ቤተመንግስት ሲሰራ ይህንን ጽሁፉን አላስታወሰም ማለት ነው ?
19/05/2025

እሄ እርካብና፡መንበር የሚለው የአብይ መጽሃፍ ላይ የጻፈው ነው ።
ለሱ ቤተመንግስት ሲሰራ ይህንን ጽሁፉን አላስታወሰም ማለት ነው ?

Gaaffiin ogeessota fayyaa gaaffii haqaati. Balaa daddabalee uummata irratti kan fidaa jiru Abiyyi. Kan itti gaafatamus A...
19/05/2025

Gaaffiin ogeessota fayyaa gaaffii haqaati. Balaa daddabalee uummata irratti kan fidaa jiru Abiyyi. Kan itti gaafatamus Abiyyi. Uummanni baldhaan ogeessota fayyaa waliin jira.

የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ፍትሀዊ ጥየቄ ነው። የዚህ ሁሉ መከራ ባለቤትና ተጠያቂ አብይ አህመድ ነው።
Milkessa Gemechu

19/05/2025

ከ80 በላይ ዶክተሮች እስር ቤት ታጉረዋል ።ማሰር መፍቴ አይሆንም።
17/05/2025

ከ80 በላይ ዶክተሮች እስር ቤት ታጉረዋል ።
ማሰር መፍቴ አይሆንም።

ገብያው ይባላል የላብራቶሪ ባለሙያ ነው በቡሬ ሆስፒታል ለምን facebook የጤና ባለሙያወችን የተቋውሞ ፎቶ ትለቃለህ ተብሎ በስራአስኪያጁ ጥቆማ ታስሯል እንዲለቀቀ ድምፅ እንሁነው
13/05/2025

ገብያው ይባላል የላብራቶሪ ባለሙያ ነው በቡሬ ሆስፒታል ለምን facebook የጤና ባለሙያወችን የተቋውሞ ፎቶ ትለቃለህ ተብሎ በስራአስኪያጁ ጥቆማ ታስሯል እንዲለቀቀ ድምፅ እንሁነው

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ምን አለ ?“ አሁንም አረፈደም፤ እልህ በመጋባት የጸጥታ ኃይል በማሰማራት የጤና ባለሙያዎችን ማፈኑ ቁሞ፤ በተገቢ ጥያቄዎች ምላሽ ትኩረት ይደረግ ” - ማኀ...
13/05/2025

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ምን አለ ?

“ አሁንም አረፈደም፤ እልህ በመጋባት የጸጥታ ኃይል በማሰማራት የጤና ባለሙያዎችን ማፈኑ ቁሞ፤ በተገቢ ጥያቄዎች ምላሽ ትኩረት ይደረግ ” - ማኀበሩ

የጤና ባለሙያዎች ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘታቸው በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች የጸጥታ አካላት የሚፈጽሙት እስራትና አፈና ሊቆም ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር በአጽንኦት አሳሰበ።

የዛሬው የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም እንቅስቃሴ በተመለከተም፣ ባለሙያዎቹ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ሥራ የማቆም አድማ እያደረጉ መሆኑን ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?

“ ሙሉ ለሙሉ ሥራ አላቆሙም፤ ባለሙያዎች የወጡት ከማህበረሰቡ ስለሆነ የድንገተኛ ክፍሎችን አልዘጉም በደረሰን መረጃ መሠረት። ይህም መሠረታዊ ጥያቄ ስላላቸው እንጂ ማኀበረሰብን ለማገልገል ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው ማሳያ ነው።

የባለሙያዎቹ ችግራቸው ሙሉ የሥራ ማቆም ውስጥ የሚያስገባ ነው።

እኛ ያሳሰብነው ጥያቄያቸውን መንግስት እንዲፈታላቸውና ባለሙያዎቹም ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ነበር፤ ግን አልሆነም እየቆጠሩ የነበሩት ቀን ዛሬ አልቆ፣ የተለያዩ ቦታዎች በከፊል ሥራ ማቆም ጀምረዋል።

በጥቁር አንበሳ፣ በአማራ ክልል ባሉ ሆስፒታሎች፣ በኦሮሚያ ክልል ባሉ ሆስፒታሎች፣ ደቡብ ባሉ ሆስፒታሎች በከፊል ሥራ እንዳቆሙ ነው ያለን መረጃ።

እንዲያውም ጎርደር ዩኒቨርሲቲ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ የጀመሩ ባለሙያዎችን ‘ባልታወቀ ምክንያት ከሥራ ቦታቸው ቀርተዋል’ የሚል ደብዳቤ እንደለጠፈ፣ ‘ወደ ስራ ቦታችሁ ካልገባችሁ እርምጃ እንወስዳለን’ እንደሏቸው ሰምተናል።

ጉዳዩ የማይታወቅ አይደለም፤ አገር አቀፍ ጉዳይ ነው።

የጻፈው አካልም ምን አይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር ያውቀዋል። ያው እንደዚህ አይነት አፃፃፍ የተለመደ ነው በኛ አገር። እነዚህም አመራሮች አመራር ከመሆናቸው በፊት ጤና ባለሙያ ነበሩ።

በትንሹ በጎረቤት ካሉ አገሮች እንኳ ተወዳዳሪ የምንሆንበት የጤና ስርዓት እንዲኖረን የጤና ባለሙያውን ያላቀፈ ከመሆን ቢከላከሉት ጥሩ ነው።

የጤና ባለሙያዎች የጠየቁት የዳቦ ጥያቄ ነው፤ በአንድ ቀን መግለጫ የሚቆምም አይደለም፤ ያን ጥያቄ ለመመለስ ከባለሙያዎች ጋር ተወያይቶ ተጨባጭ ምላሽ መሰጠት እንዳለበት ነው ማኀበሩ የሚያምነው።

አሁንም አልረፈደም፤ ጤና ባለሙያዎች ጋር እልህ በመጋባት የጸጥታ ኃይል በማሰማራት የጤና ባለሙያዎችን ማፈኑ ቁሞ፤ ተገቢ ጥያቄዎች ምላሽ ትኩረት ይደርግ።

የጸጥታ ኃይሉም ሲጎዳ የጤና ባለሙያው ጋር ነው ሂዶ የሚታከመው።

የጸጥታ ኃይል የህክምና አገልግሎት የሚሰጠውን ጤና ባለሙያ ይጎዳል ብለን አናስብም፤ ምናልባት ካድሬዎች ሊልኩት ይችላሉ። የጸጥታ ባለሙያው ከጤና ባለሙያው ጋር ተከባብሮ ሰላማዊ ነገር ቢደረግ ጥሩ ነው።

በጤና ባለሙያዎች ላይ በተለያዩ ጤና ተቋማት፣ ሆስፒታሎች እስራቶች፣ አፈናዎች፣ ሥም የማጥፋት ድርጊት እየተሰሩ ነው።

ሆኖም የጤና ባሙያዎች ጥያቄዎቻቸውን አስቀጥለዋል፤ በጥያቄያቸው ምላሽ አለማግኘት መሠረትም ከፊል የሥራ ማቆም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

አድማውን ያላደረገ ባለሙያ ሊኖር ይችላል፤ በተለያዬ ምክንያት ታፍኖ፣ በፍራቻ። አሁን ባለሙያዎች በጣም በችግር ውስጥ ነው ያሉት። ለመጠየቅ ራሱ ኢነርጂ ያስፈልጋቸዋል።

ያን ኢነርጂ አጥተው የተለያዩ ካድሬዎች አስፈራርተዋቸው ያልወጡ አሉ። ግን ታፍኖ የሚቀር ነገር የለም። መፍትሄው ምላሽና ምላሽ ብቻ ነው ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ




የሀኪሞች ድምጽ

13/05/2025

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዛሬ አገልግሎት እየሰጠ እንዳልነበር መረጃ

 #ዜናመሠረት በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ለነገ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻልበት ቀጠሮ ተጠርተዋል "በየትኛውም ሴክተር የሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ ተምሮ እንዳልተማረ በመሃይም ካድ...
13/05/2025

#ዜናመሠረት በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ለነገ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻልበት ቀጠሮ ተጠርተዋል

"በየትኛውም ሴክተር የሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ ተምሮ እንዳልተማረ በመሃይም ካድሬዎችና የቢሮ ኃላፊዎች መብቱ እየተረገጠ፤ እንዳይረጋጋ በመንግስት የታቀደ ኢኮኖሚያዊ ጫና እየደረሰበት ይገኛል። የሰሞኑ የጤና ባለሙያዎችም ጥያቄ የሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ጥያቄ ነው፤ ከእንግዲህ መሃይም ሹመኞች እራት እንዲበሉ ሻማ ይዘን የምንቆምበት ወቅት አልፏል"- መምህራን

(መሠረት ሚድያ)- ከሰሞኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ባለሙያዎች የመብት እና የዳቦ ጥያቄ በማንሳት በመላው ኢትዮጵያ በቅርብ አመታት ታይቶ የማይታወቅ የተናበበ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እ.....

 #ዜናመሠረት አምነስቲ ኢንተናሽናል የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ (መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮናታን ዳኘው...
13/05/2025

#ዜናመሠረት አምነስቲ ኢንተናሽናል የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ

(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮናታን ዳኘው ከእስር እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ማምሻውን ጠየቀ።

(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮናታን ዳኘው ከእስር እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ማምሻውን ጠየቀ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sololo News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share