
19/02/2025
ትርታ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚያስተዳድረው ትርታ 97.6 FM ሬድዮ ጣቢያ ባለድርሻዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በንግግር ለመፍታት ተስማሙ።
ታህሳስ 2016 ዓ.ም. የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የትርታ 97.6 FM ጣቢያ ባለድርሻዎች ባለፉት ሁለት ወራት ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሰፊ ውይይቶችን በማደረግ የነበሩ ችግሮችን መፍታት የቻሉ ሲሆን፣ በቀጣይም ጣብያውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ጠንከር ያለ ስራ ለመስራት ወስነዋል።
በመጨረሻም ባለድርሻዎቹ በችግሩ ወቅት ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል ።
የትርታ 97.6 ኤፍኤም ታህሳስ 13/2015 ዓም መደበኛ ስርጭቱን መጀመሩ ይታወሳል።
የትርታ 97.6 FM