
02/06/2025
Abiy Ahmed Ali
የከምባታ ዞኑ ልዩ የተፈጥሮ ገጸ በረከት የሆነው ሀምበርቾ ተራራን በማህበረሰብ ተሳትፎ የኢኮ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎችም እጅግ የሚደነቁ ናቸው። በተራራው የተገነባው 777 የመወጣጫ ደረጃ አካባቢውን ተደራሽ የመስህብ ስፍራ ያደርገው ሲሆን፣ ተራራ መውጣትና የተለያዩ የአእዋፋት ዝርያዎችን መመልከት የሚወዱ ቱሪስቶች ወደ እዚህ ስፍራ በመምጣት ማራኪ ጊዜን ማሳለፍ ይችላሉ።
Equally impressive are the community-driven initiatives to transform Mount Hambaricho, a distinctive natural landmark in the zone, into an eco-tourism destination. The construction of 777 climbing steps has made the mountain more accessible, offering a unique experience for tourists who enjoy hiking and birdwatching.