09/03/2026
አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ እንድትሆን እየተሠራች ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ የሌሎች ከተሞች ምሳሌ እንድትሆን በብዙ ዘርፎች እየተሠራች መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ይህንን የገለጹት ከዓድዋ ድል መታሰቢያ አቅራቢያ በፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ የተገነባውን "የድል ፕላዛ" መርቀው ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ነው።
ስለ ድል ፕላዛው ዝርዝር መረጃ
✅ የግንባታ ወጪ፦ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን አካቶ በ2 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ወጪ የተገነባ ነው።
✅ ስፋት፦ በ21 ሺህ 906 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ነው።
✅ ያካተታቸው አገልግሎቶች፦ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፣ ሱቆች፣ ባሕላዊ ሬስቶራንት፣ ቢሮዎች፣ የአርት ጋለሪ፣ የአረንጓዴ ቦታ፣ የመኪና ማቆሚያ፣ ካፌቴሪያ እና የልጆች መጫወቻዎችን ይዟል።
የድል ፕላዛው የተገነባበት ቦታ ቀደም ሲል ቆሻሻ ይጣልበት የነበረ እና ወንጀል ይፈጸምበት የነበረ ስፍራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውሰዋል።
አሁን ላይ የአካባቢውን መለወጥ የሚመጥን የ2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት የተሠራ በመሆኑ፣ ፕላዛው የቦታውን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለዜጎች የሥራና የንግድ ቦታ መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።
በይመር አደም