ETHIO News update

ETHIO News update We talk about True Ethiopian.

25/07/2025

ትራምፕ እንዴት ይመን አፍርካዊያን ጥቅማቸዉን ሲሸጡ እንጂ እንዲህ አይነት ግዙፍ ግድብ ሰርተዉ አያቁም።

25/07/2025

ለግንዛቤ ይሁን ይነበብ!.

የኢትዮጵያ ህዝብ ህዳሴ በአሜሪካ ገንዘብ ነዉ የተሰራዉ ትራንፕ ሲል አለመቃወሙ ገርሞኛል።እዉነት ነዉ አፍሪካዊያን ይህን የሚያክል ፕሮጀከት ሲሰሩ ያለ ብድርና ያለ ድጋፍ ሰርተዉ አሳይተዉ ስለማይታወቅ፣በአለማቀፍ ህብረተሰብ የአሜሪካን ትዛዝ ጥሳ፣የአይ ኤም ኤፍን ጫና፣አረብ ሊግ፣የአለም ህብረትና ብዙ ጫናዎችን ችላ በማሳካቷ፣እንዳይመረቅ ቀድማ ህዝብና መንግስት መካከል መተማመን በማሳጣት ግድቡ ሳይመረቅ ሀገር እንዲረበሽ ነዉ።ከዚያም የጋዛን ህብረተሰብ ለግብፅ ዉለታ ዉላ ልታሰፍር አስባ ነዉ።
ወገን አርቃችሁ አስቡ ፖለቲካ ሌላ የሀገር ጥቅም ሌላ ነዉ ወገን።
ግን እንደ ትራንፕ ባለ ጥሬ ሀብቷን አፍሪካ አብሮ ከመስራት ይልቅ ንቀትን የሚያሳዩና ዘረኛ ሆነዉ ቅድሚያ ለሰዉ ሳይሆን ለድንበር ብለዉ ከብዙ ማህበራት አሜሪካን ባወጡና የአሜሪካን የበላይነትን በአለም ጥርጣሬ ዉስጥ በሚያስገባ ሰዉ አሜሪካን መመራቷ በጣም ያሳዝናል።
ኢትዮጵያ ትችላለች ፣አፍሪካ ትችላለች፣
ያለማንም ድጋፍና ብድር ወደፊት ከህዳሴ የበለጠ ፕሮጀክት ታሳካለች!!!ሰላም ለሀገሬ፣ሰላም ኤአህጉሬ፣ሰላም ለአለም ህዝብ!!!!

09/07/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mebrat Kahsu, የፍቅር ጉዞ ማርያምን ይዞ, አሼ የማርያም ልጅ

02/04/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Netsa Yacob, ተሻለ ጎነሳሞ

13/01/2025

ልብ የሚነካ ታሪክ ያንብቡትና አስተያየት ይስጡ
***እናቴ አንድ እይን ብቻ ነው ያላት በዛም የመጣ
በጣም እጠላታለው::አባቴ...አ ባቴ ደሞ የአራስ
ቤት ልጅ እያለው ነው የሞተው እሱ ከሞተ በኋላ
እኔና እናቴ በደሳሳ ጎጆዋችን ከድህነትጋ መኖር
ጀመርን::አባዬ ያስቀመጠው ገንዘብ ሲያልቅ
እናቴ በራችንጋ ትንሽዬ ሱቅ ከፍታ
መስራትጀመረች እማ ለኔ የማታደርግልኝ ነገር
የለም እኔ ግን በሷ አፍር ነበር ትዝ ይለኛል 5ኛ
ክፍል የወላጆች ቀን እናቴ ትምህርት ቤት አበባ
ይዛልኝ መጣች "እንዴት እንዲ ታደርገኛለች?
ማን ነይልኝ አላት?" ተሸማቀኩ በጥላቻ አይን
ገልምጫት እየሮጥኩ አዳራሹን ለቅቄ ወጣው::
በሚቀጥለው ቀን ት/ቤት ስመጣ ጓደኞቼ"እናቱ
1 አይን ነው ያላት"እያሉ ሲያወሩ ሰማዋቸው
በውስጤ ምናለ እናቴ ከዚች አለም ብጠፋ ብዬ
ተመኘው እቤት ስደርስም "ደስይበልሽ በጓደኞቼ
አሳቅሽብኝ....ቆይ እንድ አይንሽ የት ሄዶነው?
ሁሌ እንዲ ከምታሸማቂኝ ለምን አትሞቺም?"
ብዬ ጮህኩባት ምንም መልስ ሳትሰጠኝ
ወጣች::እንዲ ማለቴ ስሜቴን ቢኮረኩረኝም
ለረጅም ጊዜ ልላት ያሰብኩትን በማለቴውስጤን
ቀለል አለኝ ብዙም ስሜትዋን የጎዳሁት አልመሰለኝምነበር ያን ቀን ማታ ከእንቅሌፌ ተነስቼ ውሃ ልጠጣ እቃ ቤትስገባ እናቴ እኔን ላለመቀስቀስ ቅስ ብላ
ስታለቅስ አገኘዋት ቅድም ባልኳት ነገር
እንደሆነ ገባኝ:: አሳዘነችኝ!ድምፄን ሰምታ ቀና ስትል ካንዱ
አይንዋየሚወርዱ እንባዎቿን እየዋቸው::አይንዋ
በእንባ ተሞልቶ ሳየውይበልጥኑ ጠላኋት! በዛው
ቅፅበት ለራሴ እንድ ነገር ቃል ገባው አድጌ
ስኬታማ ስሆን እንድ አይናማዋን እናቴን ጥያት
እንደምሄድ!
ከዛን ቀን ጀምሮ ጠንክሬ መማር ጀመርኩ
እናቴን ትቻት ወደ ከተማ በመሄድ አለ በሚባል
ዩንቨርስቲ ውስጥ ስኮላርሺፕ አግኝቼ በነፃ
ትምህርቴን ተከታትዬ ጨረስኩ ጥሩ ስራ
ያዝኩ፤የራሴን ቪላ ገዛው ሚስት
አግብቼምልጆች ወለድኩ::አሁን የተመኘሁትን
የልጅነት ህይወት እየኖርኩ እገኛለው::በጣም
ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ገንዘብ አለኝ፤ቆንጆ ቤት
አለኝ፤ደስተኛ ቤተሰብ አለኝ ከሁሉም በላይ ግን
የምጠላትን እናቴን የማላገኝበት ሩቅ ቦታ
ነውናየምኖረው ደስተኛ ነኝ:: አንድ ቀን ግን
ያላሰብኩት ዱብ እዳ መጣብኝ "ምን?!
ማነው ?!" እናቴ ነበረች ፀጉሮችዋ ሸብተው
ከስታና የተቀዳደዱ ቆሻሻ ልብሶች ለብሳ መጣች
ላምን አልቻልኩም ቤቴን እንዴት አወቀችው?!
ህፃንዋ ልጄ ፈርታት ሮጣ ወደቤት ገባች
እንዳላወቀ በመምሰል "ሴትዮ ምን ፈልገሽ
ነው?የሰው ቤት ዝም ተብሎ እይገባም እሺ ውጪልኝ ከቤቴ!!"አልኳት ኮስተር ብዬ እናቴ ደነገጠች "ይቅርታ ጌታዬ አድራሻ ተሳስቼ ነው" ብላኝ ወጣች.....ተመስገን አላወቀችኝም::ይህ ከሆን ካንድ ወር በኋላ ለድሮ ት/ቤቴ የመዋጮ
ፕሮግራም ተዘጋጅቶ የት/ ቤቱ ዳይሬክተር
ደውለው ጠሩኝና ሄድኩ ፕሮግራሙ ሲያልቅ
በዛውም ያደኩበት ቤት ምን እንደሚመስል
ለማየት ስሄድ እናቴ መሬት ላይ ተዘርራ
አገኘዋት::ሞታለች!! ምንም አላላቀስኩም::እጇ ላይ ወረቀትአየውና አንስቼ ማንበብ ጀመርኩ ለኔ የፃፈችው ደብዳቤ ነበር...እንዲህ ይላል "ውድ ልጄ,ካሁን በኋላ ሕይወት ማለትለኔ ምንም
አይደለችም::እንተ ወደምትኖርበት ከተማም
ተመልሼ አልመጣም::ልጄ ከምንም በላይ ግን
ናፍቆትህ ሊገድለኝ ነው ለምን አንድ አይን ብቻ
እንዳለኝ ጠይቀከኝ አልነገርኩክም ነበር
እውነታው ይህ ነው ልጄ.....ልጅ እያለክ ከባድ
የመኪና አደጋ ይደርስብክና አንድ አይንክ ይጠፋል እንደማንኛውም እናት ያለ አንድ አይን ስታድግ ማየት አልችልምና የኔን አይን አውጥተው ላንት እንዲያረጉልህ ዶክተሮቹን ጠይቄ ፈቃደኛ ሆነው አደረጉልህ...ለዚ ነዉ አለቺዉ።

13/01/2025

የማያልፍ የለም ታገስ!!

ሆድ ባሰኝኮ ወንድሜ ፍርዬ
29/12/2024

ሆድ ባሰኝኮ ወንድሜ ፍርዬ

27/12/2024

ኢትዮጵያ ከ84 በላይ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን አቅፋ ለኛ ትዉልድ የደረሰችን የጋራ መመኪያችንና በምድር ኑረን ስንሞትም መቀበሪያችን ናትና፣በፍቅር እንኑርባት

27/12/2024

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ የመወያያ ሀሳብ ዝርዝሪን ማቅረቡን ሰምተናል ሌሎችም እንዲዉ ያሳዉቃሉ ብለን እንጠብቃለለን።

25/12/2024

አብዛኞቻችን አሁን ባለንበት ከማንኛዉም ፖለቲካ ዉጪ ብንሆንም ስለዚች ሀገራችን የጋራ ሐላፊነት አለብን።እኔ ኦሮሞ ሆኜ ኢትዮጵያዊ እንደሆንኩ፣አማራ ሁኜ ኢትዮጵያዊ እንደሆንኩ፣ትግሬ ሆኜ ኢትዮጵያዊ እንደሆንኩ እንዲሁም የሌሎችም ብሔር ተወላጆችም እንደዚዉ ኢትዮጵያ የምትባል የጋራ ሀገራችን ዉስጥ በፍቅር ልንኖርና ሀገራችንም ለልጆቻችን የማቆየት ግዴታ አለን።

17/12/2024
17/11/2023

Life is always...

Address

Addis Ababa
1110

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO News update posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ETHIO News update:

Share