28/09/2026
የአሸባሪው "ህወሐት" ቡድን ጋራ የወላይታ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ አክትቪስቶችና አንዳንድ የወላይታ መጋቢ የመንግስት አመራሮች የፈጠሩት ግንኙነት ለቀጣይ ደቡብ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ስጋት እንደሚሆኑ ተጠቆመ
ለፖሊቲካ ውንጀላ እያሉ እና ከኋላቀር ፖሊቲካ አስተሳሰብ ነጻ መውጣት ያቃታቸው እንድሁ ከአሸባሪው "ህወሐት" ቡድን ጋራ ትስስር ያላቸው የወላይታ አክትቪስቶችና አንዳንድ የወላይታ መጋቢ አመራሮች ጨምሮ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ለህዝባቸው ጭቆና ምክኒያት እየሆኑ ነው! ወደኋላ መሰልጠን ማለት ይሄንን ነው
1ኛ.ለኛ ሌላ አድስ ሆስፒታል ይሰራልን እያሉ ኦቶና ሆስፒታልን አቃጠሉ፣ ሌላ የገቢያ ማዕከል ይገንባልን እያሉ ሶዶ መርካቶ ገቢያን በገዛ እጃቸው አቃጠሉ፣ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ይገንባልን በማለት ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስ ላይብሬሪ አቃጠሉ፣ በገዛ እጃቸው ስብሰባ አዳራሻቸውን በጠራራ ጸሀይ አጋይተዋል።
2ኛ. የ"ዳውሮ ዲንካን" "የኔ ነው" ይላሉ፤ እንድሁም አለም የሚያውቀው የጋሞ ህዝብ አዕምሮ ሀብት የሆነውን "ዱንጉዛ" በኛ ስም በ"UNESCO" ካላስመዘገብን ይላሉ! እየበጠበጡ በወላይታ አክትቭስቶች ምክኒያት ንጹህ ወላይታወች ከሀዲያ፣ ከሃላባና ከሀዋሳ ተረግጠው ሀብትንብረታቸውን ጥለው ተባረዋል። ዋናው ዓላማው የቀጠናውን ፖለቲካ ውጥረት ውስጥ መክተት ነው
3ኛ. አመራር ከሌላ ብሔር ለምን ይሆናል በማለት የመንግስት አስተዳደራዊ ህገደንብን እና የአመራር አደረጃጀት ምዘናን በጣሰ መንገድ እንደፈለጉ የመንግስት አመራርን ይዘልፋሉ፣ ያሰራሉ! አልተሳካላቸውም እንጂ በክልሉ ሰላም እንዳይኖር ቀንና ማታ ይሰራሉ!
ነጌ ደግሞ ሶዶ ከተማ እንደዝህ ለምን አማረባት በማለት የገዛ ከተማቸውን ማፍረስ እንዳይጀምሩ ፈራን!