Surafel bitaw

  • Home
  • Surafel bitaw

Surafel bitaw ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት

‹‹ኪዳን›› የሚለው ቃል ‹‹ተካየደ – ተዋዋለ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ፤ ተማማለ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን፣ ትርጕሙም ኪዳን፣ ውል፣ መሐላ፣ ቃል ኪዳን፣ የውል ቃል ማለት ነው /ዘዳ.፳...
26/10/2025

‹‹ኪዳን›› የሚለው ቃል ‹‹ተካየደ – ተዋዋለ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ፤ ተማማለ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን፣ ትርጕሙም ኪዳን፣ ውል፣ መሐላ፣ ቃል ኪዳን፣ የውል ቃል ማለት ነው /ዘዳ.፳፱፥፩፤ ኤር.፴፩፥፴፩-፴፫፤ መዝ.፹፰፥፫/፡፡ በሌላ በኩል ኪዳን የጸሎት ስም ሲኾን፣ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ፣ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት ያስተማራቸው ጸሎት ኪዳን ይባላል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳን (ውል፣ ስምምነት) የተቀበለችበት ዕለት (የክብረ በዓል ስም) ደግሞ ኪዳነ ምሕረት ይባላል፡፡

በየዓመቱ የካቲት ፲፮ ቀን የምናከብረው ይህ በዓል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ በልጇ በመቃብር ላይ ኾና ‹‹ኦ ወልድየ ወፍቁርየ እስእለከ በእንተ ዘተሰባእከ እምኔየ ወበማኅፀንየ ዘጾረተከ፤ ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፤ ከአንተ ጋር ከአገር ወደ አገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ›› እያለች ስትጸልይ ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደእርሷ መጥቶ ‹‹ሰላም ለኪ ማርያም እምየ፤ እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?›› አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእመቤታችንና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሰየሙትን ዅሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡

ጌታችንም ‹‹ይህን ዅሉ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ›› ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው ‹‹… ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፤ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርያችን መመኪያ ናት፡፡ አንተ ‹መታሰቢያሽን ያደረገ፣ ስምሽንም የጠራ፣ የዘለዓለም ድኅነትን ይድናል› ብለሃታልና …፤›› በማለት የሚማጸነው፡፡

በተአምረ ማርያም መጽሐፍ እንደተመዘገበው በዚህ ዕለት የሚታሰቡ ሁለት ተአምራት አሉ፤ ከእነዚህም አንደኛው የስምዖን ታሪክ ነው፡፡ ስምዖን የሚባል እንግዳ ተቀባይ ደግ ሰው ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያፍርምና ከዕለታት አንድ ቀን በእንግድነት ከቤቱ ገብቶ ‹‹ልጅህን አርደህ ካላበላኸኝ ሌላ ምግብ አልበላም›› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ስምዖን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆየና ‹‹አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው›› በማለት፣ ‹‹የእግዚአብሔርን እንግዳ›› ላለማሳዘን ሲል ልጁን አርዶ አቀረበለት፡፡ እንግዳ መሰሉ ሰይጣንም ሥጋውን ቅመስልኝ ብሎ ግድ አለው፡፡ ስምዖንም (በላዔ ሰብእ) አርዶ ያዘጋጀውን የልጁን ሥጋ በቀምሰ ጊዜ ሰይጣን ስላደረበት (ስለተዋሐደው) ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ቤተሰቦቹን፣ ጎረቤቶቹንና መንገደኛውን ዅሉ ይበላ ጀመር፡፡ በአጠቃላይ ፸፰ ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ በቍስል የተመታ ሰው አገኘና ሊበላው ሲል ‹‹ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ በሥላሴ፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም ለመነው፤ እርሱም ዝም አለው፡፡

በመጨረሻም ‹‹በድንግል ማርያም ስም›› አለው፡፡ ስምዖን የእመቤታችንን ስም በሰማ ጊዜም ወደ ልቡናው ተመልሶ ‹‹እስኪ ቃሉን ድገመው›› አለው፤ በሽተኛውም መልሶ ‹‹ስለ ድንግል ማርያም ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ ለመነው፡፡ ያን ጊዜ ‹‹ይህችስ እንደምታስምር በልጅነቴ ሰምቻለሁ›› ብሎ ጥቂት ውኃ ሰጠው፤ ውኃው ጕሮሮውን እንኳን ሳያርስለት ‹‹ጨረስህብኝ›› ብሎ ነጥቆት ሔደ፡፡ በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አግኝቶ ሊበላ ሲል ገበሬው ‹‹በላዔ ሰብ የምትባል አንተ ነህ?›› ባለው ጊዜ ‹‹ለካስ አመሌን ሰው ዅሉ አውቆብኛል›› ብሎ ዋሻ ገብቶ በመጸጸት በዚያው ሞተ፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ጽልመት መጥተው ሲወስዷት እመቤታችን ‹‹ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?›› አለችው፡፡ ጌታችንም ‹‹ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋ፣ ፈጣሪውን የካደ ሰው ይማራልን?›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹በስሜ የተጠማውን ውኃ አጥጥቶ የለምን?›› ብላ ስምዖንን (በላዔ ሰብእን) አስምራዋለች፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ብርሃን መጥተው ወደ ገነት አስገብተዋታል፡፡

ሁለተኛው ተአምር ደግሞ ከብሮ ከኖረ በኋላ ለድህነት በተጋለጠ አንድ ምእመን ላይ የተደረገ ነው፤ ከክርስቲያን ወገን የኾነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ‹‹ከብሬ በኖርኹበት አገር ተዋርጄ አልኖርም›› ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ከአገሩ ወጥቶ ሲሔድ ሰይጣን ያዘነ ሰው መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ ‹‹ሥላሴን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትንን፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን ወርቅ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡ ዅሉንም ካደለትና ወርቁን ተቀብሎ ዞር ሲል ‹‹ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም ‹የአምላክ እናት አይደለችም› ብለህ ካድልኝ›› አለው፡፡ ሰወየውም ‹‹እርሷንስ አልክድም›› ስላው በደንጊያ ቀጥቅጦ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት የሟቹን ነፍስ ሊወስዱ ሲሉ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ፡፡ እመቤታችንም ጌታችንን ‹‹ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከልብኑ ይትመሐር እምየ፤ እናቴ፣ ውሻ ይማራልን?›› አላት፡፡ እመቤታችንም፡- ‹‹‹ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ› ያልኸው ቃል ይታበላልን?›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ምሬልሻለሁ›› አላት፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ›› ባለው መሠረት ከቅዱሳን ጋር ያደረጋቸው ቃል ኪዳኖች ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ከላይ በተአምራቱ እንደተመለከትነው አንዱ ለእመቤታችን የሰጠው የአማላጅነት ኪዳን ነው፡፡ ማማለድ ማለት ስለሌላው መጸለይ፣ መለመን፣ የደረሰውን ችግር እንዲወገድ ማድረግ፣ ማስማር (ይቅርታ ማሰጠት) ማለት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ከእግዚአብሔር በታች ከቅዱሳን ዅሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት የማማለድ ሥልጣን ‹‹ሰአሊ ለነ ቅድስት፤ ቅድስት ሆይ ለምኚልን›› እያሉ ለሚለምኗት ዅሉ ከእግዚአብሔር እያማለደችና እየለመነች ምሕረትን እንደምታሰጥ ቀናውንና የተመሰገነውን ሃይማኖት የምንከተል ምእመናን ዅሉ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ እንደመኾኗ ከዅሉም ቅዱሳን በበለጠ ለእግዚአብሔር ቅርብ ናትና፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም ኾነ በሰው ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘት ወይም ቅርብ መኾን ደግሞ አንድን ጉዳይ በቀላሉ ለማስፈጸም ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ፡-

መልአኩ ቅዱስ ገብርአል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ባለሟል በመኾኑ የድኅነትን ምሥጢር አብሣሪ ኾኗል /ሉቃ. ፩፥፲፱-፳፮/፡፡

አስቴር የንጉሡ አርጤክስስ ሚስት በመኾኗ በወገኖቿ አይሁድ የታወጀውን የሞት አዋጅ አስለውጣለች /መጽሐፈ አስቴር ፫፥፲/፡፡

ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟል በመኾኑ ‹‹ይህንን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ?›› በማለት ለእስራኤላውያን ምሕረትን አሰጥቷል /ዘፀ.፴፪፥፲፬/፡፡

ስለዚህ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትም እንደ ፀሐይ የበራ ሐቅ ነው፡፡ ይህንን እውነት ቅዱስ ያሬድ ሲመሰክር፡- ‹‹ወታስተሠርዪ ኀጢአተ ሕዝብኪ ተበውሀ ለኪ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለሕዝብሽ፣ ለወገኖችሽ የኃጢአት ይቅርታን ታሰጪ ዘንድ፤ ዘለዓለማዊ ሕይወትንም ለሚወርሱ ዅሉ መሸጋገሪያ ድልድይ ትኾኚ ዘንድ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ሥልጣን አግኝተሻል›› በማለት አመስግኗታል /አንቀጸ ብርሃን/፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው፡- ‹‹ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ፤ የድኅነት ምክንያት ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት፣ መርገም (ኀጢአት) ባጠፋን ነበር›› ብለዋል፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡– ‹‹ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፡፡ መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፡፡ ለጻድቃን ያይደለ ለኀጥአን አሳስቢ፡፡ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሶስቢ፤›› ሲሉ ይማጸኗታል /ቅዳሴ ማርያም ቍ.፻፷፭-፻፸፩/፡፡

21/10/2025

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

አሳዛኝ ዜና፡ በድሬዳዋ-ደወሌ ባቡር አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ!ከደወሌ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ላይ ትላንት ምሽት 8፡00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ...
21/10/2025

አሳዛኝ ዜና፡
በድሬዳዋ-ደወሌ ባቡር አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

ከደወሌ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ላይ ትላንት ምሽት 8፡00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ አሰቃቂ አደጋ ደረሰ።

በዚህ አደጋ ምክንያት የ14 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ 29 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከሺኒሌ ወረዳ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሺኒሌ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

Via ድሬ ቲቪ

ነብስ ይማር ወገኖቻቸን

በትላንቱ የሽኝት ሂደት ከታዩ አንጀት የሚበሉ ትእይንቶች መካከል  አንዱ የኦርቶዶክስ አባት የአባ ማቲያስ መንሰፍሰፍና ለቅሶ ነበር። ድምጽ ሳያሰሙ የእንባ ዘለላዎችን አፍስሰዋል።አባ ማቲያስ ...
21/10/2025

በትላንቱ የሽኝት ሂደት ከታዩ አንጀት የሚበሉ ትእይንቶች መካከል አንዱ የኦርቶዶክስ አባት የአባ ማቲያስ መንሰፍሰፍና ለቅሶ ነበር። ድምጽ ሳያሰሙ የእንባ ዘለላዎችን አፍስሰዋል።

አባ ማቲያስ ከሙፍቲ ጋር በቅርበት የሰሩ ስለሆኑ በዚያ ታላቅ ሰው ስብዕና ውስጥ የታመቀውን እዝነት፣ሰብአዊነት፣ጥበብ፣ለዛና የሀገር ፍቅር ጠንቅቀው ያውቃሉ። አሁን ያ ተስረቅራቂ የዕውነት ድምጽ፣ ያ ባለለዛ አንደበት፣ ያ ገደብ አልባ ፍቅር፣ያ አስታራቂ ስብዕና ወደማይቀርበት ዓለም ተሸጋግሯል። እዝነት ታላቁን ልጇን አጥታለች። ሀገር አሳቢ አባቷን ተነፍጋለች። ይህ እንደአባ ማቲወስ ባለ ስብዕና ውስጥ የሚፈጥረው የሀዘንና አጋር የማጣት ስሜት ጥልቅና ብርቱ እንደሚሆን ዕሙን ነው። "ክንዴ ክንዴ" እያሉ አልቅሰው እንዳይወጣላቸው ያሉበት ዕድሜና የሀላፊነት ደረጃ አይፈቅድላቸውም። እናም የእንባ ዘለላዎች የውስጣቸው ህመምና ቃጠሉ መልዕክተኛ ሆነው እርሳቸውን ሳያስፈቅዱ በጉንጮቻቸው ላይ ፈሰሱ። ሰውነታቸው የአባትነት ክብራቸውን አሸንፎ እንደሰው አለቀሰ። ሰውነት እንደዚህ ነው። "ሰው እንሁን፤ሰውነት ይቀድማል!!!"

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡።የኀዘን መግለጫ"አድኅነኒ እግዚኦ እስለመ ኀልቀ ኄር  አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቋልና።" መዝ. ...
20/10/2025

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡።

የኀዘን መግለጫ

"አድኅነኒ እግዚኦ እስለመ ኀልቀ ኄር
አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቋልና።" መዝ. 11፥1

እግዚአብሔር በየዘመናቱ አገርን ያለ መካሪ፣ ሕዝብን ያለዘካሪ አይተወውም!

ለዚህም ምስክሩ ታላቅ አረጋዊ ፣ የበሳል አእምሮ ባለቤት፣ አገርን የሚወዱ፣ ሕዝባቸውን የሚያከብሩ፣ የተጠቁት ወዳጅ ፣ የትውልድ አባት የሆኑት የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ነበሩ፡፡

ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች ፡፡

ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው ::

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢተዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

የኀዘን መግለጫበተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርርቲያን  ስም  እንገልጻለን!!የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን...
20/10/2025

የኀዘን መግለጫ

በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርርቲያን ስም እንገልጻለን!!

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ዜና እረፍት የሰማነው በታላቅ ኀዘን ነው። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የሰላም የፍቅር ፣የአንድነት ተምሳሌት አባት ነበሩ።

በአገልግሎት ዘመናቸው ለአገር አንድነትና ለሰላም ቅድሚያ የሚሰጡ፣የርህራሔ እና የፍቅር ሰው በመሆናቸው
በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተወደዱና የተከበሩ የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በመላው ኢትዮጵያን ዘንድ በመልካም ስብእናቸው እና በርሕራሔያቸው በታሪክ ሲታወሱ ይኖራሉ።

በእኒህ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት በነበሩት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ዕረፍት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
አባ ሳዊሮስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

አቡነ ኪሮስበሀገረ ሮም ከአባቱ ንጉሥ አብያ ከእናቱ አንሰራ ተወለደ፡፡ ደጋግና ቅዱሳን ወላጆቹም እግዚአብሔርን በመፍራት እየኖሩባት በነበረበት ወቅት ይህን የተመረጠ አባት ሰጣቸው፤ አባ ኪሮስ...
18/10/2025

አቡነ ኪሮስ

በሀገረ ሮም ከአባቱ ንጉሥ አብያ ከእናቱ አንሰራ ተወለደ፡፡ ደጋግና ቅዱሳን ወላጆቹም እግዚአብሔርን በመፍራት እየኖሩባት በነበረበት ወቅት ይህን የተመረጠ አባት ሰጣቸው፤ አባ ኪሮስ የተወለደው በታኅሣሥ ፰ ቀን ነበር፡፡ ጻድቁ አባት በቅድስና ሕይወትና ትጋት ማዕረግ አባ ኪሮስ ከመባሉ በፊት ‹ዲላሶር› ተብሎ ይጠራ እንደነበር ታሪኩ ይገልጻል፡፡

ቅዱሱ ከታላቅ ወንድሙ ቴዎድሮስ ጋር በሚኖርበት ጊዜ አባቱ ስለሞተ ሀብቱን ከወንድሙ ጋር በመካፈል ለድሆች መጸወተ፤ መንፈስ ቅዱስ ኪሮስ ብሎ ጠራውና “ለብዙዎች አባት ትሆናለህ፤ በቃልህም ክርዳድ ይነቀላል፤ የአንድ ቀን መንገድ ሂድና ገዳማዊ መነኰስ ታገኛለህ፤ ከእርሱም ልብሰ ምንኲስና ትለብሳለህ” አለው፡፡ እንደ ታዘዘው በሄደ ጊዜ ከአንዲት በዓት የራስ ፀጉሩ እስከ እግሩ የሚደርስ፣ ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ወጥቶ “ኪሮስ መነኲሴ ለመሆን ወደዚህ መጣህን? አለው፡፡ ኪሮስም ግርማውን እያደነቀ ቀርቦ ተባረከና ሦስት ቀን ከቆየ በኋላ “ኪሮስ ሆይ፥ እንደ እኔ መሆን ትፈልጋለህን?” አለው፡፡ እርሱም “አዎ፥ በጣም እፈልጋለሁ” ባለው ጊዜ አባ በብኑዳ ትንሽ ደመናን ጠርቶ በዚያ ላይ በመሆን ከአስቄጥስ ገዳም በመሄድ የምንኲስናን ልብስ ተቀብሎ በዚያችው ደመና ኪሮስ ካለበት ቦታ ተመለሰ፡፡ ያመጣውን አልባሰ ምንኲስናም ለኪሮስ አለበሰው፡፡

ለአባ በብኑዳ ሁልጊዜ በሠርክ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋዐ ወይን ቅዱስ ሚካኤል ያመጣለት ነበር፡፡ አባ ኪሮስ በዚያ ለአባ በብኑዳ እየታዘዘ ሲኖር አንድ ገዳማዊ ሰው ወደ አባ በብኑዳ መጥቶ ሳለ ምንም ነገር እንደሌለው ዐይቶ “ምን ትበላለህ?” ቢለው “አምላካችን ይሰጠናል” አለው፡፡ ያ እንግዳ መነኲሴም በልቡ “እንደ እኛ ሰው አይደለምን?” እያለ ሲያስብ አባ በብኑዳ በመንፈስ ዐውቆ “ለምን እንዲህ ታስባለህ?” “እኔም እንዳንተ በደለኛና ኀጥእ የሆንኩ መነኲሴ ነኝ” አለው፡፡ ይህን እየተነጋገሩ ሳለ የሠርክ ጸሎት ደርሶ በኅብረት ሲጸልዩ ፈጽሞ ደስ የሚል መዓዛ መጣ፤ ወዲያውም የተዘጋጀ ኅብስትና ጽዋዐ ወይን ይዞ ቅዱስ ሚካኤልን ሲመጣ አየውና ተቀበለው፤ ያ እንግዳ መነኲሴ ግን አላየውም፤ አሁንም “አስቀድሞ ያልነበረ ይህን ጽዋና ኅብስት ከየት አገኘው? ይህ ባሕታዊ መሠሪ ነው” እያለ አሰበ፤ አባ በብኑዳም “ለምን እንዲህ ክፉ ታስባለህ?” አለው፤ መነኲሴውም አድንቆ ተቀምጠው መመገብ ጀመሩ፡፡

ያ እንግዳ መነኲሴ ግን ከዚያ ኅብስተ ሰማይ ቆርሶ በልብሱ ደብቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሄደ፡፡ በዚያ ያሉ መነኰሳትንም ሰብስቦ ያን በረድ የሚመስል ኅብስተ ሰማይ አሳያቸው፡፡ “የት አገኘኸው?” ቢሉት “በዮርዳኖስ ገዳም ውስጥ በብኑዳ የሚባል መሠሪ ሰው አለ፤ ኑ ተከተሉኝና ታመጡት ዘንድ ወደዚያ ልውሰዳችሁ” አላቸው፡፡ ይህን ሲነጋገሩ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ያችን የኅብስት ቁራሽ ወደ ሰማይ ወሰዳትና በልዑል ፊት ሰገደ፤ እግዚአብሔርም “መልካም አገልጋዬ ሆይ፥ የተቀደሰውን ለውሻ የሰጠ በብኑዳ ክፉ አደረገ፤ ስለዚህም በአንበሳ ተሰብሮ እንዲሞት አደረግኹ፤ ይህም በረከት ይከለከላል፤ ይህንንም ኅብስት በበረሃ ላለ ፊልሞና ለሚባል መነኲሴ እስከ ዕለተ ሞቱ ሲሳይ እንዲሆነው ስጠው” አለው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም እንደ ታዘዘው አደረገ፡፡ የአስቄጥስ ገዳም ቅዱሳንም ያን መነኲሴ “እኛን ማን መምህርና ፈራጅ አድርጐ ሾመን” አሉት፤ በዚህ ጊዜ አዘነና ወደ ማደርያው ሂዶ ታንቆ ሞተ፡፡ነህን?አሁን ዐይንህ ጠፋ ማን ይረዳሃል? ማንስ ይመራሃል?” አለው፡፡ ይህን ሲሰማ አባ ኪሮስ ወደ ጌታችን ፈጽሞ እያለቀሰ ጸለየ፤ ጌታችንም ወደርሱ መጥቶ “ኪሮስ ሆይ፥ ሰላም ላንተ ይሁን፤ በእውነት አንተ ሰውን ወዳጅ ነህ፤ ድካምህ ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተመዝግቧል፡፡ ልጁን በስምህ ለሚጠራ፣ በእምነት ሆኖ የገድልህን መጽሐፍ ያጻፈ፣ ያነበበ፣ መባዕና ዕጣን ለቤተ ክርስቲያንህ የሰጠውን ላንተ ዓሥራት ይሆን ዘንድ ሰጠሁህ፤ ካንተም ጋራ ባሕረ እሳትን ይለፍ፤ ደስም ይሰኝ” አለው፡፡ ይህንኑ ብሎ ራሱን በእጆቹ ይዞ ፈወሰው፡፡ ቅዱስ ኪሮስም “በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ እነዚያን መነኲሳት ማርልኝ” አለው፡፡ ጌታችንም ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ፤ ነፍሳቸውንም ከሥጋቸው ጋር አዋሕዶ አሥነሳቸው፤ አባ ኪሮስንም በዐዩ ጊዜ አፈሩ፡፡ በአባ ኪሮስ ልመና አልባሰ ምንኲስና ለበሱ፤ ወደ ገዳማቸው የሚወስድ መንገድንም አሳይቶአቸው እንዲሄዱ አዘዛቸው፡፡ ከገዳማቸውም ደርሰው ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በጾም በጸሎትና እንግዳ በመቀበል ኖሩ፡፡ከብዙ ጊዜ በኋላ “ቅዱስ ኪሮስ የእነዚያን መነኰሳት ሕይወታቸውን ያይ ዘንድ መልአኩን ላክ” ብሎ በጸለየ ጊዜ ጌታችን “አንተው ሄደህ ጐብኛቸው” ብሎ ደመናን ጠርቶና በዚያች ላይ አውጥቶ “በሰላም ሂድ” ብሎ አሰናበተው፡፡ ኪሮስም ወዲያው ደርሶ ወደ ሚሳኤል መቃብር ሄደ፤ መነኰሳትም ባዩት ጊዜ ከአበምኔቱ ጋር ሮጠው ሄደው አቅፈው እየሳሙት “ደኅና ነህን?” አሉት። እርሱም “ውሻና ነዳይ ለምሆን ለእኔ ይህ ክብር ለምኔ ነው?” አላቸው፡፡ እነርሱም “ባለማወቃችን ያሳዘንህን ይቅር በለን” ባሉት ጊዜ “እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሚሳኤል ሆይ፥ ይቅር በለን በሉ” አላቸው፡፡ እነርሱም “የእግዚአብሔር አገልጋይ ሚሳኤል ሆይ፥ ይቅር በለን” አሉ፡፡ በዚህን ጊዜ “እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ፤ በእናንተ ምክንያት ወደ መንግሥተ ሰማያት ገብቻለሁና” የሚል ቃል ሰሙ፡፡ እነርሱም “ይህ የናቅነውና የጣልነው ሚሳኤል አይደለምን?” ብለው እያደነቁ አጽሙን ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊያስገቡት በፈለጉ ጊዜ “ባለበት ተውት፤ ነገር ግን በጸሎቱ ትጠቀሙ ዘንድ ተዝካሩን አድርጉ” አላቸው፡፡ እርሱም እየመከራቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ደረሱ፡፡ አባ ኪሮስም “የክርስቶስ ማደረያው ሆይ፥ ሰላም” ብሎ በተሳለመ ጊዜ “በሐከ ፈላሲ ክቡር፤ ክቡር መጻተኛ ሆይ ሰላም” ስላለው አደነቀ፡፡ አበ ምኔቱም “በቤቴ እደር” ቢለውም “አይሆንም” ብሎ በሚሳኤል ማደርያ በነበረው አንጻር ሄዶ አደረ፡፡ በማግሥቱም “ከእንግዲህ ወዲህ በመንግሥተ ሰማያት እንጂ በዚህ ምድር አንተያይምና በጸሎታችሁ አስቡኝ” ብሎ ተሰናብቷቸው ወደ ማደሪያው ተመልሶ አጋንንትን ‘ኑ’ ሲላቸው እየመጡ ‘ሂዱ’ ሲላቸው እየሄዱ ሲገዛቸው ኖረ፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኪሮስ በገድልና በትሩፋት እየተቀጠቀጠ ለብዙ ዘመናት ከኖረ በኋላ በ፪፻፸ ዓመቱ ሐምሌ ፰ ቀን ቅዱስ ዳዊት እየዘመረለት እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት በተገኙበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው ለይቶ አሳርጓታል፡፡ ጌታችንም የአስቄጥስ ገዳም አባ ባውማ ሥጋውን ገንዞ እንዲቀብረው አደረገ። እርሱም የንጉሥ ዘይኑን ልጅ ቅድስት ኢላርያን ሥጋዋን የገነዘ ነው። ደግሞም አባ ባውማ ጌታችን እንዳዘዘው በመንፈስ ቅዱስ የቅዱስ ኪሮስን ገድሉን የጻፈ ነው። “እኔ አባ ባውማም የቅዱስ ኪሮስን ገድሉን ጽፌ ለሚያነበውና ለሚሰማው ሁሉ መጽናኛ ይሆን ዘንድ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉና ወደ ገዳማትም ላክሁ” ተብሎ ተጽፏል።

ቅድስት ሥላሴሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው?◉ አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈ...
17/10/2025

ቅድስት ሥላሴ

ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው?

◉ አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም።

◉ አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ።

◉ አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ።

ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ በማለት ያመሰጥራል። ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን።

◉ አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም ቅድስት ይባላሉ።

◎ አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም። ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ።

◎ ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት እንላቸዋለን።

◉ አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ ቅድስት ይባላሉ ።

✍   የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔቅድስት ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ካህናትና ምእመናን መደራጀቷ፣ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር መመራቷ ከጥንት ያለ እንጂ ዐዲስ አለመሆኑን በቤተ ክርስቲያን ታ...
17/10/2025

✍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ካህናትና ምእመናን መደራጀቷ፣ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር መመራቷ ከጥንት ያለ እንጂ ዐዲስ አለመሆኑን በቤተ ክርስቲያን ታሪክና በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን በተለይም ግብረ ሐዋርያትን መሠረት በማድረግ፣ አመራሯና አስተዳደሯ በኢየሩሳሌም በተደረገው በሐዋርያት ጉባኤ ተመክሮና ተወስኖ በተላለፈው ሕግና ሥርዓት ይመራና በማኅበረ ካህናቱና ምእመናኑ ጠቅላላ ጉባኤ በተመረጡ ቅዱስ መንፈስ ባደረባቸው ኀላፊዎች ሥራ አስፈጻሚነት ይካሄድ እንደነበረ በመገንዘብ (የሐዋ ሥራ 6፡1-6) የተቋቋመ እንደሆነ በቃለ ዓዋዲ ተጽፏል፡፡

የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ማለት በአጥቢያ ለተቋቋመውና ለሚቋቋመው የቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ (የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ) የሚያስፈልጉትን አባላት ለመምረጥና በአባልነትም ለመመረጥ የሚችሉ ቤተ ክርስቲያንን በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸው፣ በሀብታቸውና በአገልግሎታቸው የሚረዱ ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የሚገኙበት የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብስብ ነው፡፡

የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት አደረጃጀቱም የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ የወረዳ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ሰበካ መንፈሳዊ ጉበኤ፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መሆናቸውንም በቃለ ዓዋዲ ተቀምጧል፡፡

የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤ ዓላማው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅና አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን ማድረግ፣ የቤተ ክርስቲያንን አገልጋዮች በሐዋርያዊ ተግባር ማደራጀት፣ ችሎታቸውንና ኑሮአቸውን ማሻሻል፣ ምእመናን በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው በክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር ማጠናከር በገቢ ራሷን ማስቻል ነው፡፡

ለአባልነት የተመረጠው ካህን ወይም ምእመን በተመረጠበት አገልግሎት ላይ የሚቆየው ለሦስት ዓመታት ይሆናል፡፡ ከሁለት ጊዜ በላይ በተከታታይ ሊመረጥ አይችልም፡፡ የአባላቱ ቁጥር በአምስትና በዘጠኝ መካከል ይሆናል፤ በሥራ ላይ ያሉት የሰበካ ጉባኤው አባላት የሥራ ዘመን ከማለቁ ከአንድ ወር በፊት የአዳዲስ አባላት ምርጫ ይፈጸማል፤ ነገር ግን አዳዲስ የተመረጡት አባላት ሥራቸውን የሚጀምሩት በሥራ ላይ ያሉት አባላት የሥራ ዘመን ሲያበቃ ነው፡፡

በየዓመቱ ጥቅምት ወር የሚካሄደው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሐዋርያዊ አገልግሎትን ለማጠናከር፣ አስተዳደርንና አሠራርን ለማዘመን አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡

በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚሰጠው አገልግሎት ሰማያዊ ዋጋ የሚያስገኝ፣ ለተቸገሩት በመስጠትና ጉዳት የደረሰባቸውን በመደገፍ ውስጣዊ ሰላም የሚገኝበት ነው፡፡ በካህናትና በምእመናን አንድነት የሚፈጸመው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ እና ሚዛኑን የጠበቀ የሚሆነው የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተረድተው በመሥራት ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የቀረበ አሳብ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተመክሮበት በተግባር ላይ የሚውል በመሆኑ ካህናትና ምእመናን ተማምነውና ተባብረው መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ቃለ ዓዋዲ ፳፻፱፣ ፬

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማበከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ንጉሡ መልኳ (ሥነ ላህይዋ) ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ። እነርሱም መላ ሀገሪቱን...
16/10/2025

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ንጉሡ መልኳ (ሥነ ላህይዋ) ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ። እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ከቆዩ በኋላ ንጽሕት ቅድስት አርሴማ እናታችንን በአንድ በሮሜ ባለ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር አገኟትና ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። ብፅዕት እናታችን ቅድስት ንጽሕት መርዓተ ክርስቶስ ቅድስት አርሴማም ሥነ ላህይዋ እጅጉን ልዩ የሆነ መልከ መልካም ነበረች።

ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ በልቡ በእጅጉ ፈቀዳ፤ እንዲያመጡለትም አዘዘ። ይህን እንደሰሙ እኒያ ደናግልና ቅድስት አርሴማ የገዳሙም እመምኔት የሆነችው ቅድስት አጋታ ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። በዚያም ሳሉ ንጉሥ ድርጣድስ የሚገዛው ግዛቱ ነበርና ከንጉሡ ድዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው። እርሱም በመልከ መልካምነቷ በእጅጉ ተስቦ እንዲህ ያለችቱንማ ለራስ ነው እንጂ ማን ሞኝ አለ በሚል ለንጉሡ ድዮቅልጥያኖስ መሥጠቱን ትቶ ለራሱ እዚያው አኖራት። ከደናግሉም ጋራ ካሠራቸው በኋላ ቅድስት እናታችንን ብዙ ሊያታልላት ሞከረ። እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ጥብዓት ያለባት ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች ናትና ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች። ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን ይበልጡኑ አጽናናቻት፤ ‹‹አይዞሽ! እንዲ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ›› ብላ እንዲያውም ይበልጥ አስጨከነቻት። በኋላም ንጉሡ በግድ ይዞ ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ንጉሥ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ።

ንጉሡም በዚህ ሁሉ ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ወዶ እኒያን ደናግል እርሷን ፊት ለፊታቸው አሠራትና አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው። እርሷ ግን ‹‹አይዟችሁ!›› እያለች ታጽናናቸው ነበር። የሚደንቀው ትሰቀቃለች ብሎ ያደረገላት ነገር እንዲያውም ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከትበት ነበር። በኋላም ‹‹አንቺንስ እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም›› ብሎ እጅግ ብዙ ሥቃያትን አሠቃያት። ከእነዚህም አንደኛው ሁለቱን ድንግል ጡቶቿን ቆረጠ፤ ይህም አልበቃ ብሎት ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣ፤ እርሷም እንዲህ ሳለች እመቤታችን ንጽሕት ድንግል ማርያም የብርሃን ልዩ ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም ማሠቃየትን በሰለቸ ጊዜ ከእኒያ ከቀሩት ደናግል ጋራ በመስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፈና ሁላቸውም የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። እኒህም ቁጥራቸው ሰባ አምስት ወንዶችና ሠላሳ ዘጠኝ ሴቶች ነበሩ።

ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከ። ቅዱስ ጎርጎርዮስም ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። (ይኸውም በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ ይገራል)። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግል እና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዕፅም ፍልሠታቸው በዚህ በቅዱስ ጎርጎርዮስ እንዲደረግ ሆነ፤ ይህም ታኅሣሥ ስድስት ቀን ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። ከዚያም በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው እንዲሁ ያከበሩበት ነውና እናከብረው ዘንድ ይገባናል።
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሣር

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ ትልቁ የመንጋው እረኛ፣ እጅግ መንፈሳዊ፣ የመድኃኒዓለም ፍቅር ሁሌ የሚያስለቅሳቸው አባት ናቸው። ባንድ ወቅት የቅዱስ ሚካኤል ክበረ በዓል ታቦት አክብረው እያ...
12/10/2025

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ ትልቁ የመንጋው እረኛ፣ እጅግ መንፈሳዊ፣ የመድኃኒዓለም ፍቅር ሁሌ የሚያስለቅሳቸው አባት ናቸው። ባንድ ወቅት የቅዱስ ሚካኤል ክበረ በዓል ታቦት አክብረው እያከበሩ ሳለ አንድ ሰው ይህን ታቦት /በጥላቻ እና በጽርፈት/ ቃል ከዚህ ውሰዱ ብሎ መሳደብ ጀመረ። አቡነ ቀውስጦስ የተናገርክበት እንደበት የተዘጋ ይሁን ባሉት ጊዜ ለስድስት ወር አንደበቱ ታሰረ። አንድ ከተማ ሄደው በእግራቸው እየተራመዱ ሳለ እንዲት ትንሽ ልጅ የረገጡትን መሬት በሶፍት እያሻሸች ሳለ ዞር ብለው አዩአት። ምን እያደረግሽ ነው ልጄ? ባሏት ጊዜ እናቴ ስለታመመች ብጹዕነትዎ የረገጡትን አሻሽቴ ወስጄ ሰውነቷም ባሻሽ ትድናለች አለቻቸው። አለቃሻው ሊቀ ጳጳስ እንባቸው ግጥም አለ። የያዘችውን ባርከው እናትሽን ጌታዬ ይማርልሽ ብለው መርቀው ሸኟት። ያቺ እናት ድና ባለ ጤና ሆና ተራመደች። በረከትዎ ይድረሰን በሉ።
እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት
@ቀሲስአሸናፊገብረማርያም

ጥቅምት 2 ቀን 1963 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዐረፉ። ከ55 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን (ጥቅምት 2) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ...
12/10/2025

ጥቅምት 2 ቀን 1963 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዐረፉ።

ከ55 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን (ጥቅምት 2) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ቀዳማዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ በተወለዱ በ79 ዓመታቸው ሰኞ ዕለት በዘጠኝ ሰዓት ዐረፉ።

Address


Telephone

+251967879122

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Surafel bitaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Surafel bitaw:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share