
11/10/2024
ኮሜርሻል ኖሚኒስ በግንባር ቀደም ታማኝ ግብር ከፋይነት ለተከታታይ ስድስት ዓመታት ተሸላሚ ሆኗል
*******************************
• በ6ኛው የታማኝ የግብር ከፋዮች ሽልማት የወርቅ ተሸላሚ ሆነናል፤
• በቀጣይም አዳዲስ ሥራዎችን በመጨመር እና ገቢን በማሳደግ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንሠራለን፤
• ለእውቅና ሽልማቱን አስመልክቶ የምስጋና መርሐ ግብርም ተከናውኗል፤
አዲስ አበባ ጥቅምት 01/ 2017 (ሲኤን) ኮሜርሻል ኖሚኒስ በ2016 ዓ.ም በከፈለው ዓመታዊ ግብር የወርቅ ደረጃ ግንባር ቀደም ታማኝ ግብር ከፋይ ተሸላሚ ሲሆን፣ በተከታታይ ለስድስት ዓመታት የፕላቲኒየምና የወርቅ ደረጃ ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆኑም ተመስግኗል፡፡
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ስድስተኛው ዙር የፌደራል ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ የኮሜርሻል ኖሚኒስ ዳይሬክተር ጀነራል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ ተገኘተው የድርጅቱን ሽልማት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት ለታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ሀገራዊ ግዴታቸውን በታማኝነት ለተወጡት ግብር ከፋዮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ለበለጠ ጥቅም ሁላችንም የምንካፈለው ግዴታችንም ነው ብለዋል።
ለታማኝነታችሁ መንግስት የከፈላችሁት ግብር በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ለጋራ እድገታችን ወሳኝ በሆኑ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባሉ ግዙፍ የሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ አስተዋፅዖችሁን በማዋል ይህንን አደራ ያከብራል።
በግብር አሰባሰብ ላይ አወንታዊ ለውጦች እየታዩ ቢሆንም፣ ይህን ጥሩ ጅማሮ ማስቀጠል ይኖርብናል። ሙስናን መቀነስ እና የግብር አሰባሰብ ስርዓታችንን ማዘመን ለሁሉም የተመቸ፣ ግልፅ፣ ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ አሰራር ለመፍጠር ወሳኝ ናቸው ብለዋል።
ለእውቅና ሽልማቱ ጥቅምት 1ቀን 2017 ዓ.ም የኮሜርሻል ኖሚኒስ ዋናው መስሪያቤት የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል።
የድርጅታችን ዳይሬክተር ጀነራል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት፤ በግንባር ቀደም ታማኝ ግብር ከፋይነት ያገኘነው ሽልማት የሠራተኞቻችን፣ የማኔጅመንት አባላቱና የደንበኞቹም ጭምር በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡
በቀጣይ ሥራችንን በማስፋትና ገቢያችንን በማሳደግ የላቀ አፈጻጸም በማምጣት ተጠቃሚነታችንንና ለሀገር የምናደርገውን አስተዋፆ ይበልጥ እናጠናክራለን ብለዋል።
ሀገራዊ ኃላፊነታችን ለመወጣት እንደተጋነው ሁሉ በአገልግሎት አሰጣጣችን አሁን ካላን ጥራት በላቀ ሁኔታ በመፈጸም የበለጠ ውጤታማ መሆን ይገባናል ብለዋል።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ባለፉት ስድስት ዓመታት የወርቅ እና የፕላቲኒየም ተሸላሚ ተቃማኝ ግብር ከፋይ መሆኑ ይታወቃል።