
23/07/2025
ጋዛዎች በረሀብ እያለ*ቁ ነው
እነዚህ ፎቶዎች እ.ኤ.አ. በ1940ዎቹ ከተከሰተው የአፍሪካ ረሃብ ወይንም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መዛግብት የተወሰዱ አይደሉም።ይልቁንም ከዛሬዋ ጋዛ በዚህ ወቅት የተነሱ ምስሎች ናቸው
ህፃናት አይናችን እያየ ያለ መድሀኒት፣ ያለ ምግብ ፣ይህን ሲዖል ለማስቆም ምንም አይነት ድምፅ ሳይሰማ በረሀብ እየተበሉ ነው::
የንፁሀን አፅሞች የራሳቸውን ሞት ከማስታወቃቸው በፊት የሰው ልጆች ህሊና መሞቱን ቀድመው እያስታወቁ ናቸው::
እንዚህ አሰቃቂ ምስሎች በተባበሩት መንግስስታት መግቢያ በሮች ላይ ሊሰቀሉ፣ በየትኛውም የሰብዓዊ መብቶች ፎረም ላይ ሊታዩ፣ እኩልነትን፣ ገለልተኝነትን እና ደብል ስታንዳርድ ለሚሰብኩ ሁሉ ፊታቸው ላይ ያዩት ዘንድ ሊወረወር ይገባል::
እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ."
ከዚህ በላይ ምን አይነት ጅምላ ፍ*ጅ*ት ይሆን ወንጀል ሊሰኝ የሚችለው?
ምን አይነት ምክንያታዊነት ይሆን ይህን በአይን ካዩ ቡኃላ ሊቀርብ የሚችለው?
ዝምታም ከዚህ ወንጀል ጋር መተባበር ነው!
መዘግየትም ወንጀል ነው!
ጋዛ እየተጣራች ነው.....
የሁላችንንም ምላሽ ትሻለች
እያንዳንዳችን አላህ ፊት ከመጠይቅ አንድንም:: የአዛኙ ነብይ ኡመት እዝነት ጠፍቶበታል:: ምንም ማድረግ ባይቻል እንኳን አላህ እንዲረዳቸው በዱዓ እናስታውሳቸው:: ለወንድሞቻችን ሁላችንም ማድረግ የምንችለው ቀላሉ ነገር ዱዓ ነው:: ልጆቻችንን ፣ እራሳችንን በነሱ ቦታ አድርገን በማየት ህመማቸውን እንታመም:: ፈረጃው ቅርብ እንዲሆንላቸው ወደ አላህ እጃችንን አንስተን እንማፀን::