Pro media tv ፕሮ ሚዲያ ቲቪ

Pro media tv ፕሮ ሚዲያ ቲቪ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Pro media tv ፕሮ ሚዲያ ቲቪ, Media/News Company, Bole, Addis Ababa.

ነብስህ በሰላም ትረፍ💔💔💔 #አሳዛኝ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከዚህ አለም በሞት ተለየበርካታ ፊልሞችን በመስራት የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ /ባባ/  ዛሬ  ታህሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም...
11/12/2022

ነብስህ በሰላም ትረፍ
💔💔💔

#አሳዛኝ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

በርካታ ፊልሞችን በመስራት የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ /ባባ/ ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ ላይ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
ከሰራቸው ፊልሞች መካከል
3+1፣ 300 ሺ ፣አስነኪኝ ፣ባላ ገሩ፣ የፍቅር ABCD ፣ብላቴና ፣ቦሌ ማነቂያ፣እንደ ባል እና ሚስት፣ኢንጂነሮቹ፣እርቅ ይሁን፣ ኢዮሪካ ፣ጉዳዬ፣ሀገርሽ ሀገሬ፣ ሕይወቴ፣ ህይወት እና ሳቅ፣ከባድ ሚዛን፣ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ፣ ኮከባችን፣ ማርትሬዛ፣ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ትዳርን ፍለጋ፣ አንድ ሁለት ፣ብር ርርር፣ወደው አይሰርቁ፣ወፌ ቆመች፣ወንድሜ ያዕቆብ ፣እንደ ቀልድ ፣ወቶ አደር ፣አባት ሀገር ፣የሞግዚቷ ልጆች፣ይዋጣልን፣ዋሻው፣ወሬ ነጋሪ ወጣት በ97 ሌሎችም ፊልሞች ሰርቷል።

የአሊ አላሙዲን የለስላሳ መጠጥ ድርጅት ስራውን ማቆሙ ተገለፀ❗️የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የለስላሳ መጠጦችን ማምረት እንዳቆመ ካፒታል ጋዜጣ አረጋግጧል ። እንደ ሰበን አፕ፣ ሚሪንዳ ፔፕ...
03/05/2022

የአሊ አላሙዲን የለስላሳ መጠጥ ድርጅት ስራውን ማቆሙ ተገለፀ❗️

የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የለስላሳ መጠጦችን ማምረት እንዳቆመ ካፒታል ጋዜጣ አረጋግጧል ። እንደ ሰበን አፕ፣ ሚሪንዳ ፔፕሲ፣ ኩል የተፈጥሮ ማዕድን ውሃ ያሉ መጠጦችን በማምረት ታዋቂ የሆነው ሞሃ አሁን ላይ የማምረት ሂደቱን አቁሟል።

የካፒታል ጋዜጣ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ኩባንያው ምርቱን ለማቆም የተገደደው ለምርቶቹ የሚሆን ጥሬ ዕቃዎች እጥረት ስላጋጠመው ነው ።

እንደ ካፒታል ምንጮች ገለጻ፣ ከጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ ኩባንያው በጥሬ ዕቃ እጥረት እና በውጭ ምንዛሬ እጦት ሳቢያ ከአቅሙ በታች በሳምንት ሦስት ቀን እየሠራ የነበር ቢሆንም ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ለስላሳ መጠጥ ድርጅቱ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ስራውን ሙሉ በሙሉ ማቆሙ ነው የተነገረው። ችግሩ እስኪስተካከል ድረስ ሰራተኞችም ዕረፍት እንዲወስዱ መደረጋቸው ተገልጿል።

©ካፒታል

የመግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩንቨርስቲዎች!!የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ።እስ...
03/05/2022

የመግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩንቨርስቲዎች!!

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ።

እስካሁን ባለው የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ያሳወቁ ተቋማት እና የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ/ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት
👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2015 ዓ/ም፤በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ
👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም፤ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም
👉 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም
👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም
👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም
👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም
👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም
👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም
👉 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም
👉 ASTU/AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1/2014 ዓ/ም
👉 ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9፤ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11
👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም
👉 ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች ጥሪ ሲያቀርቡ ተከታትለን የምናሳውቅ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጉዳይ ብቻ በ ፕሮ ሚዲያ ቲቪ የፌስቡክ ገፅ ላይ መከታተል ይቻላል።

ናይጄሪያዊዉ ፓለቲከኛ በምርጫ ካሸነፍኩ የሀገሪቱን ስም ወደ "ኒግሪሻ" እለዉጣለሁ አሉ!!የናይጄሪያ ፕሬዝዳንታዊ እጩ አዳሙ ጋርባ የሀገሪቱን ስም ወደ "የኒገሪሻ ፌዴሬሽን" ወይም በቀላሉ ኒግ...
27/04/2022

ናይጄሪያዊዉ ፓለቲከኛ በምርጫ ካሸነፍኩ የሀገሪቱን ስም ወደ "ኒግሪሻ" እለዉጣለሁ አሉ!!

የናይጄሪያ ፕሬዝዳንታዊ እጩ አዳሙ ጋርባ የሀገሪቱን ስም ወደ "የኒገሪሻ ፌዴሬሽን" ወይም በቀላሉ ኒግሪሻ ተብሎ እንዲለውጥ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡በምርጫ ካሸነፉ ከሚያደርጓቸዉ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ የሀገሪቱ የስም ለውጥ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የናይጄሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በቀጣዩ ዓመት የካቲት ወር ላይ ይካሄዳል።"እንዴት ነው የዚችን ሀገር ስም ቀይረን፣ በትክክል ፌደራላዊ እናደርጋታለን እና "የኒግሪሺያን ፌዴሬሽን" ወይም በቀላሉ ኒግሪሻ ብለን እንጠራዋለን በሚለዉ ላይ እንሰራለን ብለዋል። ጨምረዉም ሌዲ ሉጋርድ ናይጄሪያ ብላ ከመስየሟ በፊት ኒግሪሻ የጥንት ስማችን ነበር ሲሉ አክለዋል።

“እራሳችንን ከአሉታዊ አመለካከቶች ማፅዳት፣ በመደራጀት ከቅኝ ግዛት ማንነታችን መለየት እና መለያየት አስቀግደን ወደ አንድነት፣ የመደመር፣ የመቻቻልና የመተሳሰብ ፍቺ የምንሰጥበት ጊዜ አሁን ነው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡እንደ ጋና፣ኬንያ፣ቤኒን እና ቶጎ ያሉ ሀገራት የቅኝ ግዛት ስማቸውን ቀይረዋል በማለት "ማንነት ሁሉም ነገር ነው" ሲሉ ተከራክረዋል።

ጋርባ የአዲሱ የናይጄሪያ ስም ትክክለኛውን አጠራር የሚያሳይ ቪዲዮ አጋርተዋል፡፡

ደራሲ ይስማከ ወርቁ የመኪና መገልበጥ አደጋ ደረሰበት‼️ትናንት ሌሊት ሊነጋጋ አቅራቢያ 10:50 ላይ ደራሲ ይስማከ ወርቁ ከመገናኛ ወደ ላምበረት በሚወስደው መንገድ ወደ ቤቱ እያሽከረከረ ዲያ...
27/04/2022

ደራሲ ይስማከ ወርቁ የመኪና መገልበጥ አደጋ ደረሰበት‼️

ትናንት ሌሊት ሊነጋጋ አቅራቢያ 10:50 ላይ ደራሲ ይስማከ ወርቁ ከመገናኛ ወደ ላምበረት በሚወስደው መንገድ ወደ ቤቱ እያሽከረከረ ዲያስፖራ አደባባይ ላይ የመኪና መገልበጥ አደጋ ደርሶበታል ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የሚዲያ ሀላፊና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ረዳት ኮማንደር ማርቆስ ታደሰም የአደጋውን መድረስ ለብስራት ሬድዮ አረጋግጠዋል።

ረዳት ኮማንደር ማርቆስ አያይዘውም በደራሲው ላይ የደረሰው አደጋ ቀላል የሚባል እንደሆነና የካ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ተወስዶ ህክምና ከተደረገለት በኋላ ለተሻለ ህክምና ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል መወሰዱ አረጋግጠዋል ።

ደራሲው በአሁኑ ሰዓት ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገለት ይገኛል ሲሉ ሃላፊው ተናግረዋል።

በተጨማሪም የአደጋውን መንስኤ እና ዝርዝር ጉዳዩን ፖሊስ እያጣራው ይገኛል ብለዋል።

በቅርብ ቀን በ ፕሮ ሚዲያ ቲቪ የዩቲዩብ ቻናል ይጠብቁን አዳዲስ እና ምርጥ ምርጥ ፕሮግራሞች ወደ እናንተ እናደርሳለን በቅርብ ቀን ይጠብቁን
26/04/2022

በቅርብ ቀን በ ፕሮ ሚዲያ ቲቪ የዩቲዩብ ቻናል ይጠብቁን አዳዲስ እና ምርጥ ምርጥ ፕሮግራሞች ወደ እናንተ እናደርሳለን በቅርብ ቀን ይጠብቁን

Address

Bole
Addis Ababa

Telephone

+251925757604

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Pro media tv ፕሮ ሚዲያ ቲቪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Pro media tv ፕሮ ሚዲያ ቲቪ:

Share