Orthodox Media

Orthodox Media Dhugaan Dhugaadha sobaan hin madaalamu. Namni Afaan dhaloota isaatin haa baratuun Galma keenya, Sirna uumamaan hunda jabeeffanna.

👉   የቅጥር ማስታወቂያ   👉 የሰሜን ጎጃም ሀገረስብከት በሰሜን አቸፈር ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለይስማላ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ የቅኔ መምህር አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።👉ስለዚህ የመ...
30/07/2025

👉 የቅጥር ማስታወቂያ

👉 የሰሜን ጎጃም ሀገረስብከት በሰሜን አቸፈር ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለይስማላ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ የቅኔ መምህር አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

👉ስለዚህ የመመዝገቢያ መሥፈርቶች
1ኛ በቅኔ መምህርነት የተመረቀና ጉባኤ ዘርግቶ ከ1 ዓመት በላይ ያስተማረ።
2ኛ የክህነት ማስረጃ ማቅረብ የሚች።
3ኛ ዕድሜው ከ40 ዓመት በታች የሆነ።
4ኛ ቢቻል አዲስ ኪዳን (አቋቋም)የተማረ ቢሆን ይመረጣል
5ኛ በስነምግባሩ የተመሰከረለትና ማስረጃ ከነበረበት ቦታ ማቅረብ የሚችል።
6ኛ ደምወዝ 4000(አራት ሺህ ብር)
7ኛ የፈተና ቦታ በሰሜን ጎጃም ሀገረስብከት ጽ/ቤት
8ኛ የምዝገባ ቀን ከሐምሌ 21/11/እስከ28 2017 ዓ/ም ድረስ
👉 ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር ለምትፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሀገረስብከቱ ጽ/ቤቱና በሰሜን አቸፈር ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት መረጃችሁን ይዛችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
👉የፈተና ቀን 28/11/2017 ዓ/ም ከሰሜን ጎጃም ሀገረስብከት ጽ/ቤት
ባሕርዳር
ተደራሽነት እንዲኖረው ሸር አድርጉት
ለበለጠ መረጃ 0918838447 ወይም 0918112177 ይደውሉ

3,237 ኢ አማንያን ወደ ኦርቶዶክሳዊ በረት ተደመሩ***በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረስብከት ውስጥ በምትገኘው አንዲት ቀበሌ ብቻ በአንድ ጀንበር 3,237 ኢ አማንያን የስላሴ ልጅነት ማ...
30/07/2025

3,237 ኢ አማንያን ወደ ኦርቶዶክሳዊ በረት ተደመሩ
***

በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረስብከት ውስጥ በምትገኘው አንዲት ቀበሌ ብቻ በአንድ ጀንበር 3,237 ኢ አማንያን የስላሴ ልጅነት ማግኘታቸው ተሰምቷል።

በነገራችን ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ አብዛኛው የገጠር ቀበሌ አገልጋይ የለም እንጅ ለመጠመቅ ቀን የሚጠብቀው ኢአማንያን ብቻ አሁን ካለው የደቡብ ኦርቶዶክስ መጠን የሚሰተካከል ነው።

ዓለም ላይ ለጥምቀት የመጣውን ተጠማቂ ካህኑ በማጥመቅ አገልግሎት ድካም ወይም ተጠማቂያን የሚለብሱት ነጠላ ስላለቀ ብቻ " ነገ ኑ" ተብሎ የሚመለሱ ጥምቀት ፈላጊ ነፍሳት የሚገኙት ደቡብ ውስጥ ነው።

አንድ ቀበሌ ሙሉ ህዝብ አጥምቀህ የምትመለሰውም ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ምናልባትም የቅድስት ቤተክርስትያን የማገገም የምስራች ከደቡብ የመታወጁ ቀን እየቀረበ ነው።

(Kune Demelash kassaye -Arba Minch)

አንድ ቀን ከመኖሪያ ሰፈሬ አቅራቢያ ካለ ፍርድ ቤት ለየት ያለ እንቅስቃሴ አየሁና ትኩረቴን ስለሳበው ተጠጋሁ።የታጠቁ የፀጥታ ሰዎች በዛ ብለው ግን ተራርቀው ቁመዋል።አንድ የተከበበ ሰው ግን ...
29/07/2025

አንድ ቀን ከመኖሪያ ሰፈሬ አቅራቢያ ካለ ፍርድ ቤት ለየት ያለ እንቅስቃሴ አየሁና ትኩረቴን ስለሳበው ተጠጋሁ።
የታጠቁ የፀጥታ ሰዎች በዛ ብለው ግን ተራርቀው ቁመዋል።
አንድ የተከበበ ሰው ግን አለ- ጠጋ ስል ካህን እንደሆኑ በክህነት ቆባቸው አወቅሁ። ደነገጥሁና የበለጠ ቀረብ አልሁ።
ቁመታቸው ረዥም ነውና በግርግር መሐልም ሁነው በክህነት ቀሚስ አየኋቸው። ቀሲስ በላይ መኮንን።
እውነት ለመናገር ቶሎ ከቆባቸው ቀጥሎ የታየኝ እጃቸው ላይ የያዙት መስቀልና ቀሚሳቸው ነበር።
ወደ መኪና እንዲገቡ ሲመሯቸው አስቤ ይሁን ሳላስበው ጮህ ብዬ “ቀሲስ” ብዬ ተጣራሁ። የታጠቁ ሰዎች ዙረው ሲያዩኝ አንዴ ልሳለም አልኋቸው። ቀሲስ ስለሰሙኝ “ እንዴ ምን ችግር አለው” ብለው መጡና አሳለሙኝ።
ደህንነቴንና ስለአገልግሎት ጠየቁኝ። እግዚአብሔር ያስፈታዎት ብያቸው ወደ ፖሊስ መኪና ገቡ። እኔም ወደቤቴ አመራሁ።
ደብልቅልቅ ያለ ስሜት ነበረኝ!
ያደረጉት ቆብ፣ የያዙት መስቀል፣ የለበሱት ቀሚስና ፎጣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው።
ካህናት ጥሩም ይስሩ ክፉ ከቤተ ክርስቲያኗ ነጥሎ ለማየት በሚቸገር ማኅበረሰብ ውስጥ ቀሲስ በላይንም ስታዩ ያቺን ፍጽምት ቤት አለማሰብ አይቻልም።
እርግጥ ነው ቀሲስ ቤተ ክርስቲያኗን ለአንድ ብሔር ሰጥተው የከሰሱበት እና በመናገር ልደግመው በማልፈልጋቸው የስህተተት ንግግሮችና ድርጊቶች ውስጥ አልፈዋል።
ዛሬም በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ሳይሆን በራሳቸው ጉዳይ ጥፋተኛ ተብለው ታስረዋል።
አንዳንዶች የቀደመውን የአስተዳደርና የቀኖና ጥሰታቸውን ጨምረው የእግዚአብሔር ፍርድ አድርገው ሲጽፉ አይቻለሁ- እሱን እግዚአብሔር ይወቅ!።
በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን በያዙት መስቀል ምክንያት ቤተ ክርስቲያንን አስበን አለማዘን አንችልም። አገልጋዮች በተለይም በክህነት መሰላል ውስጥ ያሉ ቅድስት እና ንጽሕት ስለሆነች ቤታቸው ሲሉ እንዲህ ካለው የሕይወት መንገድ ቢርቅሉን በወደድን!
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ባለ የሰዎች ስጋዊ ድካም እንደማትወከል ለማስረዳትም አቅም ያጣንበት ጊዜ ሆነ!
ባይሆን ሁላችንም በድካም ታስረናልና እግዚአብሔር ያስፈታን!
ዛሬ ሰዎች ጋር አንድ ጉዳይ ቢነሳ እንደገና ትዝ አለኝ!
ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸዉ

ክብሩ
27/07/2025

ክብሩ

🤔ሻማን በሕይወትሽ የጎዳሽ ምንድነው ቢሏት ከክብሪቱ በላይ አቅፌ የያዝኳት ክር ናት አለች ይባላል  በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የጓዳችሁ ምንድነው ቢባሉ ይህን ቃል ...
21/07/2025

🤔ሻማን በሕይወትሽ የጎዳሽ ምንድነው ቢሏት ከክብሪቱ በላይ አቅፌ የያዝኳት ክር ናት አለች ይባላል

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የጓዳችሁ ምንድነው ቢባሉ ይህን ቃል የሚደግሙት ይመስለኛል

ቤተክርስቲያንን እየጎዳት ያለው እያበላች እያጠጣች የያዘችው ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ያስቀመጠችው በቤተመቅደስ ያለው አገልጋይ ነው

ኢትዮጵያንም የጎዳት ገበሬ አርሶአደር ነጋዴ አይደለም በንብረቷ የሾመችው ከደመወዙ በላይ በየቀኑ በአበል አንቀባራ የያዘችው በእራስዋ ላይ የተሸከመችው ጥጋበኛ ነው

🤔ለሁላችንም በእያንዳንዳችን ዙሪያ ካሉ ሰዎች ውጭ ምንም አይነት ስጋት የለብንም ሥጋታችን ያከበርነው የወደድነው ብዙ ነገር የሆንለት በችግሩ የደረስንለት እንደሻማ እየቀለጥን ያገለገልነው ሰው ነው የሚያሳዝነው መጎዳታችን አይደለም

ከጉዳታችንን አለመማራችን ነው 🤔🤔🤔

21/07/2025

አሳዛኝ መረጃ‼️
በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት የመርዓዊ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሚካኤል የ፬ቱ ጉባዔያት መምህር የሆኑት መምህር ሥሙር ታደሰ ተገደሉ።

የሰበካ ጉባኤ አባል አጫሽ፣ ጫት ቃሚ...?ነጋሽ ሚዲያ የቀረቡት የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አብሯቸው የሚሠራውን "ሲጋራ አጫሽ ነው" አሉት። ካህን እንዴት እንዲህ ይላል? የሚለውን ክርክር ተ...
21/07/2025

የሰበካ ጉባኤ አባል አጫሽ፣ ጫት ቃሚ...?

ነጋሽ ሚዲያ የቀረቡት የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አብሯቸው የሚሠራውን "ሲጋራ አጫሽ ነው" አሉት። ካህን እንዴት እንዲህ ይላል? የሚለውን ክርክር ተውትና። የአጥቢያ ምዕመናን ሰበካ ጉባኤ አባል እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነው? በአግባቡ አስበን እንመርጣለን? የምንመርጠው ራሱን የማይገዛ አጫሽና መጠጥ ሲገለብጥ የሚያድርን ነው? በቃለ ዐዋዲው መሠረት ሰበካ ጉባኤ አባል ለመሆን አንዱ መስፈርት ቆራቢ የሆነ የሚል ነው። በደህናው ጊዜ እከሌ ቆራቢ ነው ማለት ከታማኝነት ጀምሮ እስከ ቅንነት ድረስ ትርጉሙ ብዙ ነው።

አሁንማ ከልማት ኮሚቴ እስከ ሰበካ ጉባኤ አጫሽ ካለማ ጫት ቃሚ ወሮ በላ የሰበካ ጉባኤ አባል የሚጠፋ አይመስለኝም። ቢያንስ ሰበካ ጉባኤ አባል የምናደርገውን እንዴት ማወቅ ያቅተናል? እውቀትና መንፈሳዊነት መለኪያ ማድረግን ትተው የምርጫ ጊዜ ተደራጅተው ይመጡና በቲፎዞ የሚያስመርጡ ወሮ በላ መንጋዎች አሉ። በተግባርም ታይቷል። ብቻ የምንመርጠውን አለማወቅ መፍትሔ የሚያመጡ ሳይሆን ብዙ ውስብስብ ችግር ፈጣሪዎችን ቦታ እየሰጠን ነው። ሲጋራ አጫሽ፣ ጫት ቃሚ፣ መጠጥ ገልባጭ ... ራሱን የማይገዛ ሰውን መምረጥ መዘዙ ብዙ ነው።

"የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው ማቴዎስ5:9 የሚል የእግዚአብሔር ቃል አንግበው በእነሱ አጠራር " የትግራይ ኦርቶዶክስ ሲኖድስ የሚባሉት ስለ ሰላም ለመነጋገርና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋ...
21/07/2025

"የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው ማቴዎስ5:9 የሚል የእግዚአብሔር ቃል አንግበው በእነሱ አጠራር " የትግራይ ኦርቶዶክስ ሲኖድስ የሚባሉት ስለ ሰላም ለመነጋገርና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ለመገናኘት በዛሬው ቀን ወደ አዲስ አበባ አምርተዋል። የሚል በድምፂ ወያኔ ላይ አንብበናል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖድስ ቤተክርስቲያን ጋር ይነጋገራሉ ወይስ አይነጋገሩም ያሉት ነገር የለም።

20/07/2025

አድባራትና የገዳማት ጸሐፊዎች ቁጥጥሮችና ሒሳብ ሹሞች ዝውውር ሊደረግ መሆኑን የተዋሕዶ የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። ለተጨማሪ መረጃ ፔጃችንን ላይክና ፎሎው በማድረግ ቤተሰብ ይሁነን። እናመሠግናለን🙏🙏

ከፕሮቴስታንት ባህል ወደ አሐቲ ቤተክርስቲያን ዘጠኝ ምዕመናን ተመልሰዋል። ይህ አገልግሎት በገጠር ሸመራ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን በተደረገ እንቅስቃሴ ነው። ጠንካራ ሥራ ከተሠራ ቅጣንባሩ ...
20/07/2025

ከፕሮቴስታንት ባህል ወደ አሐቲ ቤተክርስቲያን ዘጠኝ ምዕመናን ተመልሰዋል። ይህ አገልግሎት በገጠር ሸመራ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን በተደረገ እንቅስቃሴ ነው። ጠንካራ ሥራ ከተሠራ ቅጣንባሩ ከጠፋበት ጴንጤነት ብዙዎችን ነጥቆ ማውጣት ይቻላል።

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግንኙነት: የሩሲያ እና የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ትስስርዛሬ በሩሲያ ኦርቶዶክስ እና በህንድ ኦርቶዶክስ መካከል የተፈጠረው ግንኙነት በኦርቶዶክሳዊው ዓለም ...
20/07/2025

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግንኙነት: የሩሲያ እና የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ትስስር

ዛሬ በሩሲያ ኦርቶዶክስ እና በህንድ ኦርቶዶክስ መካከል የተፈጠረው ግንኙነት በኦርቶዶክሳዊው ዓለም ውስጥ ያለው ክፍፍል እየተጠናቀቀ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ነው ተብሏል። ይህ ግንኙነት በብዙ የስምምነት ነጥቦች ላይ የተመሰረተ ነው።

ገዳማት ትስስር እና ልውውጥ: ከብዙ ስምምነቶች መካከል፣ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ገዳማት የቱፊት ስርዓት ልውውጥ እንዲያደርጉ መወሰናቸው ጎልቶ ይታያል። ይህ የገዳማት ትስስር አዲስ የተጨመረ ስምምነት ነው።
የቅዱሳን ትምህርት: በቅርብ ጊዜ ከተደረሰባቸው ስምምነቶች አንዱ፣ የሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት የሚዘከሩ ቅዱሳንን ለመጪው ትውልድ ለማስተማር መሰማማታቸው ነው። ይህም የጋራ መንፈሳዊ ቅርስን የማስቀጠል ፍላጎት ያሳያል።
ሆስፒታል መስፋፋት: በቀሪዎቹ ስምምነቶች ውስጥ፣ የሆስፒታሎችን ማስፋፋት ጉዳይ ላይ ትኩረት ተደርጓል።
ይህ ሁሉ የሚያሳየው በኦርቶዶክሳዊት ዓለም ውስጥ የመተባበርና የአንድነት መንፈስ እያደገ መምጣቱን ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብዙ የውስጥ የቤት ስራ ቢኖራትም፣ ያላትን መንፈሳዊ ጸጋ በመጠቀም የውጪውን ዓለም መምራት የምትችልበት አቅም እንዳላት በአሁኑ ሰዓት ግን ውስጣዊ ጉዳዮቿን በመፍታት ላይ እንደምትገኝ እና የውጪው ቅንጦት የሁለተኛ ደረጃ ጉዳይ ሆኖባታል ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያላትን ታላቅ መንፈሳዊ ሀብት ተጠቅማ አለምን የመምራት አቅም ያላት መሆኑን ነው፣ ሆኖም መጀመሪያ የውስጥ ጉዳዮቿን ማስተካከል እንደሚያስፈልጋት እሙን ነው ።

ይህም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ደስታን የሚፈጥር እና ለአንድነት ተስፋ የሚሰጥ ነው።

ዝሙት ሳይፈጽሙ ሥጋዊ ድንግልና ባይገኝባቸው   !!!ዝሙት ሳይፈጽሙ ሥጋዊ ድንግልና ባይገኝባቸው   ቤተክርስቲያን ተክሊልን የማትከለክልባቸው ሁኔታዎች አሉ። እኒህ ሁኔታዎች ፍትሐ ነገሥቱ ላይ...
20/07/2025

ዝሙት ሳይፈጽሙ ሥጋዊ ድንግልና ባይገኝባቸው !!!

ዝሙት ሳይፈጽሙ ሥጋዊ ድንግልና ባይገኝባቸው ቤተክርስቲያን ተክሊልን የማትከለክልባቸው ሁኔታዎች አሉ።
እኒህ ሁኔታዎች ፍትሐ ነገሥቱ ላይ ተብራርተው የተገለጡ አይደሉም። ሥርዓትን በተመለከተ በሲኖዶስ የሚወጣውን ትእዛዝ የሚጨምር በመሆኑ የግድ ጽሑፍ ላይ መሥፈር አለበት የሚባል አይሆንም። ኅሊናዊ ጉዳይ ነው ሞራል ከመጠበቅ አንጻር እንዲሁም ያለፍላጎት በግዴታ የሚፈጸም አልያም በነገሮች አስገዳጅነት የሚከናወን በመሆኑ ነው ።
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፳፬ ም.፭ ክፍል ደግሞ ፥ መጅ ፩ . . . ተክሊል የሚፈጸምላቸው ደግናልን መሆናቸውንና እንዴት መፈጸም እንዳለበት በደፈናው ያወራል ።
" አዕማደ ምሥጢራት ሁለተኛ እትም ኅዳር 2005 ዓ.ም በመምህር አብርሃም ገብረ ዮሐንስ የተዘጋጀ መጽሐፍ ገጽ 104" ላይ የሰፈረውን ሀሳብ የሚከተለው ነው :-
1/ በሕክምና ምክንያት ድንግልናቸውን ለሚያጡ ሰዎች ተክሊል አይከለከሉም
2/ በተፈጥሮ ሲወለዱ የድንግልና ምልክት የሌለባቸው ጥናት እንደሚያመለክተው ከ100-3 ፐርሰንት አሉና እነዚህ አይከለከሉም ።
3/ ለአቅመ አዳም ወሔዋን ሳይደርሱም ሆነ ደርሰው በጠለፍ ( ግዳጅ) አማካኝነት ለመደፈር ሲወሰዱ የተቻላቸውን ያህል ጥረት በማድረግ የሚየስጥላቸውን ሰው ወይም ረዳት ድምጽ በማሰማት ተጣርተው ነገር ግን የሚደርስላቸው ቢያጡ ተክሊል አይከለከሉም ዘዳ. 22:25
4/ አንዳንድ ሴቶች ከአቅም በላይ ሥራ ሲሠሩ ሰውነታቸው ስለሚሳሳ ድንግልናን ወደማጣት ያደርሳቸዋል ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Orthodox Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Orthodox Media:

Share