07/06/2026
▫️የሰው ክፉ አለ !
አንተ ከራስህ ቀንሰህ ጥሩ ነገር ስታደርግለት እሱ ግን በአንተ ላይ ክፉ የሚመኝ ፤ ልታግዘው ስትፈልግ አንተን ጥሎህ ለመሄድ የሚሞክር ፤ በከፍታው ስትደግፈው መውደቂያህን የሚያመቻችልህ ክፉ ሰው አለ።
በዚህ ሰዓት አንተ የሰውን በጎ ጎን ብቻ ለመመልከት ስትሞክር፣ እናትህ ግን ከጀርባው ያለውን ተንኮል ታያለች። እሷ መጥፎ ነገርን የምታሳይህ ህይወትን ስለምታውቃትና ካንተ በላይ ሰውን ስላጠናች እንጂ እንደአንተ ቀና ስላልሆነች አይደለም።
ለፍተህ ያገኘኸውን ጊዜህን እና ጉልበትህን ለማይገባው ሰው አትስጥ።
ከመጎዳትህ በፊት አስቀድመህ ተከላከል ፤ የእናትህን ምክር ስማ።
መልካም ቀን 🙏