MGT Online Market

MGT Online Market Optimistic

ሰላም ኤምጂቲ ኦንላይን ማርኬት ቤተሰቦች። ሰሞኑን በተደጋጋሚ ከሚደርሱኝ ጥያቄዎች ዋናወቹናቸው፣ "ሊንክዲን አካውንቴን ላከራይ?" የሚለው ነው። ለዚህ መልሱ እንደሚከተለው ነው። ምናልባት ለማ...
31/05/2025

ሰላም ኤምጂቲ ኦንላይን ማርኬት ቤተሰቦች። ሰሞኑን በተደጋጋሚ ከሚደርሱኝ ጥያቄዎች ዋናወቹናቸው፣ "ሊንክዲን አካውንቴን ላከራይ?" የሚለው ነው። ለዚህ መልሱ እንደሚከተለው ነው።

ምናልባት ለማታውቁ LinkedIn እንደሌላው አይነት የማህበራዊ ሚድያ (እንደነፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቴሌግራም ወይም ትዊተር/X) አይደለም። ተቋማት ማንነታቸውና ስራቸው በግልጽ ከሚታይበት፣ ቀጣሪዎች አስቀድመው ከሚያጣሯቸው መለኪያዎች አንዱ ሊንክዲን ነው። ቢዝነስ ካርድ፣ ፓስፖርት፣ መታወቂያ ወይም ሲቪ ልትሉት ትችላላችሁ። "አየለች_ቀበጧ_ከሸጎሌ" ወይም "የጨበራ ሰፈር ልጆች ሜም" የሚል ማንነት እዚህ አይሰራም። በየትኛውም ጊዜ ማንም ሰው ደጃችሁን አንኳኩቶ መምጣት የሚያስችለው ትክክለኛ መረጃ ነው ያለው። እና ይሄን የግል መረጃና ምስል የያዘ አካውንት፣ አይታችሁ ሰምታችሁት ለማታውቁት ሰው ለመስጠት መሞከር (ማሰቡ ራሱ) አደጋን ና ግባ በሞቴ ብሎ እንደመጋበዝ ይመስለኛል።

(የሚያጋጥሟችሁ አደጋዎች)

1. የ LinkedIn ደንቦችን መጣስ
አካውንትን ለሌላ ሰው መስጠት ከ LinkedIn ደንቦች ጋር በቀጥታ የሚጋጭ ነው። ይሄን ስታደርጉ ብትገኙ አካውንታችሁ ሊዘጋ ወይም ሊታገድ ይችላል — ዛሬን እንዳታዩ፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ብዙ የምታጧቸው እድሎች አሉ።

2. የስም መጥፋትና የወንጀል ተባባሪ መሆን
አካውንታችሁን የሚወስዱ ሰዎች በምን ስራ እንደተሰማሩ አታውቁም። ከናንተ ባህል እሴትና ሀይማኖት ውጪ የሆነ ድርጊትና የጥላቻ ንግግር፣ በቀጥታ በስማችሁና በምስላችሁ ተጠቅመው ሊያስተላልፉበት ይችላሉ። ሰሞኑን ግብረሰዶማዊ ምስሎችን ሲለጥፍ የነበረውን ልጅ ልብ ይሏል።

3. ሕጋዊ ቅጣት
ቅድም እንዳልኳችሁ። በዚያ አካውንት ወንጀል ከተሰራ ቤታችሁ ድረስ የሚያደርስ መረጃ ስላለ በወንጀል ተጠያቂ ልትሆኑ ትችላላችሁ።

ስለዚህ በአጭሩ "አልፈልግም፤አመሰግናለሁ" ብሎ መመለስ ከባሰም ለLinkedIn ሪፖርት ማድረግ ትችላላችሁ። በተጨማሪም ባለሁለት-ደረጃ ቬሪፊኬሽን (2FA) በመጠቀም የበለጠ ሊንክዲናችሁን ጠብቁ።

ምንጭ ትማርኢትዮጵያ

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Md Kabir, Mengesha Getahun, Timrolagi Bachako Ma, Saleh R...
31/05/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Md Kabir, Mengesha Getahun, Timrolagi Bachako Ma, Saleh Ramadan, ገብርኤል አባቴ

ማዕከላዊ ባንክ ባንኮች የማገገሚያ እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አወጣየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ከባድ የገንዘብ ችግር ሲያጋጥማቸው ራሳቸውን እንዲያገግሙ የሚያስችል ዝር...
25/05/2025

ማዕከላዊ ባንክ ባንኮች የማገገሚያ እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አወጣ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ከባድ የገንዘብ ችግር ሲያጋጥማቸው ራሳቸውን እንዲያገግሙ የሚያስችል ዝርዝር እቅድ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ ቁጥር SBB/93/2025 አውጥቷል። ይህ መመሪያ የባንኮችን የገንዘብ መረጋጋት ለማረጋገጥ እና ቀውስ ከመከሰቱ በፊት ዝግጁ እንዲሆኑ ለመርዳት ያለመ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት፣ ሁሉም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ባንኮች አጠቃላይ እና አስተማማኝ የማገገሚያ እቅድ ማዘጋጀት አለባቸው። ይህ እቅድ አስፈጻሚ ማጠቃለያ፣ ስትራቴጂካዊና የአመራር ትንተና፣ የማገገሚያ አማራጮችን፣ የአሰራር የአደጋ ጊዜ እቅድ እንዲሁም የግንኙነትና ይፋ የማድረግ እቅድን ማካተት ይኖርበታል።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ዓላማ ባንኮች የገንዘብ ቀውስ ሲገጥማቸው ከብሔራዊ ባንክ ወይም ከመንግስት ልዩ ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው የማገገም አቅም እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ገልጿል።

ካፒታል ከመመሪያው እንደተመለከተው ፣ ባንኮች በቂ እና የተለያዩ የማገገሚያ አማራጮችን ማካተት አለባቸው። እነዚህ አማራጮች የካፒታል እና ስጋትን መቀነስ፣ በቂና የተለያየ የገንዘብ ምንጮችን ማግኘት፣ እንዲሁም እዳዎችን እንደገና ማዋቀርን የመሳሰሉ እርምጃዎችን ያካትታሉ።

ባንኮች ከብሔራዊ ባንክ ያልተለመደ የፖሊሲ ጣልቃ ገብነት ወይም ከመንግስት የገንዘብ ድጋፍ እንደማይጠበቅባቸው ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

የማገገሚያ እቅዱ በባንኩ የውስጥ ኦዲት፣ ስጋት እና ተገዢነት ክፍሎች ከተገመገመ በኋላ በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ መጽደቅ እንዳለበት መመሪያው ይደነግጋል። የውጭ ባንኮች ቅርንጫፎች ከሆኑ ደግሞ በዋናው ወይም በአለም አቀፉ ዋና መስሪያ ቤት መጽደቅ እንዳለበት ያስገድዳል።

ባንኮች የማገገሚያ አመልካቾችን በመጣስ በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለብሔራዊ ባንክ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም፣ ባንኮች እቅዳቸው ውጤታማ መሆኑን ለመፈተሽ የተለያዩ የወደፊት ሁኔታዎችን ገለፃ ማካሄድ ይኖርባቸዋል።

ይህ መመሪያ ባንኮች የመጀመርያውን የማገገሚያ እቅዳቸውን ከመመሪያው ተፈጻሚነት ቀን ጀምሮ በስምንት ወራት ውስጥ ለብሔራዊ ባንክ እንዲያስገቡ ያዛል። ከዚያ በኋላም በየሶስት ወሩ የዘመነ እቅድ ማቅረብ አለባቸው። መመሪያውን ባለማክበር ላይ የገንዘብ ቅጣቶች እስከ 100 ሺህ ብር ተጥለዋል።

በኢያሱ ዘካሪያ

25/05/2025

#ምክር የኦንላይን ስራ
ባጭሩ የምነግራችሁ የኦንላይን ስራ ወይም የኢንተርኔት ስራ ከፈለጋችሁ በመጀመርያ Skill ሊኖራችሁ ይገባል። ያንን Skill በመሸጥ ገንዘብ ታገኛላችሁ። በተለይ Digital Skill ተፈላጊ ነው። ለዚህ Fiver እና Upwork እንዲሁም Freelancer ዋና ተጠቃሽ ፕላትፎርሞች ናቸው። ከዛ ውጪ የኦንላይን ስራ የሚሰራው በግል ማስታወቂያ በመልቀቅ ለአገልግሎት ፈላጊዎች ተገቢ ዋጋ እያስከፈሉ መስራት ነው። ሌላው Content Creator በመሆን በYouTube እና TikTok ላይ ጠቃሚ ቪድዮዎችን በመልቀቅ መስራት ነው። ከእነዚህ ውጪ ሌላ የኦንላይን ስራ የለም። በተለይ invest አድርጋችሁ ምናምን የሚሉት 99.99% Scammers (አታላዮች) ናቸው። ኢንቨስት አድርጋችሁ የምትሰሩት ትልቁ ቦታ Trading ነው። እሱም ዕውቀት ይጠይቃል። ዘው ተብሎ አይገባበትም። ስለዚህ ነፃ ገንዘብ አትጠብቁ። ይልቁንስ Content Creator ሁኑና ዛሬውኑ ጥሩ Niche መርጣችሁ YouTube እና TikTok ላይ ጀምሩ።
፧፧ ምክሬ ነው —

15/05/2025
ዓለም ላይ ያለው ችግር ተፈጥሮዊ ነው:: የአትዮጵያ ቺግር ሰው ሰራሽ ነው!?ስለዚህ ጊዜ እስኪፈታው መታገስ ነው ::
15/05/2025

ዓለም ላይ ያለው ችግር ተፈጥሮዊ ነው:: የአትዮጵያ ቺግር ሰው ሰራሽ ነው!?
ስለዚህ ጊዜ እስኪፈታው መታገስ ነው ::

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913212792

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MGT Online Market posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to MGT Online Market:

Share