Ethio promotion

Ethio promotion Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio promotion, Media/News Company, Addis Ababa.

የፅናት ተምሳሌት!!
30/06/2025

የፅናት ተምሳሌት!!

ክልላችን የሰላም ተምሳሌት ሆናለች።
30/06/2025

ክልላችን የሰላም ተምሳሌት ሆናለች።

ኢራን አደገኛ የተባለውን  በናኢቭ በረሃ የሚገኘውን   የእስራኤል ዲሞና  ኒውክሌር ማብላያ  ጣብያን  ለመምታት ውሳኔ  አሳለፈች ።  ዲሞና  የኒውክሌር ሪአክተር ጣቢያ እስራኤል  ከ1967G...
22/06/2025

ኢራን አደገኛ የተባለውን በናኢቭ በረሃ የሚገኘውን የእስራኤል ዲሞና ኒውክሌር ማብላያ ጣብያን ለመምታት ውሳኔ አሳለፈች ። ዲሞና የኒውክሌር ሪአክተር ጣቢያ እስራኤል ከ1967G.C ጀምሮ ያዘጋጀቻቸው እስከ 400 የሚጠጉ የኒውክሌር ቦምቦች አሉት ተብሎ የሚታመን ሲሆን ፤ የኢራን ውሳኔ እጅግ እጅግ በጣም አደገኛና ምናልባትም እነዚህ ቦምቦች አልያም ርዝራዥ እንኳን በጣቢያው ቢኖር የማይቀለበስ አደገኛ መዘዝ ምድራችን ላይ ይዞ ሊመጣ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

የገባው 1 ሰው ካለ አሜን ነው ወይ 😂😂?😭😭😭😭የልጁ አባት ማኖ 🙄?!😭😭😭
22/06/2025

የገባው 1 ሰው ካለ አሜን ነው ወይ 😂😂?
😭😭😭😭

የልጁ አባት ማኖ 🙄?!😭😭😭

ከ150 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው የአንድ ግለሰብ ንብረት በመብረቅ አደጋ ጉዳት መድረሱ ተገለጸሰኔ 15/2017 ዓ.ምከ150 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው የአንድ ግለሰብ ንብረት በመብረቅ ወ...
22/06/2025

ከ150 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው የአንድ ግለሰብ ንብረት በመብረቅ አደጋ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ

ሰኔ 15/2017 ዓ.ምከ150 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው የአንድ ግለሰብ ንብረት በመብረቅ ወደመ።

ጉዳት የደረሰው በኣሪ ዞን በገሊላ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ሻማ ቡልቀት ተብሎ በምጠራ ቀበሌ መንደር ስሆን በደረሰው የመብረቅ አደጋ ከ150 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች መውደሙን የከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታውቋል።

ቀን ሰኔ 14/2017 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ ከቀኑ ማታ 7:00 ሰዓት ገደማ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ነው የመብረቅ አደጋው የተከሰተው።

⚠️⚠️⚠️እጅግ አደገኛ ዕቅድ!! የኢራን ፓርላማ በአለም ላይ በጣም ወሳኝ ከሆኑ የነዳጅና ጋዝ መተላለፊያዎች ተጠቃሹን ‘ ሆርሙዝ ባህር ‘ ለመዝጋት ያቀረበውን ረቂቅ ፀደቀ   ይህ የኢራን እ...
22/06/2025

⚠️⚠️⚠️እጅግ አደገኛ ዕቅድ!!

የኢራን ፓርላማ በአለም ላይ በጣም ወሳኝ ከሆኑ የነዳጅና ጋዝ መተላለፊያዎች ተጠቃሹን ‘ ሆርሙዝ ባህር ‘ ለመዝጋት ያቀረበውን ረቂቅ ፀደቀ

ይህ የኢራን እርምጃ ወደ ተግባር ለመግባት ከኢራን ከፍተኛ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የመጨረሻውን ይሁንታ እየጠበቀ ነው ።

ውሳኔው ተተግብሮ ሆርሙዝ ቢዘጋ አለም አቀፍ የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ላይ አስከፊ መዘዞች የሚያስከትል ሲሆን - ይህ የ Hormuz መተላለፊያ 21 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ዘይት እና አንድ ሦስተኛው የዓለማችን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ በእያንዳንዷ ቀን የሚጓጓዝበት ነው።

21/06/2025
ቻይና እያስፈራራች ነው። ከብርሃን ድምፅ ፍጥነት በ4 እጥፍ (mach 4) የሚበልጥ ጀት   | በ Space transportation የተመረተው ይህ ዩንዢንግ ፕሮቶታይፕ ሱፐርሶኒክ ጀት ከብርሃ...
19/06/2025

ቻይና እያስፈራራች ነው።

ከብርሃን ድምፅ ፍጥነት በ4 እጥፍ (mach 4) የሚበልጥ ጀት

| በ Space transportation የተመረተው ይህ ዩንዢንግ ፕሮቶታይፕ ሱፐርሶኒክ ጀት ከብርሃን ድምፅ ፍጥነት በ4 እጥፍ የበለጠ መሆኑን ተነግሯል።

አዲሱ የተሳፋሪዎች ጀት ከለንደን ወደ ኒውዮርክ ከተማ ለመድረስ 90 ደቂቃ ይወስድበታል። እንዲሁም ከቤጂንግ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ለመድረስ ሁለት ሰዓት ይፈጅበታል። ይህ ጀት በሰዓት 4,924 ኪ.ሜትር መጓዝ ይችላል።

እንዲህ ካለ መጋለጥ ይጠብቀን??? 😂😂😂😂😂😂😂😂" እናቴ ' ልጅሽ ሞቷል ' ተብላ እያለቀሰች ነበር ፤ ነገር ግን ቤተ ዘመድ ለቅሶ ከመቀመጡ በፊት እናቴንና ቤተሰቦቼን አረጋግቻለሁ " - አብ...
10/06/2025

እንዲህ ካለ መጋለጥ ይጠብቀን???
😂😂😂😂😂😂😂😂
" እናቴ ' ልጅሽ ሞቷል ' ተብላ እያለቀሰች ነበር ፤ ነገር ግን ቤተ ዘመድ ለቅሶ ከመቀመጡ በፊት እናቴንና ቤተሰቦቼን አረጋግቻለሁ " - አብዮት ጩሎ

➡️ " ' ሞቷል ' እየተባለ ፎቶዬ በተሰራጨበት ማግስት የ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ ፅሑፌን አቅርቤ መመረቄን አረጋግጫለሁ ! "

| ትላንት የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድን ከሲዳማ ቡና አቻው ጋር የነበረው የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያለ ደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲደረግ ከመወሰኑ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች " በፀጥታ ሃይሎች ደጋፊዎች (የወላይታ ዲቻ) ተገደሉ " እየተባለ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ነገር ግን ክለቡ መረጃዎቹ ውሸት መሆናቸውንና " አንድም ደጋፊ አለመሞቱን " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ባደረገዉ ተጨማሪ ማጣራት በርካቶች በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተቀባበሉትና " ሞተ/ተገደለ " የተባለው ወጣት ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑንና ወጣቱ በሕይወት መኖሩን ከራሱ አንደበት አረጋግጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከላይ በፎቶው የሚታየውንና " ተገደለ / ሞተ " ተብሎ በስፋት በማህበራዊ ሚዲያ የተወራበትን ወጣት አብዮት ጩሎ አገኝቶ አነጋግሯል።

" የወላይታ ዲቻ ቀንደኛ ደጋፊ ብሆንም በጨዋታው ዕለት ማግስት የ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ ፅሑፌን የማቀርበብት ዕለት ስለነበር ወደ አዲስ አበባ አልሄድኩም " ያለው አብዮት " ነገር ግን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያዎች ፎቶዬ እየተሰራጨ 'በፀጥታ ሃይሎች ተገድሏል' የሚል መረጃ ደጋግሜ ስመለከት በጣም ነበር የደነገጥኩት " ብሏል።

በወላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ ማለያ የተነሳውና ብዙ የማህበራዊ ሚዲያዎች ያሰራጩት ፎቶ የራሱ ቢሆንም ፎቶውን ግን የተነሳው ትላንት እንዳልነበር አረጋግጧል።

" አሁን ላይ እኔም ተረጋግቻለሁ " የሚለዉ ወጣት አብዮት " በወቅቱ ወደ እናቴ ስደውል ' ሞቷል ' ተብላ እያለቀሰች ነበር ፤ ነገር ግን ቤተ ዘመድ ለቅሶ ከመቀመጡ በፊት እናቴንና ቤተሰቦቼን አረጋግቻለሁ " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

" እኔ ' ሞቷል ' እየተባለ ፎቶዬ በተሰራጨበት ማግስት የ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ ፅሑፌን ያቀረብኩበትና መመረቄን ያረጋገጥኩበት ነበር ፤ ፈታኞቼና አማካሪዎቼ በተረጋጋ መንፈስ ጥናታዊ ፅሑፌን እንዳቀርብ አግዘዉኛል " ሲል አክሏል።

#ጌጡ ተመስጌን

. ........ ፖራ ወላይቶ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭🙄🙄🙄🙄😭😭😭😭😭የወላይታ ዞን አንዳንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች በ12 ሚሊዮን ብር የታክስ ስወራ ቅሌት ከሀብታሞች ጋር በመመሳጠር ተከሰሱ።በወላይታ ዞን...
04/06/2025

. ........ ፖራ ወላይቶ
😭😭😭😭😭😭😭😭😭
🙄🙄🙄🙄😭😭😭😭😭
የወላይታ ዞን አንዳንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች በ12 ሚሊዮን ብር የታክስ ስወራ ቅሌት ከሀብታሞች ጋር በመመሳጠር ተከሰሱ።

በወላይታ ዞን በርካታ የአካባቢ የመንግስት ባለስልጣናት ከሀብታሞች ጋር በመመሳጠር ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ከቀረጥ ለማምለጥ መሞከራቸው ከታወቀ በኋላ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ቅሌት እየተፈጠረ መሆኑን ገቢዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ አመልክቷል።

ለምርመራው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳረጋገጡት የወላይታ አንዳንድ አመራር አካላት ተደማጭነት ካላቸው የንግድ ባለቤቶች ጋር በመቀናጀት የፋይናንሺያል መረጃዎችን በማጭበርበር፣ የንግድ ገቢን ለመደበቅ እና መደበኛ የታክስ ኦዲት እንዳይደረግ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል።

“የታክስ ግዴታዎች ሆን ተብሎ በተጭበረበሩ ሰነዶች እና በህገወጥ ስምምነቶች የተዘገበ ስለመሆኑ አስተማማኝ ማስረጃ አግኝተናል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የገቢ ከፍተኛ ባለሙያ ተናግረዋል። "ይህ የገንዘብ ህግ መጣስ ብቻ ሳይሆን የህዝብ አመኔታ ክህደት ነው።" ብለዋል።

የተጠረጠረው እቅድ የግንባታ ተቋራጮች፣ የሆቴል ባለቤቶች እና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አስመጪና ላኪ ድርጅቶችን ያካተተ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች አመራር አካላት ግምገማዎችን ለመቀየር እና የማስፈጸሚያ እርምጃዎችን ለማዘግየት ጉቦ እንደሚቀበሉ ተነግሯል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አመራሮች ማንነት በይፋ ባይገለጽም፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና ተቃዋሚዎች ግልጽነትና ፈጣን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ መጠየቅ ጀምረዋል።

ሰሙ እንዳይጠቀስ የሚፈልግ መረጃ ሰጪ "ይህ የሚያሳየው በሕዝብ ተቋሞቻችን ላይ ሙስና ምን ያህል ሥር የሰደደ መሆኑን ነው" ብለዋል። "ለሆስፒታል፣ ለትምህርት ቤት እና ለመንገድ መሄድ የነበረባቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በግል ኪስ ውስጥ ገብቷል።"

የህግ ባለሙያዎች ቅሌቱ ሙስና፣ ማጭበርበር፣ የታክስ ህግን ማደናቀፍ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን አላግባብ መጠቀምን ጨምሮ ክስ ሊመሰርት እንደሚችልና ይህም በኢትዮጵያ በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ህግ መሰረት ከባድ እስራት እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ጉዳዩ በቀጣዮቹ ቀናት ለፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለተጨማሪ ምርመራ እና ክስ ሊቀርብ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

እግዚአብሔር አዋቂ ነው።ሁላችንም የምንሄዴው ወደዚያ ነው። 😭😭😭😭😭😭
02/06/2025

እግዚአብሔር አዋቂ ነው።
ሁላችንም የምንሄዴው ወደዚያ ነው።
😭😭😭😭😭😭

ለምን ለምን ለምን ይሆን እግዚአብሔር አ/ምንጭን ብቻ እንዲህ ያሳመራት???!?
31/05/2025

ለምን ለምን ለምን ይሆን እግዚአብሔር
አ/ምንጭን ብቻ እንዲህ ያሳመራት???!?

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911853624

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio promotion:

Share