
23/07/2025
የ2017 በጀት ዓመት በቦሌ ክፍለ ከተማ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት ነበር፡፡ በበጀት ዓመቱ በመደበኛ ሥራዎች፣ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ በሰላምና ጸጥታ፣ በሰው ተኮር ተግባራት፣በሕዝብ ተጠቃሚነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎችም መስኮች ተጨባጭ ውጤቶች ከመመዝገባቸው ባሻገር የሕዝባችንን የተጠቃሚነት ጥያቄዎች በአግባቡ በመመለስ የኅብረተሰብ እርካታን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችለናል፡፡
እነዚህን ተግባራት ስናከናውን የአመራሩ፣ የፈጻሚዎቻችን፣ የአደረጃጀቶች፣የመላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች እና የአጋር አካላት የጋራ ርብርብና ቅንጅታዊ ሥራ ወሳኝ ሚና ነበረው፡፡ ይህንን ስኬት በ2018 በጀት ዓመትም አጠናክረን በመቀጠል በተለይም መልካም አስተዳደርን በተሟላ መንገድ ለማስፈን፣ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ፣ ብልሹ አሠራሮችን በማስወገድ ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እና የቦሌ መለያ የሆነውን አቅዶ የመፈጸም ብቃትና አርአያነት ያላቸው አዳዲስ አሠራሮችን የመተግበር ሥራችንን አጠናክረን ለማስቀጠል በበለጠ ትጋትና ቁርጠኝነት ልንረባረብ ይገባል፡፡ የክፍለ ከተማችንን ውጤታማ ጉዞ ቀጣይ ለማድረግ የጀመርነውን ጥረት አሁንም በላቀ ደረጃ ለማሳካት የሁላችንም የጋራ ርብርብ ወሳኝ በመሆኑ ለዚህ ግብ በጋራ እንድንተጋ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡
ዶ/ር እሸቱ ለማ
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ