Odaa Nabee

Odaa Nabee odaa nabee News goes deep beneath the surface, providing the key stories from Ethiopia and around the world.

Exciting reports and interviews from the worlds of politics, business, sports, culture and social

የሠላም በር‼   ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን ወታደራዊ ውጥረት ለማርገብ ጥረት እያደረገች መሆኑ ተሰምቷል‼በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየታየ የመጣውን እ...
24/02/2026

የሠላም በር‼

ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን ወታደራዊ ውጥረት ለማርገብ ጥረት እያደረገች መሆኑ ተሰምቷል‼

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየታየ የመጣውን እና ቀጠናዊ ስጋት የደቀነውን ወታደራዊ ውጥረት ለማርገብ ሳውዲ አረቢያ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መጀመሯ ተነግሯል። በተለይም በዚህ የካቲት ወር የሳውዲ መንግስት ሁለቱን ሀገራት ወደ ንግግር ጠረጴዛ ለመመለስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።

የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በአዲስ አበባ እና በአስመራ ባደረጉት ጉብኝት፣ የሁለቱን ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ አመራሮች በተጠናጠል በማነጋገር ለማግባባት ጥረት አድርገዋል። ይህ የሳውዲ ጥረት ትኩረት ያደረገው በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ እየታየ ነው የተባለውን የኃይል ማሰባሰብ ሂደት እንዲቆም እና ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

ሳውዲ አረቢያ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ውስጥ ቁልፍ ሚና ስትጫወት የመጀመሪያዋ አይደለም። እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 2018 በንጉስ ሰልማን ቢን አብዱላዚዝ አደራዳሪነት፡

📌 የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በጂዳህ ተገኝተው ታሪካዊውን "የጂዳህ የሰላም ስምምነት" መፈራረማቸው ይታወሳል።

📌 ይህ ስምምነት ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን የ"ጦርነትም የሰላምም የሌለበት" ሁኔታ መቋጫ የሰጠ ነበር።

አሁን እየተደረገ ያለው ጥረትም ያንን የሰላም መንፈስ ለመታደግ እና የቀይ ባህር ቀጠናን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

የውጥረቱ መነሻ ምንም እንኳን በይፋ የተገለጸ ምክንያት ባይኖርም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በኩል የሚሰሙ "የባህር በር" ጥያቄዎች እና ከሰሜኑ ጦርነት ማብቃት በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው የፖለቲካ ቅዝቃዜ ለውጥረቱ መባባስ እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ።

የሳውዲ አረቢያ የሰላም ጥረት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አለመግባባት ፈቶ ወደ ቀድሞው ወዳጅነት ይመልሳቸው እንደሆነ የሚጠበቅ ይሆናል።
Wasu Mohammed - Mereja

09/02/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ያስጀመሩበት ሥነ ስርዓት

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር እና  ወታደራዊ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ  የሰላም አማራጭን ተቀበሉበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ...
12/01/2026

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር እና ወታደራዊ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ የሰላም አማራጭን ተቀበሉ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር እና ወታደራዊ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር እና ወታደራዊ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ አፋህድ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ከእነ ሠራዊታቸው የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር፣ ወታደራዊ ዋና አዛዥ እና የወሎ ጠቅላይ ግዛት እዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ አፋህድ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር በአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ አማካኝነት ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሰላም ስምምነቱን በመቀበል ነው ከነሠራዊታቸው ወደ ሰላም የመጡት።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረገውን ስምምነት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መፈራረማቸው ይታወሳል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል ሲካሄድ የነበረው ውይይት እና ድርድር በአፍሪካ ሕብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ሲካሄድ መቆየቱም የሚታወስ ነው።

12/01/2026
28/12/2025

🎯ታሪክ የሰሩት ሴራ ዞሮ ሲወጋቸው ማየት እንዴት ደስ ይላል?

ለዓመታት "ኢትዮጵያን በውሃ፣ በወታደር እና በዲፕሎማሲ ከበብናት" እያሉ ሲፎክሩ የነበሩት የግብፅ ፈርኦኖች እና የሻቢያ ርዝራዦች፣ ዛሬ ባላሰቡት አቅጣጫ ወገባቸው ተሰበረ። እስራኤል እና ሶማሌላንድ ያደረጉት ታሪካዊ ስምምነት ለኢትዮጵያ ጠላቶች የመርዶ ያህል ነው።

🥁ይህ ዝም ብሎ ስምምነት አይደለም። ይህ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በወታደራዊ ደህንነት እና በስትራቴጂክ ትብብር የታጠረ የኒውክሌር ቀለበት ነው።

🎯ኢትዮጵያ በዝምታ የሰራችው ስራ፣ ዛሬ ጠላቶቻችንን መፈናፈኛ አሳጥቷቸዋል። እነሱ እኛን አጠርን ብለው ሲያስቡ፣ የራሳቸው ቤት እየፈረሰ ነው። ቀጠናው በሙሉ በፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ የኃይል ሚዛን እያመዘነ ነው፤ ማንም ሊደፍረው የማይችለው የብረት አጥር ተበጅቷል!

04/12/2025

በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተደረገ።

በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተደርጓል።

ስምምነቱ የክልሉ መንግሥት ለሰላም የሰጠው አማራጭ አንዱ አካል የኾነ እና ለቀጣይ የሕዝብ ሰላማዊ እፎይታ መሠረት የሚጥል ነው ተብሏል።

በሁለቱ ወገኖች ስምምነት በአደራዳሪነት የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ተሳትፈዋል።

የሰላም ስምምነቱ በአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ተወካይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መካከል ተደርጓል።

በስምምነት ሥነ ስርዓቱ ላይ ከጦርነት ያተረፈም ኾነ በጦርነት የተጠናቀቀ ግጭት ባለመኖሩ ይህ ድርድር ለክልሉ ሕዝብ ሰላም መነሻ እና ለሰላም የተሰጠ ተግባር ነው::

01/12/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አምባሳደር በትረ መንግስቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾሙ

-በሮቤ ከተማ  በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌላ ቦታ ሊዘዋወር የነበረ 400 ኩንታል ሲሚንቶ ተያዘ። አንዳንድ አካላት የሲሚንቶ ምርትን በመደበቅ ከተፈቀደው ዋጋ በላይ በድብቅ እየሸጡ መሆኑን ከማ...
30/10/2022

-በሮቤ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌላ ቦታ ሊዘዋወር የነበረ 400 ኩንታል ሲሚንቶ ተያዘ።

አንዳንድ አካላት የሲሚንቶ ምርትን በመደበቅ ከተፈቀደው ዋጋ በላይ በድብቅ እየሸጡ መሆኑን ከማህበረሰቡ በተገኘ ጥቆማና ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር በሚደረው ቁጥጥርና ፍተሻ በ18/2/15 በከተማዋ በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 400 ኩንታል ሲሚንቶ መያዙን የሮቤ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት አስታውቆአል።
በዛሬው እለትም በህገወጥ መንገድ ተጭኖ በሮቤ ከተማ ውስጥ አልፎ ወደ ሌላ ቦታ ሊዛወር 400 ኩንታል ሲሚንቶ ተይዞ በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የከተማዋ ንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፋይሰል አብዱሮ የገለፁት።
በህገ ወጥ ንግድና ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላትን ስራ ለመግታትና ህገወጥ ንግድን ለማስቀረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ በመሆኑ የከተማዋ ማህበረሰብ የድርሻውን ይወጣ ዘንድ መልእክት አስተላልፈዋል አቶ ፌይሰል ።
ጥቅምት 20/2015

"ባሌ፤ አርሲ፤ ሸዋና ጎጃም በእነዚህ አራት ክፍለ ሃገሮች እጅግ የትረፈረፈ የእህል ምርት አየሁ። ሲኒማ ተገብቶ እንደሚታይ ፊልም በዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ የተመረተ ምርት ወደ ቀሪ አለም ሲጫ...
30/10/2022

"ባሌ፤ አርሲ፤ ሸዋና ጎጃም በእነዚህ አራት ክፍለ ሃገሮች እጅግ የትረፈረፈ የእህል ምርት አየሁ። ሲኒማ ተገብቶ እንደሚታይ ፊልም በዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ የተመረተ ምርት ወደ ቀሪ አለም ሲጫን ቁልጭ ብሎ ተመለከትኩ......የሚመረተው ምርት በታላልቅ ዘመናዊ መሳሪያዎች መሆኑን ተመለከትኩ። የአሁን ገበሬ በበሬ እና በፈረስ እንደሚያርስ አይደለም ትልልቅ ትራክተሮች እዚህም እዚያም በስራ ተጠምደው ትራክተር ሲያርስ በግልጽ ተመለከትኩ።"

የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ፤ 1993/ በቄስ በሊና ሳርካ ገጽ 54

ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ምህወሓት ተስፋ ሲቆርጥ ውሸት ማቀናበር ያደገበት ልማዱ ነው።ህወሓት የሀገር መከላከያ  ሠራዊትን በትር መቋቋም ሲያቅተው የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋትን ተያይዞ...
30/10/2022

ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም

ህወሓት ተስፋ ሲቆርጥ ውሸት ማቀናበር ያደገበት ልማዱ ነው።

ህወሓት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በትር መቋቋም ሲያቅተው የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋትን ተያይዞታል። የሐሰት ፊልሞችን እያቀናበረ የሐሰት ክሶችን መፈብረክ ቀጥሏል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተላበሰው ዕሴት ሕዝባዊነት መሆኑን ዓለም ያውቀዋል። ይሄንንም እንኳን በሀገሩ እና በሕዝቡ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮው በተግባር አሳይቷል። ይሄንንም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሰላም ካስከበረላቸው ሕዝቦች የተሰጡት የምስክር ወረቀቶች እስከ ዘለዓለም ሲናገሩለት ይኖራሉ።

ህወሓትና ጋሻ ጃግሬዎቹ መጀመሪያ ተቋሙን ለማፍረስ ሞከሩ፤ አልተሳካም። ጥቅምት 24 ሌሊት በክህደት ወግተው ሊያጠፉት ተፍጨረጨሩ፤ አልተሳካም። ደጋግመው ጦር መዘዙበት፤ ሽንፈት አከናነባቸው። አሁን በመጨረሻ ወደ ቆርጦ ቀጥል አመላቸው ገቡ።

አንዳንድ የሠራዊታችን አባላት በተለያዩ ጊዜያት፣ ለተለያየ ዓላማዎች፣ የተናገሩትን ቆርጦ እየቀጠለ፣ የሠራዊቱን ስም በማጥፋት፣ ጉዞውን የሚገታ መስሎት፣ ህወሓት መከራ እያየ ነው።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከግንዘቤ እጥረትም ሆነ የጠላት መጠቀሚያ በመሆን ከዕሴቱ ውጭ የሆኑ መልክቶችን የሚያስተላልፉ አባላቱን በከፍተኛ የዲሲፒሊን ጥሰት ይቀጣል። ይሄንንም የሚያደርገው ራሱን እያረመና እያበቃ የመሄድ ነባር ሥርዓት ስላለው ነው። የተልዕኮው ዋና ግብ ሕዝብን ከጉዳት መጠበቅ ስለሆነም ነው።

ስለሆነም ሕዝባችን ከህወሓት የቆርጦ ቀጥል ሤራ እንዲጠነቀቅና በዓላማና በአቋም ከሠራዊቱ ጋር የጀመረውን ቅንጅት እንዲያጠናክር፣ የመከላከያ ሠራዊት ጥሪውን ያቀርባል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Odaa Nabee posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Odaa Nabee:

Share

Category