26/08/2024
የብአዴን ቡችላዉ ቡድን አቋራጭ የአራት ኪሎ ጉዞ !!
የዚህ ፕሮጀክት አስተባባሪዎች
ጥላሁን አበጀ
አስረስ ማረ
ማርሸት ፀሃይ
አረጋ ከበደ
ከደህንነቶችጋ ግንኙነት ፈጣሪ መንግስቱ አማረ
ከሃገር ውጪ በዋነኛነት ፦
መአዛ መሃመድ
ኢንጅነር ይልቃል
ጉዱ አንዳርጋቸው
መአዛ መሃመድ ይበልጥ የምትሰራው የፋኖ አመራሮች ከወያኔጋ በስምምነት ስልጣን እንዲረከቡ ማድረግ ነዉ ። ለዚህም ሃገር ውስጥ ይህን ግንኙነት ለመፍጠር የመቀሌው ጋዜጠኛ ወደነ አርበኛ ዘመነ ካሴ በቅርብ እንደመጣ የእዙ የፕሮፓጋንዳ ክፍሎች በይፋ እያስጮሁት ነበር።
በዚህ ጉዳይ ለወያኔ ስስ ልብ ያላት አሜሪካ ጣልቃ ገብታለች። ጠቅላይ ሚንስትሩን ስልጣን ለማስለቀቅ በቀላሉ እሺ ስለማይል ለማስወገድ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። እናሳ ማነው ስልጣን የሚረከበው?? ለዚህም በአፋጣኝ ሴንትራል ኮማንድ ማቋቋም አስፈላጊ ስለሆነ በአርበኛው ዘመነ ካሴ የሚመራው የጎጃም እዝ የራሱን ሴታፕ ሰርቶ መሯሯጥ ጀመረ። ሁላችንም እንደምናውቀው። በየሶሻል ሚዲያው ሲዟዟር ያየነው እና በእዙ ቃል አቀባይ በኩል ሲነገር እንደሰማነው ከመሪ ጀምሮ እስከታች ድረስ የስራ ድርሻ ሃላፊነት በመደልደል ሊያለማምዱን ሚዲያውን አጨናንቀውት ከርመው ነበር። ታዲያ ይህ የሆነው በማርሸት አማካይነት ገና ውይይት ላይ እያሉ ገና ምኑም ሳያዝ ነበር።
ሃሳብና እቅዳቸው ፦
በመጀመሪያ ከወያኔጋ በጋራ ለመስራት እና ከበአዴን ጋር ተሃድሶ ለማድረግ እንቅፋት ሊፈጥርብን ይችላል አይቀበለንም ብለው ያሰቡትን አርበኛ እስክንድር ነጋን ብዙ ተሳትፎ የማያደርግበትን ቢያደርግም በድምፅ ብልጫ ሃሳቡ ውድቅ ሊሆን የሚችልበት ዘርፍ ላይ ማስቀመጥ የሃገር ውስጥ የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ( በውጭ በተፅኖ የሚጥሉት ገዱ እና ይልቃልን ጨምሮ ሌሎቹ አንጃዎቻቸው) በዚህ ካልተሳካ እና እስክንድር መሪ የሚሆን ከሆነ በሱና በዙሪያው ያሉት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አስጀምሮ የማሸማቀቅና ተቀባይነት እንዲያጣ ማድረግ ከአማራ ፖለቲካ ማስወጣት ከተቻለም እስከወዲያኛው ማስወገድ።
ይህ ከሆነስ???
1ኛ~የነዘመነ ቡድን ከብአዴንጋ ስልጣን reform ያደርጉና ክልሉን በሰላም ይረከባሉ
2ኛ~ አብይ ከተወገደ ምክትሉ ተመስገን ጥሩነህ የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን ይይዛል። (የማርሸት ፀሃይ አጎት)
3ኛ~ በሂደት ዘመነ ካሴ የአዲሱ ጠቅላይ ምክትል(ለጊዜው) በመሆን ጉዞ ወደ አራት ኪሎ ይሆናል።
4ኛ~ የወያኔን የፕሪቶርያል ስምምነት ዋናው የፀጥታ ሃይሉን ወያኔዎች ትረከባለች። ከፋኖስ መሪ ነን ካሉትጋ በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ስለተስማማች።
5ኛ ~ አሁን የአማራው ጥያቄ ስለተመለሰ ፋኖ ወደመከላከያ ግባ ያልገባ ትጥቅ ያውርድ ይባላል ። ( መከላከያ በማን ስር ነው በህወሀት)
ወያኔ የፀጥታ ዘርፉን ከያዘች ወልቃይትና እራያ ስጋት የለባትም ማለት ነው። እና የአማራ ነፃነት ታጋይ ነን ባዮች በዚህ ጉዳይ ምን ይሉ ይሆን ? የስልጣን ጥማት የመሪነት እርሃብና ዝነኛነት ባለበት ዘመነ ካሤ ላይ የፋኖ መሪዎች ምን አቋም ይይዙ ይሆን ???
አደረጃጀቶችን መከፋፈል እና ከእዞች አፈንግጠው የወጡትን ስልጣን ድልድል ውስጥ አስገብተው ፖለቲካዊ ቁማር መጫወት በሚልም ጨርሰዋል ።