Afri View

Afri View Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Afri View, Digital creator, Addis Ababa.

ሁለት ልብ እንዳያመልጣችሁ ምርጥ ድራማ
05/09/2025

ሁለት ልብ እንዳያመልጣችሁ ምርጥ ድራማ

ሁለት ልብ ክፍል 8 Hulet Lib Episode 8 Kana tv

ኮሜዲ
02/09/2025

ኮሜዲ

ኮሜዲያን ማርቆስ ቁራሌው - Comedian Markos Ethiopia comedy

አዲስ ተከታታይ የኮርያ ድራማ እንዳያመልጣችሁ
01/09/2025

አዲስ ተከታታይ የኮርያ ድራማ እንዳያመልጣችሁ

ሁለት ልብ ክፍል 1 Hulet Lib Episode 1 Kana tv

አዲስ ተከታታይ የኮርያ ድራማ እንዳያመልጣችሁ
01/09/2025

አዲስ ተከታታይ የኮርያ ድራማ እንዳያመልጣችሁ

ጓደኛሞቹ ክፍል 1 - guadegamochu episode 1

ተዋናይ ቸርነት በሰይፉ ሾው ላይ ባደረገው ቆይታ ፦★ እስከዛሬ ድረስ ከሰራኋቸው ፊልሞች ቀንጃን የተለየ     ቦታ አስቀምጠዋለሁ።★ መስከረም አበራ ለፊልሙ ፀጉሯን ተቆርጣለች።★ መስከረም ና...
01/09/2025

ተዋናይ ቸርነት በሰይፉ ሾው ላይ ባደረገው ቆይታ ፦

★ እስከዛሬ ድረስ ከሰራኋቸው ፊልሞች ቀንጃን የተለየ
ቦታ አስቀምጠዋለሁ።

★ መስከረም አበራ ለፊልሙ ፀጉሯን ተቆርጣለች።

★ መስከረም ናት የስራውን ፓሽን ያመጣችው።

★ ደመና የሚባለው በሬ በጣም ቆንጆ አድርጎ ነው
የተወነው። እንደበሬ አልነበረም።

★ በሬው ተንከባሎ ወድቆ እሱን ለማዳን ከተራራ ላይ
ወድቄ እግሬን ተሰብሬ ነበር።

★ እዚህ መጥቼ እግሬ 3 ወር ታሽጓል። እዛ ግን
ፊልሙ ላይ ጨክኜ ነው የሰራሁት።

★ ፊልሙ ላይ በሬው በመ*ታረዱ ሰው ቅር ብሎት ነበር።
33 ቀን ከኛ ጋር የነበረን በሬ ማረድ ከባድ ነው።
ሌላ ተመሳሳይ ነጭ በሬ መጥቶ ታ*ረደ።
ደመና አሁን ወልዷል። ጎንደር ነው ያለው።
ምርቃቱ ላይ ይገኛል ብለን አስበን ነበር።

★ ከተማው ናፍቆን ነበር። ቤተሰቦቻችን እዚህ ተጨንቀው
ነበር።

★ የጥይት ድምፅ እየሰማን ነበር ፊልሙን የሰራነው።

★ አንድ ጫካ ላይ አንድ ሲን እየቀረፅን የእውነት ጥይት
ተተኩሶብናል።

★ ሰው ፍቅር ሊሰጠን ሲመጣ እኛ ቢዚ ነበርን።

★ የጎንደር አዘዞ ነዋሪዎችን በዚህ አጋጣሚ እናመሰግናለን።

★ የፊልሙን ቀረፃ አጠናቅቄ አዲስ አበባ ስገባ
እናቴ ፌንት ነቀለች።

★ ፊልሙን ሰርተን ከጨረስነው አንድ ዓመት ከዘጠኝ
ወር ሆኖታል።

★ የምርቃቱ ዕለት የፊልሙን ክሩ አባላት ፊት ለፊቴ ሳያቸው
ያሳለፍነውን መስዋዕትነት ሳይ ደስ አለኝ።
ዕንባዬም መጣ።

★ እድገትና ውልደቴ መርካቶ ( ኳስ ሜዳ ) ነው።

★ የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር አየልኝ ፀጋዬ ይባላል።
ጎበዝ ልጅ ነው።

★ ሰለሞን የመጀመሪያ ፊልሙ ነው። ጥሩ አድርጎ
ተውኖታል።

ተዋናይ ቸርነት ፍቃዱ ፦ ለኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ
እድገት እየደከምክ ላለኸው በጎ ስራ ምስጋና ይገባሃል።
አድናቂህ አክባሪህ ነኝ።

ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

መኮንን ላዕከ ተሞሸረአርቲስት መኮንን ላዕከ የ57ኛ ዓመት ልደቱ በልዩ ዝግጅት ተከበረ። የመኮንን የአመታት ህልምና ፍላጎትም ተፈጽሞ ዳግም ከ ካለቤቱ ተሞሸረ። አራት ልጆቹም አጃቢና ሚዜዎቹ ...
29/08/2025

መኮንን ላዕከ ተሞሸረ

አርቲስት መኮንን ላዕከ የ57ኛ ዓመት ልደቱ በልዩ ዝግጅት ተከበረ። የመኮንን የአመታት ህልምና ፍላጎትም ተፈጽሞ ዳግም ከ ካለቤቱ ተሞሸረ። አራት ልጆቹም አጃቢና ሚዜዎቹ ሆኑ።

ነገሩ እንዲህ ነው!!!

አርቲስት መኮንን ላዕከ በህይወቱ ውስጥ ከሚቆጩት ነገሮች አንዱ ባለቤቱን ወይዘሮ ሰላማዊትን በቬሎ አለማግባቱ ነው። ይህ ቁጭት የመኮንን ብቻም ሳይሆን የባለቤቱም ጭምር መሆኑን የቅርብ ሰዎች ይመሰክራሉ። እናም ይህንን ምኞት ለማሳካት እና መኮንን ላዕከን ለማስደሰት ያለመ ኮሚቴ በራስ ተነሳሽነት ተቋቋመ። ኮሚቴው ስለ ዝግጅቱ፣ ስለዝግጅቱ ማከናወኛ ስፍራ፣ ስለዝግጅቱ ይዘት፣ ስለሚጠሩ እንግዶች፣ ስለ ዝግጅቱ ምስጢራዊነት፣ መኮንን ላዕከ በዕለቱ ሊደረግለት ስለሚገቡ ድንገቴ ስጦታዎች...... ወዘተ ለአንድ ወር መከረ ለፋ። በመጨረሻም ትናንት ልፋቱ እውን ሆነ። ስለ ልደቱም ሆነ ስለ ዳግም መሞሸሩ መኮንን እና ባለቤቱ እንዳያውቁ ከባድ ምስጢርን የመጠበቅ ስራ ተከናወነ። መኮንንም ባለቤቱም ባልጠበቁት ዕለት ልደትና ሰርጋቸውን አደረጉ።

መቼም ምሽቱ ልዩ ነበር። መኮንና ባለቤቱ የነበራቸው መደንገጥና ያለማመን ሁሉም እንግዶች ላይ ተጋብቷል። ህልሙን እውን እናድርግ ብሎ የቆረጠው ኮሚቴም በአንድ ወር ቆይታው ብዙ ስለለፋ ሁሉም ተሳካ። በድንገቴ ላይ ድንገቴው ቀጠለ። ለመኮንን መኪና ማግኘት ህልሙ የነበረው ኮሚቴ ህልሙ ተሳክቶ መኮንን የመኪና ባለቤት መሆን የሚችልበትን ዕድል ፈጠረ። በዲጄ ቤቢ (አዲስ ሚዩዚክ) ትልቅ ጥረት ታግዞ ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ደግሞ መኪና ለመስጠት ቃል ገባ። ትናንት ምሽት በዝምታ ሬስቶራንትና ላውንጅ የዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዶኒክ ወርቁ እና የድርጅቱ አምባሳደር አርቲስት እንግዳሰው ሀብቴ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመኪናው ስጦታ እውንነትን አረጋገጡ።

ቴምር ሪል ስቴት 300,000 ብር ለመኮንን ልደት ስጦታ ላከ። የማስታወቂያ ባለሙያው እና የረዥም ዓመታት ወዳጁ ዘላለም ኩራባቸው የ1 ሚሊዮን ብር ስጦታ ላከ። ጎልደን ዲዛይን ምርጥ እና በልዩ ሁኔታ የተሰራ የሀገር ባህል ልብስ ለጥንዶቹ አበረከተ። የስዕል እና ሌሎች ስጦታዎችም ቀጠሉ።

አድዋ ባንድ የመኮንን ላዕከን ልደትና ዳግም ሰርግ አደመቀ። ስንግ ኬተሪንግ እንግዶቹን ጭምር ጋበዘ። Focus Studio ይህንን ውብ ዝግጅት ሰናጅ ሆነ። ድምጻዊት ሳሮን (ሚሶ ነገያ) ሜከአፑ ላይ ተጠበበችበት

ስሜትን ለመግለጥ የሚያስቸግረ ምሽት ሆነ። ላዕከ እና ባለቤቱ ኮሚቴውን በከፍተኛ መገረም ውስጥ ሆነው አመሰገኑ እንግዶች ፍቅራቸውን አፈሰሱት። ደስታቸውንም ተጋሩ።
ድንቅ ምሽት!!!!
የሰው ፍቅር ሞልቶ የፈሰሰበት ዝግጅት!!!!

ምርጥ የኮሚቴ ስብስብ። ምርጥ ትብብር። ምርጥ ርብርብ። የማይረሳ ዝግጅት ።

መኮንን ላዕከ በድጋሚ መልካም ልደት።
እንኳንም ህልምህን ኖርከው!!!!
Via: በፍቃዱ አባይ
ፎቶ
ሲሳይ ጉዛይ
Focus Studio

የፊታችን ሀሙስ ከ10:00 ጀምሮ ልዩ የመጽሐፍ ምረቃና የኪነጥበብ ድግስ!! በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል ሶስተኛው መጽሐፌ የተፈቱ ሰንሰለቶች እንዚህ ሁሉ ዕውቅና ድንቅ እንግዶች በተገኙበት በ...
27/08/2025

የፊታችን ሀሙስ ከ10:00 ጀምሮ ልዩ የመጽሐፍ ምረቃና የኪነጥበብ ድግስ!!

በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል ሶስተኛው መጽሐፌ የተፈቱ ሰንሰለቶች እንዚህ ሁሉ ዕውቅና ድንቅ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል:: መጥተው የደስታዬ ተካፋይ ይሁኑ:: አመሰግናለሁ!

የወንዶች ጉዳይ ~ መጡ በአዲስ ጉዳይ? አዎ! ...ከጥቂት ቀናት በኋላ ከእናንተ ጋር!
26/08/2025

የወንዶች ጉዳይ ~ መጡ በአዲስ ጉዳይ?
አዎ! ...
ከጥቂት ቀናት በኋላ ከእናንተ ጋር!

22/08/2025

ሁለት ልብ ክፍል 1 Hulet Lib Episode 1 New Movie - Hello ethiopia #ትርጉም | Melgna film | film wedaj

ዋንቲያ ሰለሞን በመቄዶንያ ዋንቲያ ሰለሞን በችግሬ ጊዜ አብሮኝ አልቅሶ ከጎኔ ነበር በማለት የመቃብር ስፍራው ድረስ በመሄድ የአበባ ጉንጉን ካስቀመጠች በኋላ በመቄዶኒያ በመገኘት ለአረጋዊያንን...
21/08/2025

ዋንቲያ ሰለሞን በመቄዶንያ

ዋንቲያ ሰለሞን በችግሬ ጊዜ አብሮኝ አልቅሶ ከጎኔ ነበር በማለት የመቃብር ስፍራው ድረስ በመሄድ የአበባ ጉንጉን ካስቀመጠች በኋላ በመቄዶኒያ በመገኘት ለአረጋዊያንን የምሳ ግብዣ አድርጋለች።

ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ መኪና ሊሸልም ነው። ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የ2025 ሽልማት ኖቬምበር 22/2025 (ህዳር 13/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድ ዛሬ በስ...
21/08/2025

ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ መኪና ሊሸልም ነው።
ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የ2025 ሽልማት ኖቬምበር 22/2025 (ህዳር 13/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።

የ2025 ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ G-Power creative award የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ሽልማቱ የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታ ከማበረታታት ባለፈ ሰላምን በዲጂታል መረብ የሚያስተዋውቁ ወጣቶችን የሚያበረታታ እንደሆነ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

ሽልማቱ የሚሰጥባቸው 26 ዘርፎች

📌 Tik Tok Creator of the Year
📌 Funniest Comedy Content (Male)
📌 Funniest Comedy Content (Female)
📌 Best Social Impact Content
📌 Best Health & Medical Informative Content
📌 Tik Tok for Business
📌 TikTok for Science & Technology (Best STEM Content Award)
📌 Creative Editing & Effects
📌 Best Dancer / Performer
📌 Best Musician or Producer
📌 Best Traveling Content
📌 Best Review Content
📌 Best Informative Content
📌 Best Emerging TikToker
📌 Best Sports & Fitness for Health Content
📌 Best Lifestyle Content
📌 Best Artist / Painter / Poet
📌 Best Motivational Content
📌 Best TikTok Chef
📌 Best Live Streamer
📌 Best Memer Award
📌 Best Dressed on the Day of the Event (Female)
📌 Best Dressed on the Day of the Event (Male)
📌 TikTok Short Movie Video of the Year
📌 Lifetime Award
📌 G-Power Award

የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር የመኪና ሽልማት እንደሚሸለም ተነግሯል። ለሽልማት በቂ የሚያደርገው መስፈርት ከ400ሺህ በላይ ተከታይ ያለው እና ከህዳር 2024 እስከ ህዳር 2025 ባለው አንድ አመት ውስጥ ከ24 ቪዲዮ በላይ የለቀቀ መሆን አለበት ተብሏል።

ሽልማቱ 70% የህዝብ ድምጽ ሲሆን 30% የአዘጋጅ ኮሚቴ እንደሚወሰን ተገልጿል።

''ማለፊያ'' ልዩ የመዝናኛ የራዲዮ ፕሮግራም በትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በቀጥታ ስርጭት!ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 15  ከቀኑ 9:00 - 11:00 መደመጥ ይጀምራል።
21/08/2025

''ማለፊያ'' ልዩ የመዝናኛ የራዲዮ ፕሮግራም በትርታ ኤፍ ኤም 97.6 በቀጥታ ስርጭት!

ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 15 ከቀኑ 9:00 - 11:00 መደመጥ ይጀምራል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afri View posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share