Abiyot wami

Abiyot wami ሀገሬ ክብሬ ናት

ሰው መሆንቃልስ ኬት ይገኛል ከቶ ምገልፅበትየአንቺን ሰው መሆን የአንቺን ሰብአዊነትራስን አሳልፎ ለሌላ መሞትንአየሁት ባንቺ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትንልክ እንደ መላኩ እንደቅዱስ ገብርኤልህፃን ልጅ...
06/08/2020

ሰው መሆን

ቃልስ ኬት ይገኛል ከቶ ምገልፅበት
የአንቺን ሰው መሆን የአንቺን ሰብአዊነት

ራስን አሳልፎ ለሌላ መሞትን
አየሁት ባንቺ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን

ልክ እንደ መላኩ እንደቅዱስ ገብርኤል
ህፃን ልጅን ማትረፍ ከእቶኑ መሃል
ሰው መሆን እንዲህ ነው ሌላ ምን ይባላል

15/07/2020

እሰይ

መቀነቷን ፈታ ቦንድ የቆረጠችው
ብርሃኔ ብላህ ተስፋ ላረገችው
አንተን ላመነችው

እሰይ ያገሬ ወንዝ ልብህ ተመልሶ
ጭስ ያስነባት እናት ልመናዋ ደርሶ

ደረስክላት አሉ እንባዋን ልታብስ
ቤቷን ብሩህ አርገህ እምዬን ልትክስ

ሻ/ል አብዮት ዋሚ
ሐምሌ 8/2012 ዓ/ም
ደቡብ ሱዳን ጁባ

06/07/2020

የነገ የነገ

ሀገር አለኝ አትበል ስሟንም አትጥራ
እትብቴ ተቀብሯል አትበል ከአፈሯ
እባክህ ዝም በል ምንም አታውራ

ለሷ ብታዝንማ እሷን ብትልማ
ትቆጭ ነበረ ክፉዋን ስትሰማ
ትደርስ ነበረ ሮጠህ በህመሟ

በተደላደለ አገር ላይ ተቀምጠህ
እጅህ ላይ ባለ ስልክ መርዙን እየረጨህ
ሰውን እያጋጨህ

የምትኖረው ኑሮ የእውነት መስሎሃል
ሀገርን በመካድ ህሊና ታስረሃል
የነገ የነገ ያንተው ክፉ ስራ ያቅበዘብዝሃል

ሻ/ል አብዮት ዋሚ

ደቡብ ሱዳን ጁባ
ሰኔ 29/2012

30/06/2020

የሚያቆምሽ የለም

በወርሃ ሰኔ ቀን እየቆጠሩ
ጠብ እሸመቱ ጥላቻን ሚዘሩ
የመግደል ሱሰኞች በደም የሰከሩ

በንፁሃን መሞት ደስታን የሚያገኙ
እድገትሽን ሳይሆን ውድቀትሽን ሚመኙ

በሽግግር ድልድይ እንዳትሻገሪ
ሸብበው በመያዝ ቆመሽ እንድትቀሪ

ብቅ ብቅ እያሉ በሰኔ ደመና
ህይወትን ቢቀጥፉ ዘንድሮም እንዳምና
አይዞሽ ኢትዮጵያዬ ይሔም ያልፋልና

ቢፈታተኑሽም ሌት ተቀን ቢሰሩ
እነሱም ያልፋሉ ዘላለም አይኖሩ

ስለዚህ ሀገሬ አንቺ እናት ዓለም
ዛሬ ላይ ክፉዎች ቢነሱሽም ሠላም
ነገን ከመሻገር የሚያቆምሽ የለም

ሻ/ል አብዮት ዋሚ

ደቡብ ሱዳን ጁባ
ሰኔ 23/2012

30/06/2020

ገዳይም ይሞታል

በግፍ ሰውን መግደል ማሸነፍ መስሎታል
ቀን ይቆጥራል እንጂ ገዳይም ይሞታል

27/06/2020

በል ቅኔህ ይፈታ

ገና መሬት ሳቲዝ ሳትቆም ተደላድለህ
ዝናህ የተሰማው በዓለም ላይ ነጉደህ

አንዴ በአረብ ሊግ አንዴ በአሜሪካ
አንዴ በአውሮፓ አንዴ በአፍሪካ

አንዴ በሲ ኤን ኤን አንዴ በአልጀዚራ
በቀን አስር ጊዜ ስምህ እየተጠራ
ስላንተ ሲነገር ስላንተ ሲወራ

ባለብዙው ሃይል ባለብዙው ግርማ
ቁልቁል የምትፈሰው ማንንም ሳትሰማ

አባይ ታላቁ ወንዝ የወንዞቹ ጌታ
አሁንስ በቃ በል ምንድነው ዝምታ
አረፍ በልና ጉባ ላይ አንድ አፍታ
በወርሀ ሐምሌ በል ቅኔህ ፍታ

ሻ/ል አብዮት ዋሚ

ደቡብ ሱዳን ጁባ
ሰኔ 20/2012 ዓ/ም

21/06/2020

አንደበተ-ርቱዕ ናቸው። እሳቸው ሲናገሩ አይን እና ጆሮን የሚስብ ማግኔት ያለባቸው ቃላትን በተረጋጋ መንፈስ ወደ አድማጭ ተመልካች ያፈሳሉ። በዛላይ ግርማሞገሳቸው ውበትን ከዕውቀት ጋር አከናንቧቸዋል።

ከሐረር ጦር አካዳሚ እስከ ሩሲያና አሜሪካ የውትድርናን ሳይንስ ቀስመዋል። ተዋጊ ብቻ ሳይሆን መርቶ ማዋጋትንም ኖረውበታል።

ውትድርና የተከበረ ሙያ መሆኑን ከሀገር መውደድ ጋር ቁልጭ አድርገው አስገንዝበዋል። በጃንሆይ ዘመን ውትድርናን አንድ ያሉት ብ/ጀ ካሳዬ ጨመዳ አሁንም በወታደራዊ ቁመናቸው እንደተዋቡ ቆፍጠን ብለው በመከላከያ ቴሌቪዥን እንግዳ ሆነው ሳያቸው እጅጉን ደስ አለኝ።

እንደዚህ አይነት ልምድና ተሞክሮ ያላቸውን የጦር መሪ ላቀረብሽልን የስራ ባልደረባዬ በዚህ አጋጣሚ ማመስገን ፈለኩኝ።

ብራቮ ወይን

Address

Addis Ababa

Telephone

+251917517469

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abiyot wami posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category