ነጥብ - Netib

ነጥብ - Netib ይህ ፔጅ የተመረጡ ዜና እና አዝናኝ ጽሑፎች ይጋሩበታል::

19/04/2024
28/03/2024

ሌላ ታሪክ

አልማዝን አይቼ አልማዝን ባያትሦስተኛዋ አልማዝ ብትመጣ ድንገትሁለቱን አልማዞች ስላስረሳችኝምርጫየ በምርጫ ተበላሸብኝሦስቱንም አልማዞች ባያቸው ባያቸውይችም ያችም አልማዝ ሁሉም አልማዝ ናቸውለ...
04/03/2024

አልማዝን አይቼ አልማዝን ባያት
ሦስተኛዋ አልማዝ ብትመጣ ድንገት
ሁለቱን አልማዞች ስላስረሳችኝ
ምርጫየ በምርጫ ተበላሸብኝ
ሦስቱንም አልማዞች ባያቸው ባያቸው
ይችም ያችም አልማዝ ሁሉም አልማዝ ናቸው
ለሰሚው ግራ ነው የሚያደናግር
ከአልማዝ መሃል ቆሞ ባልማዝ መቸገር

07/02/2024

  በምግብ ውስጥ  አደንዛዥ ዕፅ  ደብቆ ተጠርጣሪ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ ። ግለሰቡ ከናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ይዞ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓ...
29/01/2024


በምግብ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ደብቆ ተጠርጣሪ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ ።

ግለሰቡ ከናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ይዞ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ የሄደው ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ ምግብ ይዞለት የሄደው ይኸው ተጠርጣሪ ከድፍረትም ድፍረት የሚያሰኝ ተግባር ነበር የፈፀመው፡፡

በወቅቱ በሳህን የተቋጠረው ምግብ እንጀራ ፍርፍር በማካሮኒ ነበር፡፡ በእነዚያ የማካሮኒ ቀዳዳዎች ውስጥ የሚያብለጨልጩ ነገሮች ተወታትፈዋል፡፡

ምግቡን ፈትሸው የሚያስገቡት የፖሊስ አባላት ባዩት ነገር ተጠራጥረዋል፤ ምግቡ ተዘርግፎ ሲፈተሽ ብዛት 51 የማካሮኒ ፍሬዎች በተጠቀለሉ የአልሙኒየም ወረቀቶች አባብጠዋል፡፡ ወረቀቶቹን በመፍታት ለማየት ሲሞከርም ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ግለሰቡ ከዚህ በፊት በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ በዚያው ፖሊስ መምሪያ ታስሮ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ድፍረት በተቀላቀለበት ሁኔታ አደንዛዥ ዕፁን በምግብ ውስጥ ደብቆ ወደ ተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ለማስገባት የሞከረው ጠያቂ ሰዎች የሚበዙበትን ሠዓት በማጥናትና የፖሊስ አባላት በዚያ ሰዓት ሊዘናጉ ይችላሉ ብሎ በማሰብ መሆኑም ታውቋል፡፡ በፈፀመው ወንጀል የምርመራ መዝገብ ተደራጅቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል፡፡

ታዋቂው ሙዚቀኛ አቤል ተስፋየ The Weekend ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ኮሰርት ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰምቷልThe Weekend መቸ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ ትክክለኛው ቀን ባይገለጽም ወደ ኢትዮ...
15/12/2023

ታዋቂው ሙዚቀኛ አቤል ተስፋየ The Weekend ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ኮሰርት ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰምቷል
The Weekend መቸ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ ትክክለኛው ቀን ባይገለጽም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ኮሰርት እንደሚያቀርብ ታውቋል
የኮነሰርቱ የመግቢያ ትኬቶችም ዝቅተኛው 90 ዶላር ወይም 5,000 ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግም 550 ዶላር ወይንም 30,000 ሺህ ብር ነው ተብሏል!!
The Weekend (አቤል ተስፋየ) የቀድሞው የመረር አውራጃ ገዥ የፊታውራሪ ተስፋየ ወንድምአገኝ የልጅ ልጅ ሲሆን የድምጻዊ ይሁኔ በላይ ባለቤት ጋር የአንድ አያት የልጅ ልጆች (የፊታውራሪ ቸስፋየ ወንድምአገኝ) የልጅ ልጆች ናቸው!!
The Weekend ከአርቲስትነቱ በተጨማሪ በሰብአዊ እርዳታው የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ በጋዛ ለተጎዱ ዜጎች ከ 2 ሚሊየን ዶላር በላይ ለግሷል !!

ዝነኛው ሼፍ በፊፋ ምርመራ ሊደረግበት ነው ባሳለፍነው እሁድ በአርጀንቲና አሸናፊነት በተጠናቀቀው የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ወደ ሜዳ በመግባት ከዋንጫው ጋር ፎቶ ሲነሳ በነበረው እውቁ የ...
24/12/2022

ዝነኛው ሼፍ በፊፋ ምርመራ ሊደረግበት ነው

ባሳለፍነው እሁድ በአርጀንቲና አሸናፊነት በተጠናቀቀው የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ወደ ሜዳ በመግባት ከዋንጫው ጋር ፎቶ ሲነሳ በነበረው እውቁ የምግብ አዘጋጅ ኑስራት "ሳልት ቤ" ላይ ፊፋ ምርመራ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

ቱርካዊው ዝነኛ የምግብ አዘጋጅ ሳልት ቤ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ከአርጀንቲና ተጫዋቾች ጋር ሜዳ ውስጥ በመግባት የዓለም ዋንጫውን ይዞ የሚያሳዩ ፎቶዎችን በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ አጋርቷል።

በፊፋ ደንብ መሠረት ባለ ወርቁን ዋንጫ ለመንካት ፈቃድ ያላቸው በጣም ጥቂት የተመረጡ ሰዎች ሲሆኑ እነሱም የውድድሩ አሸናፊ ቡድን አባላት፣ የፊፋ ባለስልጣናት እና የሀገራት መሪዎች ብቻ አንደሆኑ ፊፋ ይደነግጋል።

ከነዚህ ዝርዝሮች ውስጥ የማይካተተው "ሳልት ቤ" እንዴት ወደ ሜዳ ገብቶ ዋንጫውን መያዝ እንደቻለ ለማጣራት ፊፋ ምርመራ እንደሚያካሂድ ታውቋል።

በዓለም ዋንጫው ያደረገው ድርጊት ያላስደሰታቸው አካላት ከውድድሮቻቸው እያገዱት ይገኛሉ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት እንደሚደረግ የሚጠበቀው "US OPEN" የሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ "ሳልት ቤ" መገኘት እንደማይችል አወዳዳሪዎቹ ይፋ አድርገዋል።

(ሀዋርያው ጴጥሮስ fm 97.1)

The Central Bank of the Republic of Argentina discussed putting Messi on a thousand-peso currency note.✋(አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ...
22/12/2022

The Central Bank of the Republic of Argentina discussed putting Messi on a thousand-peso currency note.✋

(አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ ስም ገንዘብ ልትሰይም ነው

የመገበያያ ገንዘቡ 1000 የአርጀንቲና ፔሶ ሲሆን 10 ቁጥር የሜሲ ማሊያ ያረፈበት ይሆናል

09/11/2022

ፈረንጁ ማሲንቆ ተጨዋች

ባሕር ዳር ከተማ እየተገነባው ያለው አዲሱ የአባይ ድልድይ መረጃ፦👉 የድልድዩ ግንባታ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለት ሀምሌ 2011 ዓ.ም ተጀመረ። 👉በሶሥት አመታት ለማጠናቀ...
02/11/2022

ባሕር ዳር ከተማ እየተገነባው ያለው አዲሱ የአባይ ድልድይ መረጃ፦

👉 የድልድዩ ግንባታ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለት ሀምሌ 2011 ዓ.ም ተጀመረ።

👉በሶሥት አመታት ለማጠናቀቅ ታቅዶ ነበር።

👉በክረምት ወቅት የሚፈጠረው የወንዙ ሙላት ለሥራ አመች አለመኾን፣ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ድልድዩ ላይ የተደረገው የዲዛይን ማሻሻያም በተቀመጠለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ አድርጎታል።

👉ድልድዩ በአይነቱ እና በርዝመቱ ከሀገሪቱ የመጀመሪያው ነው። 380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር የጎን ስፋት አለው።

👉ለባሕር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበትን በሚያላብስ መልኩ እየተሠራ ነው ። በአንድ ጊዜ ስድስት መኪኖችን ማሳለፍ ይችላል።

👉የእግረኛ መንገድ እና የብስክሌተኞች መተላለፊያን ጨምሮ እየተገነባ ነው። 380 ሜትር ከሚረዝመው ዋናው የድልድዩ አካል ውስጥ 321 ሜትር ግንባታ ተጠናቅቋል።

👉ድልድዩ ስምንት ምሰሶዎች አሉት። እያንዳንዱ ምሰሶዎች ዘጠኝ በአጠቃላይ ደግሞ 72 ተንጠልጣይ መወጠሪያ የብረት ገመዶችን ይይዛል። ከ72ቱ መወጠሪያዎች ውስጥ የ64ቱ ሥራ ተጠናቋል።

👉ከተያዘለት በጀት በተጨማሪ 111 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አለም በደረሰበት ቴክኖሎጅ የታገዘ እና ለድልድዩ ልዩ ውበት የሚያላብስ የመብራት ቴክኖሎጅም ጎን ለጎን እየተገጠመለት ነው።

👉ወደ ድልድዩ የሚያገናኙ አራት ማሳለጫዎች እየተገነቡለት ነው። 4 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ደረጃውን የጠበቀ የድልድዩ መዳረሻ መንገድም ጎን ለጎን እየተገነባ ይገኛል።

👉ውበቱ እንደተጠበቀ ለ100 ዓመታት እንዲያገለግል ታልሞ የሚገነባ ነው።

👉ድልድዩ በመጭው ሰኔ 2015 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎቶ ክፍት እንደሚኾንም ይጠበቃል።

አቫንስ ሚድያ (Avance Media) የዘንድሮውን "100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት አፍሪካውያን" ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል። በዝርዝሩ ላይ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የዶት ኮኔክት አፍሪካ ...
02/11/2022

አቫንስ ሚድያ (Avance Media) የዘንድሮውን "100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት አፍሪካውያን" ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በዝርዝሩ ላይ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የዶት ኮኔክት አፍሪካ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሶፊያ በቀለ ተካተዋል።

በዘንድሮው ዝርዝር ላይ ከ36 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች የተካተቱ ሲሆን ናይጄርያ 18፣ ኬንያ 10፣ ጋና 7፣ ሴኔጋል 6 እና ታንዛንያ 5 ሰዎችን አስመርጠዋል።

28/10/2022

ልቤ አንችን በዳዳ 😂
የልጅቱ ጥያቄ የኔም ጥያቄ ነው

Address

Adwa
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ነጥብ - Netib posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share