Gospel Realm

Gospel Realm Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gospel Realm, Media, Somewhere, Addis Ababa.

ከጎኑ ተወለድን¤ ኢየሱስ በመስቀል ሳለ ያልሞቱትን ጭናቸውን ሰብረው ማውረድ በጀመሩ ጊዜ አንዱ ኢየሱስ እንደሞተ ለማረጋገጥ ጎኑን በጦር ወጋው። ከጎኑም ደምና ውሀ ፈሰሰ። ዮሐ ፲፱÷፴፩-፴፯❤...
29/07/2022

ከጎኑ ተወለድን

¤ ኢየሱስ በመስቀል ሳለ ያልሞቱትን ጭናቸውን ሰብረው ማውረድ በጀመሩ ጊዜ አንዱ ኢየሱስ እንደሞተ ለማረጋገጥ ጎኑን በጦር ወጋው። ከጎኑም ደምና ውሀ ፈሰሰ። ዮሐ ፲፱÷፴፩-፴፯

❤ ከዚህ ክፍል ደስ የሚለኝና ሚገርመኝ ነገር ቢኖር እኔ ከተወጋው ጎኑ መወለዴ ነው። "እንዴት?" በሉኝ.. ሔዋን አዳም ተኝቶ በተወሰደው አጥንት ከሱ እንደወጣች እኔም ክርስቶስ ሞቶ ከጎኑ በፈሰሰው ደምና ውሃ ዳግም ተወልጃለሁ።

❤ ውሃው:- መንፈስ የመያዝ ተፈጥሮ ያለው ነውና በዛ ውሃ ተጠምቄ አሮጌውን ማንነት አውልቄ አዲሱንም ህይወት አጥልቄ ከሱ ተወልጃለው።
ደሙ:- ከየትኛውም ሀጥያት እያነፃኝ በሰማይ ልጅና ወራሽ መሆኔን የማህተም ቀለም በመሆን አረጋግጦልኝ ቀጥያለው።
❤❤❤ እኔ የክርስቶስ ከጎኑ የወጣሁ ልጁ ነኝ!❤❤❤

የጌታ እራት* ጌታ ታልፎ ሊሰጥ ባለበት ቀን እንጀራን አንስቶ ስጋዬ ፅዋውን አንስቶ ደሜ ነው አላቸው። ግን ይሄ Password እስራኤልን ከግብፅ ካወጣ በኋላ ለብዙ አመታት የእስራኤል ህዝብ ...
21/07/2022

የጌታ እራት

* ጌታ ታልፎ ሊሰጥ ባለበት ቀን እንጀራን አንስቶ ስጋዬ ፅዋውን አንስቶ ደሜ ነው አላቸው። ግን ይሄ Password እስራኤልን ከግብፅ ካወጣ በኋላ ለብዙ አመታት የእስራኤል ህዝብ ቂጣ ሲጨፈጭፍ ቆይቶ ለመጀመርያ ጊዜ ሚስጥሩ ለደቀመዛሙርቱ የበራው ያኔ ነው።

♥ በጣም ከሚገርመኝ ሚስጥር የእስራኤል ህዝብ ከግብፅ ከወጣ ጀምሮ ሳያውቀው በቂጣና በፅዋ መልክ የጌታን ስጋና ደም ይካፈል ነበር። ጌታ ህዝቡን ያፈቀረው አለም ሳይፈጠር ነው። አለም ሲፈጠር ለሚሰራው ሀጢያት የሞተለትም አለም ሳይፈጠር ነው።

• አንድ ባለጸጋ ሰው አንዲትን ሴት ቢያፈቅር እሷን ለመተዋወቅ ሆነ ለመቅረብ የቅድሚያ ተግባሩ ግብዣ ነው። በትልቅ እውቅና አደባባይ ስፍራ ላይ እራት ይጋብዛታል። በግብዣውም የተወደደውንና ምርጡን ምግብ እንዲሁም ውዱን መጠጥ ያስመጣላታል። ይህ የመጀመሪያ ፍቅር መግለጫ ነው።
♥ ክርስቶስም ስላፈቀረን በአለም ሊጋብዘን ውዱን ምግብና መጠጥ ፈለገ። ግን ሁሉም በአይኑ የቀለለ ሆነ። ስለዚህ በአለም ላይ ያግኘው ውዱ ምግብ የገዛ ስጋው ውዱ መጠጥ የገዛ ደሙ ሆኖ አገኘው። ስለዚህ ከፍቅሩ የተነሳ ሳይሰስት ውዱን ስጋውን ቆርሶ ውዱን ደሙን ቀድቶ ሰጠን።

♦ ይህን በበላችሁ ጊዜ ሞቱን ትናገራላችሁ የሚለው ጥቅስ በቤተ ክርስቲያን እንደምንሰማው ትእዛዝም ጥያቄም አይደለም ። ነገር የተጋበዘችው ያቺ ተፈቃሪ የተጋብዘችውን ላለመናገር እንደማያስችላትና ለምትቀርበውና ለጓደኞቿ እንደምትወተውት ግብዣው አስችሎን ዝም እንደማንል የሚነግረን የልብ ጩኸታችንን የሚናገር ጥቅስ ነው።
_________\\________

♥ ሙዚቃ♥            ✍☞ የሰው ልጅ የሶስት  ነገሮች ስብስብ ነው፡፡ የስጋ የነብስ እና የመንፈስ፡፡ አለም ሳይፈጠር መላዕክት ለእግዚአብሔር ይዘምሩ ነበር፡፡ ነገር ግን በሰው ቋንቋ ...
02/03/2022

♥ ሙዚቃ♥
✍☞ የሰው ልጅ የሶስት ነገሮች ስብስብ ነው፡፡ የስጋ የነብስ እና የመንፈስ፡፡ አለም ሳይፈጠር መላዕክት ለእግዚአብሔር ይዘምሩ ነበር፡፡ ነገር ግን በሰው ቋንቋ አልነበረም፡፡ አለም ከተፈጠረ በኋላ ሰዎች እግዚአብሔርን ያገመልኩ ዘንድ በሰዎች ቃል እና ዜማ በልባቸው አስቀመጠ፡፡ ሙዚቃ ከስጋ እና ከነብስ ይበልጥ ለመንፈስ የቀረበ ነው፡፡ ሙዚቃን በሰማን ጊዜ በውስጣችን ፈለግነውም አልፈለግነውም የተለየ ስሜት ይሰማናል፡፡ ውስጣችን የተለየ የመንፈስ እርካታ ያገኛል፡፡ ከምንም በላይ ሊያስደስተንም ሆነ ሊያስለቅሰን እንባችንን ሊያፈስ ትልቅ አቅም አለው፡፡ በሕይወታችን ያለፋትን ትዝታዎችን ስናስታውስ በውስጣችን የትዝታ ዜማ ይፈጠራል፡፡ ወይንም በዛን ወቅት ይበልጥ ይደመጡ የነበሩ ሙዚቃዎች አብረው ይታወሱናል፡፡ በ Hollywood ፊልሞች ላይ የሙዚቃውን ድርሻ የሚወስዱ አካላት ፊልሙ በሰዎች ውስጥ እንዲቀር ተጠንቅቀው ይሰራሉ፡፡ ❖☞ የሙዚቃ ትልቁ ስራ እና ድርሻ ወደመንፈሳችን በመዝለቅ መንፈሳችንን ማነቃቃት እና መንፈሳችን ከመንፈስ ጋር እንዲገናኝ መንገድ መክፈት ነው፡፡ ሙዚቃ የመንፈሳዊው አለም ከገሀዱ አለም ጋር እንዲገናኝ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ሙዚቃ የእግዚአብሔርም የሰይጣንም ትልቅ መሳሪያ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሙዚቃ እያመለክነው እና እያመሰገነው መንፈሳችንን ስናነቃ ፈቃዳችንን አድምጦ ሲገናኘን ሰይጣን ግን "አንቺዬም" ሆነ "አንተዬ" ብለን ብቻ መንፈሳችንን አነቃቅትን መንገድን ስንከፍትለት ፈቃድ ሰጠንም አልሰጠንም ሊገናኘን ይችላል፡፡ በመሰረቱ ' የእግዚአብሔርም የሰይጣንም አይደለሁም' የሚባል ንግግር ከቀልድ አይተናነስም፡፡ ሰይጣን መንገድን ያግኝ እነጂ ፈቃድ አይጠብቅም፡፡ ለሰይጣን ካለመሆን የእግዚአብሔር አለመሆን ይቀላልና፡፡

ጣኦታት ጉልበት አላቸውዛሬ ደሞ ምን ልትል ነው? ልትሉኝ ይሆናል። "አምላካቸው አይን አለው አያይም.... " የሚል መዝሙር አለና እሱን እየዘመርኩኝ እራሴን ጥያቄ ጠየኩ። "ታዲያ ሰው እንዴት...
23/11/2021

ጣኦታት ጉልበት አላቸው

ዛሬ ደሞ ምን ልትል ነው? ልትሉኝ ይሆናል። "አምላካቸው አይን አለው አያይም.... " የሚል መዝሙር አለና እሱን እየዘመርኩኝ እራሴን ጥያቄ ጠየኩ። "ታዲያ ሰው እንዴት ደረቅ እጅ ስራ ከጥንት ጀምሮ ያመልካል?.." መልሱ ግን ቀላል ነበር። ምክንያቱም እጅ ስራው አምላኩ ይመልስለታል። ይሄንን ስታዩ መቼስ እንዴዴ... ብላችሁ ፊታችሁን ኮስተር አርጋችሁ ይሆናል። ግን እውነት ነው።
♦ የውላችሁ ሰይጣን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ተጣላና ራቅ እንጂ በማንምም ሆነ በምንም እንጨት ስም ለምን የሚከፈለውን ከፍሎ ያደርግልሃል። የመለሰልኝ እንጨቱ ነው በልና እንጨቱ አርገው ያንተ እሳቤ ነው ግን እሱ ግድ የለበትም። ሀሳቡ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ማራቅ እንጂ ተከታይ ማፍራት አይደለም። ሰለዚህ ጣኦታትየማድረግ ሐይል አላቸው። ምክንያቱም እነሱ እንዳረጉት አስመስሎ የሚያደርግ የሰይጣን እጅ ከጀርባቸው ስላለ!

ሳይሞቱ ህይወቴ አበቃ ማለት ውሸት ነው። ህይወት ካበቃ ሰማይ ለምን ቀጣዩን ቀን መኖር ይፈቅዳል? •> ንጋትና ነገ ካለ ሁሌም አንድ እድል አለ።•> እኔ ተራ ሰው ነኝ ማለት እምላክ ተራ ሰራ...
08/10/2021

ሳይሞቱ ህይወቴ አበቃ ማለት ውሸት ነው። ህይወት ካበቃ ሰማይ ለምን ቀጣዩን ቀን መኖር ይፈቅዳል?
•> ንጋትና ነገ ካለ ሁሌም አንድ እድል አለ።
•> እኔ ተራ ሰው ነኝ ማለት እምላክ ተራ ሰራተኛ ነው ማለት ነው። አምላክ ተራን ነገር በቁም ነገር ጊዜ ሰጥቶ አይፈጥርም።
•> መሸብኝ ለሰው እንጂ ለአምላክ የለም። ባምላክ መልክ ለተፈጠረ ለማንምም ምሽት የልም።
•> ህይወት አንዴ ናት ማለት መዝናኛ ናት ማለት አይደለም። ምናልባትም የስራ ናት።
•> ጠላት ክልል ተቀምጦ ጤነኛ ነኝ ቀልድ ነው።
•> አለማወቅ እንደ ማወቅ ከተኮራበት አእምሮ ሀኪም የማይፈታው ህመም ላይ ነው።
•> እየሄድክ ነው እና እየኖርክ ነው ይለያያሉ። እነሱን ሚዳኛቸው የህይወት ራእይ ይባላል። ራእይ ከሌለህ መረን ነህ። መረን ከሆንክ መሪ የለህም ዘፈቀደ ነህ። አንተንና ፈረስንም ማንም እያሰረ ወደፈለገው ይጋልባል። ከፈረሱም ምትለየው በፀጉርና ሽእግር ብቻ ነው።

መርዶኪዮስ ሊሻን
If you like it Share it

03/10/2021

ነብይ በችግር ውስጥ ለችግሩ ችግር ሊሆን የተወለደ እንጂ ተጨማሪ ችግር ሊሆን የተወለደ አይደለም!

ሰይጣን ከሰው ይማራል•> ብዙ ሰዎች ሰይጣን ሲባል ሁል ጊዜ በሰው ጆሮና ልብ እየመጣ ክፉ ክፉ ወሬዎችን የሚመክርና ሰላምን የሚያሳጣን ነገር የሚናገር ይመስላቸዋል። በርግጥ ትክክል ናቸው። ነ...
10/08/2021

ሰይጣን ከሰው ይማራል

•> ብዙ ሰዎች ሰይጣን ሲባል ሁል ጊዜ በሰው ጆሮና ልብ እየመጣ ክፉ ክፉ ወሬዎችን የሚመክርና ሰላምን የሚያሳጣን ነገር የሚናገር ይመስላቸዋል። በርግጥ ትክክል ናቸው። ነገር ግን ያንን ክፉ ነገር ከነሱ እንደተማረው አያውቁም።
* በመሰረቱ ሰይጣን የራሱ የሆነ እውቀት፣ ማንነት፣ ሀብት፣ አካል፣ ምናምን የሚባል ነገር የለውም። መረሳት የሌለበት ነገር ጨለማ ሲባል ወደ አእምሯችን ብቅ የሚለው ሰይጣን ቀድሞ የታላቅ ብርሃን ምሳሌ የአጥቢያ ኮከብ እግዚአብሔርን እስኪመስል ድረስ የትልቅነት ጥግ ነበር። አሁን የሚነሮው የጨለማና የወረደ ኑሮ መርጦት የሚኖረው ህይወት ሳይሆን አማራጭ አቶ የሚኖረው ኑሮ ነው። በስሩም የእልፍ ሲሶ እልፍ ነውና አብረውት የወደቁ እልፍ መላእክት አሉት።
•> በተቃራኒው የሰው ልጅ በአምላክ አምሳል የተፈጠረ፤ አምላኩ አባት የሆነው ከእውቀቱ ያካፈለው ፍጡር ነው። በተፈጥሮው አዋቂ (Intellect) የሆነ ነው። በፍጥረት ጊዜ እንኳን እግዚአብሔር አንበሳን አንበሳ ካለው በኋላ የአዳምን አእምሮ ለማየት ወደሱ ሲያመጣው አዳምም ያንኑ ነው የደገመለት።
*እንዲሁም ሰውን ሰው ያደረገው ምርጫው ነው። ምርጫ ያሌለው ሰው ከእንስሳ አይለይም። አዳምን አዳም ያስባለችው በገነት ያለችው ክፉዋ ዛፍ ነች። ሁሉ ነገር የተመረጠለትና የተመረጠለትን ብቻ ሚኖር ሰው እስረኛ ነው።
** የሰይጣን በሰው ላይ ያለው አስተዋጾ ግፊትና እገታ ነው። አማረኛ የሚያወራ ሰው ውስጥ ቻይነኛ የሚያወራ ሰይጣን የለም። ምክንያቱም በሰው ውስጥ ያለው ሰይጣን ከሰው አእምሮ ውስጥ አማረኛ ይማራል። በሰው ውስጥ ክፉም መልካምም ትምህርቶች አሉ። እነሱንም ከዛው አእምሮ ይማራል። መልካሞቹ ግን ድሮ ትቷቸው የወድቀው ትምህርቶች ስለሆኑ ሊረዳቸው አይችልም። ሰለዚህ ክፉዎቹን እውቀቶች እንዲተገበሩ ይገፋፋል። የትኛውም ሰይጣን ያደረበት ሰው ቀድሞ የማያውቀውንና ያልተማረውን ወሬ አይናገርም። የትኛውም የቀለም ት/ት ያልተማረ ሰው ሳይንሳዊ ተንኮል አያስብም። የበታችነትን ስሜት ያለበትን ሰው እሱኑ ያጎለብትለታል እንጂ ክፉ ስልጣናዊና ትዕቢተኛ ስሜትና ማንነት አይሰጠውም። ምክንያቱም ሰይጣን የሚተገብረውንና የሚያስተገብረውን ክፉ ሁሉ ከሰው ይማራል።

በመርዶኪዮስ ሊሻን.

አስፈላጊነት•••☞ በአለማችን በተፈጥሮው ፍጥነት ማንነቱ ያደረገው አቦ ሸማኔ (chitah) ነው። የትኛውም እንስሳ ሮጦ አያመልጠውም፡፡ ይህንንም ፍጥነቱን ተጠቅሞ የሚፈልገውን አድኖ ይበላል።...
12/05/2020

አስፈላጊነት•••

☞ በአለማችን በተፈጥሮው ፍጥነት ማንነቱ ያደረገው አቦ ሸማኔ (chitah) ነው። የትኛውም እንስሳ ሮጦ አያመልጠውም፡፡ ይህንንም ፍጥነቱን ተጠቅሞ የሚፈልገውን አድኖ ይበላል። ይህ ማንም ጋር የሌለ የተፈጥሮው ችሎታው ነው።

✍ ነገር ግን ስለዚህ እንስሳ የሚገርመው እውነት ከፍጥነቱ በላይ እርጋታው ነው። ስለ እርጋታው ደግሞ አንድ ቦታ ከተቀመጠ ሳይገላበጥና ሳይንቀሰቀስ ለ 8:00 መቀመጥ ይችላል። ይህ ማለት እሱ ፍጥነት ስላለው ሁል ጊዜ አይሮጥም። ሲረጋጋ ለረጅም ጊዜ ነው፡፡

★ በህይወታችን "የሚጠቅም" እና "የሚያስፈልግ" የሚባሉ ቃላቶችን መዘንጋት የለብንም፡፡ ይጠቅሙናል ብለን የምናሳድዳቸውን 'በጊዜው ያስፈልጋሉ?' ብሎ መጠየቅ ዋነኛ ነገር ነው፡፡ የቻልናቸውን ነገሮች ሁሉ የምናደርጋቸው ከሆነ ወደ ማንችለው ረመጥ ውስጥ ይከቱናል፡፡ ስለዚህ የቻልነውና የሚጠቅመን ነገር ሁሉ አያስፈልገንም!

ዘይት☞ ስለ ዘይት አስባችሁ ታውቃላችሁ? በመጽሐፍ ዘይት የቅባቱ የፀጋው መገለጫ የመንፈሱ ማረፊያ ትልቅ የህይወት ምሳሌ ነው። ✍  እኔን ግን የገረመኝ ዘይት ከእሳት ጋር ያለው ቁርኝት ነው።...
21/02/2020

ዘይት

☞ ስለ ዘይት አስባችሁ ታውቃላችሁ? በመጽሐፍ ዘይት የቅባቱ የፀጋው መገለጫ የመንፈሱ ማረፊያ ትልቅ የህይወት ምሳሌ ነው።

✍ እኔን ግን የገረመኝ ዘይት ከእሳት ጋር ያለው ቁርኝት ነው። ውሃ እሳት ከተጣደ ከጥቂት ጊዜ በሗላ እሳት በስሩ በኖሩን ሲያውቅ መንጫጫት ይጀመራል። አስከቻለው እየተንጫጫ ቀስ በቀስ አየተነነ አልቆ ይጠፋል። ዘይት ግን ከመርጋቱ ይላቀቅነና ይቀልጣል። ከወዝ አልባነት ወደ ማብረቅረቅ ይሸጋገራል። ድንገት ከተደፋ ሊሮጥ ቀልጦ ውሃ እስከሚሆን ይጠብቃል። በዚ ሁሉ ግን ምንም ያክል የእሳት ሙቀት ቢለቀቅበት ትንፍሽ አይልም። ከመጠኑም ምንም አይጎድልም። ምክኒያቱም እሳት ሐይሉ ነው። እሳቱ በጠፋ እንኳን ቶሎ የማይበርድ አቅም አለው። በዚ ዝምታው ድክመት የመሰለው አንድ ጥቂት ነገር ዘው ቢል እንዳልበረ ሊሆን ውሃ ቢሆን ሊተን ስጋ ቢሆን ሊጠበስ: እንደ ድንገት አሱም ተፈናጥሮ ሰው እጅ ላይ ቢያርፍ በቃጠሎው አሳብዶ የማይጠፋ አሻራን ሊያስቀምጥ ትልቅ አቅም አለው። ውሃ ስንታጠብበት አጥቦን ሲያልፍ በቆይታዎች ሲደረቅ ዘይት ግን ሲቀመጥ ለረጅም ጊዜ ሊያወዛን ከላይ አልፎ ውስጥን ሊያርስ አቅም አለው። ምክኒያቱም ዘይት ነው።

✍ በህይወታችን ከውሃነት ይልቅ የዘይትነት ባህሪ ካለን ሊያጠፋን የመጣው እሳትና መከራ ሐይላችን ነው፡፡ አሳቱ ቢበዛ በእሳቱ ጉልበታችንን እናድሳለን እንጂ አናማርርም አንጫጫም። በዛም የእሳት ብዛት ሃይል አግኝተን ስንወጣ ለጠላታችን ቃጠሎ ልንሆን ውሃ ውሃ የሚልን ነገር ልናተን; ጥሬ የሆነውም ጣዕም ሰተን ልናበስል አቅም አለን በእንቀስቃሴያችን ለብዙዎች ድርቀት ወዝ እንሆናለን።
ውሃ ከመሆን ዘይትነት ይሻላል። በደረሰብን የህይወት መከራ ተንጫጭቶና ተኖ ከማለፍ ከእሳቱ ሀይልን ተቀብሎ ድምጽን አጥፍቶ ዘላቂ ጉልበት መሆንን እንምረጥ!!

01/02/2020

የይሁዳ ማንነት•••

☞ ይሁዳ ደቀ-መዝሙር ያደረገው ጥረቱ አይደለም፡፡ መልካም ስብዕናውም አይደለም፡፡ ግን ይሁዳ ተወደደም ተጠላም ከእየሱስ ጋር ካሳለፋ አስራ ሁለት ምርጦች አንዱ ነው፡፡ ምናለፋን ይሁዳ የእየሱስ የምህረት ጥግ ማሳያ ነው፡፡
✍ እኔ እየሱስን ብሆን እራት ስንበላ "ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል፡፡ ስለዚህ ጴጥሮስ ያንን ሰይፍ አቀብለኝ፡፡ " እል ነበር፡፡ ወይም ሊስመኝ ሲመጣ የሆዱን ከበሮ አናጋለት ነበር፡፡ ግን ደስ ይላል ፡፡ ምክንያቱም ሰውዬው እኔ ሳልሆን ክርስቶስ ነው፡፡

☞ ይሁዳ ብር ይወዳል፡፡ ግን የብር ጌታ ሆኖ በማይረባ ብር የተሸጠው ክርስቶስ አላጠፋውም፡፡ የማይረባው ብር እንጂ..

★ በህወታችን አጥፍተናቸው ስቃይን የቀመስንባቸው ነገሮች እመኑኝ ያሰቃዩን እራሳቸው ነገሮቹ ዕንጂ ጌታ አይደለም፡፡ ከተፀፀትንም በራሳችን ይሁን።

★የዘላለም ምህረት እኮ ላጠፋ እንጂ ለጨዋው አይደለም፡፡ ስለዚህ በቀጣዩ ጌታ ሳይሆን ጥፋታችን እንዳያሸን፡፡

ስካር•••✍ ብዙ ሰዎችን ይዤ "ለምን በገዛ ዕጃችሁ ሰካራም ትሆናላችሁ?.." ስላቸው አንዳንዶቹ "..አኔ ለመስከር አልጠጣም፡፡ " ይሉኛል፡፡ ታዲያ ለምን ይጠጣሉ?. ★ መጽሐፍ መጠጥን " እ...
28/01/2020

ስካር•••

✍ ብዙ ሰዎችን ይዤ "ለምን በገዛ ዕጃችሁ ሰካራም ትሆናላችሁ?.." ስላቸው አንዳንዶቹ "..አኔ ለመስከር አልጠጣም፡፡ " ይሉኛል፡፡ ታዲያ ለምን ይጠጣሉ?.
★ መጽሐፍ መጠጥን " እባብ! " ይለዋል፡፡ ምክንያቱም እባብ ልስላሴው እና ማንነቱ አንድ ስላልሆነ ነው፡፡ ብዙ ሰዎችም መጠጥን ለመደገፍ ጥቅስ ይጠቅሳሉ፡፡ ለነገሩ እባብም ጠቅሶ የለ?..

♦ እና ወደዋናው ስመጣ ስካር ምንድነው?.. እንዴትስ ይፈጠራል?.. ሳይንስ ስለዚህ ብዙ ቢያቅም ስፖንሰሩን ብዙ ብሎ መጉዳት አይፈልግም፡፡ የሰው ልጅ አይምሮ በውስጡ ጥልቅና ውስብስብ ነገሮች አሉት፡፡ ወደ 86 billion ኒውሮኖች በትሪሊየን የሚቆጠር ውስብስብ ግንኙነቶች ታግዘው በ2.5 petabyte ሚሞሪ ተደግፈው ስራቸውን ያከናውናሉ፡፡ የምናስበውና የምንወስነው የምናስታውሰውም በዚህ ምክኒያት ነው፡፡ መጠጥ ትልቁ ስራው ወደ አይምሯችን ገብቶ እነዚህን ግንኙነቶች መበጣጠስ ነው፡፡
የእያንዳንዱ የስካር ባህሪ እይምሮው ላይ እንደደረሰው የመበጣጠስ ህመም ይወሰናል፡፡ የሰው ልጅ የማመዛዘንና የማሰብ ችሎታውን ክፍል ሲበጣጠስ ሌላ ስሜት የተሰማው ይመስለዋል፡፡ አንዳንዱ የደስታው ማመዛዘኛ ክፍል ሲበጣጠስ ያለምክኒያት ያለቅሳል፡፡ የሀዘኑም ሲበጠስ ያለምንም ምክኒያት ይስቃል፡፡ የአካል ክፍል ማመዛዘኛ መበጠስ ሲጀምርም መንገዳገድ ይጀምራል፡፡ ብዙዎች ሃዘን ለመርሳት ሲጠጡ ማመዛዘኛቸውን ይበጥሰዋል ዕንጂ አያስረሳቸውም፡፡
በነጋታው ስካሩ አልቆ ሲነሳ ሀይለኛ የራስምታትና የተለያዩ የህመም ስሜቶች (Hangover) ያስተናግዳል፡፡ ይህም የተበጣጠሱት ሊቀጠሉ ሲሄዱ የሚከሰት ነው፡፡በቀጣይም እየተደገመ ሲመጣ እየተላመደ ይመጣል፡፡ ጭራሽ የአይምሮ ክፍል እሱን መፈለግ ይመጣል፡፡ አስተሳሰብም እየተዳከመ ይመጣል፡፡ አወራር እየተለወጠ አይምሮ እየደከመ ይሄዳል...

☞ ታዲያ ይህ ጤነኛነት ነው?.. እግዚአብሔር ሰውን ከእንሰሳት የሚለየውን የአካል ክፍል ጎድቶ መልሶ የእንስሳ ማስመሰል ጥፋት አይሆንም?.. ጳውሎስ ጢሞቲዎስን ሲነግረው በአውዱ " ለሆድ ህመም ብለህ አስታከህ መጠጣት ከፈለክ ጠጣ፡፡ ግን ሐጢአትህ ተደብቆ አይቀርም ይወጣል.." እያለው ነበር፡፡ ክፍሉን ደጋግማችሁ አንብቡት...
.. ይቀጥላል...

13/01/2020

ባለ ራዕይ ወይስ ሕልመኛ •••

✍ ሕልምና ራዕይ በአብዛሃኛው በሰዎች ዘንድ ልዩነቱ ሊገባ ያልቻለ ጉዳይ ነው። አንዳንዶች ጭራሽ ልዩነት የለውም ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ አለው ግን የሰፋ አይደለም። በኔ በኩል ግን ልዩነት አለው። የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም እይታ መሆናቸው ነው።
★ ሕልም ፦ እይታ ቢሆንም ከብዙ የህይወት ትምህርት ልምድ እና ተሞክሮ አንጻር ልታየው የምትችለው እይታ ነው።
★ ራዕይ ፦ ደግሞ ከምንም ልምድና ተሞክሮ የማይነሳ አንተ ብቻ ልታየው የምትችለው እንደሚሆን በግልህ እርግጠኛ የሆንክበት ነገር ግን ለሌሎች ብትነግራቸው ባብዛኛውን ሊገባቸው የማይችል ምናልባትም እንደሞኝ ሊያስቆጥርህ የሚችል እይታ ነው። ራዕይ ከሌለህ መሪ የሌለው መጽሐፍ እንደሚለው መረን ትሆናለህ። ለምን እንደምትኖር ግራ ይገባህ መኖርህ ጭምር ሊያስጠላህ ይችላል።
ባብዛኛው ጊዜ ትልልቅ ራዕይ የሚታያቸው ሰዎች መሪዎች የሆኑ ናቸው።
☞ መጽሐፍ ቅዱስ የሁለቱን ልዩነት ሲያስረዳ "... ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ "
(ትንቢተ ኢዮኤል 2:28)

08/01/2020

የአብ አንድ ልጅ •••

~>ቁጥር መጀመሪያ አለው ማለቂያ ግን ሊኖረው አይችልም። አንድ የቁጥር መጀመሪያ ነው። ነገር ግን አንድ ለብዙ ሰዎች ጥቂት ነው። ላስተዋሉት ግን ከአንድ ውጪ ሁለት የለም። ምክንያቱም ከአንድ ወደ ሁለት ለመሻገር ዜሮ ነጥብ ተብሎ (0.1, 0.01, 0.001, 0.0001 ...) እልፍ ቁጥሮች አሉ አያልቁም። ስለዚህ አንሰው እልፍ እየሆኑ ስለሚመጡ ህግ ጥሰን እንጂ ወደ ሁለት መሻገር አንችልም። አብ አንድ ልጅ አለው በሱ ውስጥም እልፍ ልጆች አሉት። ለኛ ልጁ ለተሰጠነ ደግሞ በአንድ በልጁ እልፍ ፍቅር እልፍ በረከት እልፍ ህይወት አለን። አንድ ማለት እልፍ ነው። አንድ አያልቅም አንድ መጀመሪየም መጨረሻም ነው። ስለዚህ አንዱ ከበቂ ያልፋል!!

08/01/2020

°°°እውነትና ትክክል°°°


☞ እውነት የሚለው ሐሳብ ብዙ አዋቂዎችንና ተመራማሪዎችን ያወዛገበና ያመራመረ ጉዳይ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ እየሱስ በንግግሩ "እውነት እውነት" እያለ ሲናገር እናየዋለን። ጲላጦስ ግን እውነት ምንድን ነው ሲለው በዝምታ እንዳለፈውም እናውቃለን። አንዳንድ ኮሜዲያን የሆኑ ተመራማሪዎች እየሱስ መልስ ያልመለሰለት መልሱን ስለማያውቀው ነው ብለው ካንገት በላይ ፈገግ የሚያስብሉም አልጠፉም። በርግጥ ስለእውነት ሙሉውን ማለት ባይቻልም ግን በጥቂቱ እውነት ሁልጊዜ ትክክለኝነት ማለት አይደለም። ስለእውነት ጨርሶ መግለጥ ያልተቻለው በጣም ጥልቅ የሆነ ሀሳብ፣ በአራት ፊደል የተቀመጠ ብዙ ትርጉም ድርጊትና ሚስጥር በአጠቃላይ እውነት ክርስቶስ ስለሆነ ነው። እውነትን ላስተዋለ ዝምታው ያወራል። አንደበት አይፈልግም። ለጲላጦስ ጥያቄ መልሱ ዝም ብሎ ፊቱ የቆመ እውነት ነበር። በጥያቄው "ማነው" ቢለው አካል ነውና ይነግረው ነበር ። ነገር ግን "ምንድነው" ብሎ እንደ ግኡዝ ቆጥሮ ጠይቋልና ለተሳሳተ ጥያቄው መልሱ እንደ ግኡዝ ዝምታ ነበር።

✍......ይቀጥላል...

Address

Somewhere
Addis Ababa

Telephone

0902601278

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gospel Realm posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category