06/07/2022
አስፈሪው ጭርታ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬●●▬▬▬▬▬▬▬▬▬
©Mujib Amino
ሰዎች የሚርመሰመሱባቸው አውራ ጎዳናዎች፣ ብዙዎች የሚበዙባቸው የንግድ ስፍራዎች፤ የግብይት ና የአገልግሎት ተቋማት ሕንጻዎች፣ ባንኮች፤ የመጓጓዣ ተራዎች፣...ወዘተረፈ በጭርታ ዝምታቸው ያስተጋባል።
ከተማው ኦና ሆኗል። ሕዝብ ቅሬታ ውስጥ ያለ ይመስላል። መንግስት እየፈጸመ ያለዉን አሰራርና ሕግጋት እንዲያስተካክል መጠቆሚያ አንዱ ማሳያም ይሆናል።
ዜጎችን ጠብቅ ተንከባከብ፣ የኑሮ ዉድነቱን አረጋጋ፣ ሕገ መንግስቱን አክብር አስከብር፤ አብሮነትና አንድነትን ስበክ፣ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አትጣስ፣ የፕሬስ ነጸነት ይረጋገጥ፤•••የሚሉ ሐሳቦችን እያዉጠነጠኑ ማህበረሰሰቡ ፣ ወጣቱና ፖለቲለኛዉ •••የተቃዉሙን ሐሳብ ከአደባባይ ይልቅ በየቤቱ ተቅምጡ በጭርታ ድምጹን ለማሰማት እየጣረ ነው።•••
ጭርታዉ••• ከነፍስ መገንቢያ፤ ከልብ ማጽጃና ማጎልበቻ፤ ከአካል ብርታት ፤ ከሞራል ከፍታ፤ ከስነ ምግባር ማስዋቢያ፤ ከኢማን ማዕድ፣ ከፍቅር ገበታ፣ ከፍቅር አክሊል፤ ከውዴታ ማሳ፣ ከክብር ምንጭ፣ ••• የጌታችን ቀጥተኛ ትእዛዝ በውዱ ነብይ የተላከልን ውዱን ስጦታ በጭርታ አመጽነው።
በአቅራቢያዬ የሚገኝ መስጂድ ለፈጅር ሶላት አመራሁ። በመስጂዱ ውስጥ እንደገባሁ፤ ኢማማችን ነቢያዊ ፈለግ ተከትሎ፣ ምዕመናኑ ረድፉን ያስተከክል ዘንድ ወደቀጭ ወደግራ እያየ «ኢስተዉ፣ ወተራሱ፣ ወሱዱል ኸለል ... ተስተካከሉ፣ ክፍተት ዝጉ፣ ...ተጠጋጉ፣ ተቀራረቡ•••»
ኢማማችን በምዕመናን ጭርታ መስጂዱ ኦና በመሆኑ ምን ያህል ይሰማዉ ይሆን? ምን ያህል ይሸማቀቅ ይሆን? በሰጋጆች የሚሞሉት ረድፎች በጭርታ ተተክተዉ መመልከት ምነኛ ያማል?... 1 ሶፍ መሙላት ተሳነን•••
ጭርታዉ••• ከዚህ ሁሉ ዉለታና እዝነት ቡኃላ አሏህ ላይ ቅሬታ ለማቅረብ ነው? ጭርታዉ••• የሰጠንን ሲሳይ ለማስተባበል ነው? ጭርታዉ•••አሏህን ለማመጽ የተሰናዳ ነው? ጭርታዉ•••የሸይጧን ምርኮኛነትን ለማወጅ ነው?ጭርታዉ••• ተዝቆ የማያልቀዉን ውለታውን ለማሳነስ ነው?፤ ጭርታዉ•••ሪዝቅ አነሰብን ነው?፣ ጭርታዉ•••ምቾት አሽቆለቆለብን ነው?፣ ጭርታዉ •••ሀብትና ንብረት ወደመብን ነው?፣ ጭርታዉ •••አሏህ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ነው? •••እ ? ? ?
ማሰብ የሚችል አእምሮ፣ መስማት የሚችል ጆሮ፣ መመልከት የሚችል ዓይን፣ መናገር የሚችል አንደበት፣ መንቀሳቀስ የሚችል እግር፣ መያዝና መጨበጥ፡ መስጠትና መለገስ የሚችል እጅ የሰጠን እሱ አይደለምን? (ሱረቱ-ነሕል 78)፡፡
“የአሏህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፤ አሏህ በእርግጥም መሐሪ አዛኝ ነውና።” (ሱረቱ-ነሕል 18)፡፡
በዚህ አንቀጽ ብቻ እንኳ እኛ የጌታችን አሏህ የውለታው ባለ-ዕዳዎች መሆናችንን መረዳት ይቻላል፡፡ አሏህ ለውለታው ክፍያን ቢጠይቀን ኖሮ ምን ይሆን መልሳችን? ለዚህ ውለታ የተጠየቅነው ክፍያ “ምስጋና” ብቻ ነው፡፡
ደግሞም የምናመሰግነውም በጸጋ ላይ ሌላ ጸጋ ሊጨመርልን እንጂ ጌታችን የምስጋና እጥረት ኖሮበት አይደለም፡-
“ጌታችሁም፦ ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋላሁ)፤ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)።” (ሱረቱ ኢብራሂም 7)፡፡
አላህን ከማመን ብናፈገፍግ እራሳችንን እንጎዳለን እንጂ እሱን አንጎዳውም፡፡ እሱ ከፈለገ የሚወዳቸውንና የሚወዱትን መልካም ባሮች መፍጠር ይችላል።