Yekidanemihret lejoch

Yekidanemihret lejoch የመንግስቱ ወራሾች

09/05/2025
09/05/2025

✅☦️ #ምድር #እንግዳ #ልደትን #ዛሬ #አስተናገደች ☦️✅
(እንኳን ለቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የልደት በዓል አደረሳችሁ!)

☦️

¹✍️ያለበደል ያለነውር የሆነች ልዩ ማንነት ያላት ልደት ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ተከናወነች! (መኃ 4:7)::

☦️

²✍️ያለበደል በገነት የነበሩትን የአዳምንና የሄዋንን ማንነት የያዘች ሴት ዛሬ በምድር ተወለደች! (ዮሐ 2:4)::

☦️

³✍️አምላክ ሰው ሆኖ የሚገለጥባት የድንግል ልዩ አካል ዛሬ ተገለጠች! የተዋህዶ ልዩ አውድማ ዛሬ ተደለደለች:: (ማቴ 1:23)::

☦️

⁴✍️ለማንም የማይሰጥ እድል የተሰጠው እናትም ድንግልም የሚሆን የእመቤታችን አካል ዛሬ ተወለደ! (ኢሳ 7:14)(ምሳ 31:29)::

☦️

⁵✍️ኢየሱስ ክርስቶስን የምታፈራውን የሐዲስ ኪዳን አስኳል ዛሬ በተራራ ላይ አፈ'ሯ'ት: ከመልካም በላይ የሆነውን ፍሬ የምታፈራ መልካም ዛፍ ዛሬ በቀለች! (ማቴ 7:17)::

☦️

⁶✍️ የፀሐይ መውጫው ምስራቅ ዛሬ ወጣች! (ሚል 4:2) (ራዕ 12:1]::

☦️

⁷✍️ትውልድ የሆነ ሁሉ "ብፅእት ይላል" ብላ የትውልድነትን መስፈርት የምትነግረንን የሁላችን እናት ዛሬ እናቷ ወለደቻት! (ሉቃ 1:48)::

☦️

⁸✍️ዓለም ሁሉ: ፍጥረትም ሁሉ: ሰማያትም: በሰማያትም ያሉ ሁሉ ተደምረው በክብር ከራሷ ፀጉር አንዲቱን እንኳ የማያህሉ ክብርተ ክቡራን ንዕድተ ንዑዳን ዛሬ ተወለደች:: (አርጋኖን ዘእሁድ 2:3)::

☦️

⁹✍️የዓለምን እውነተኛ ብርሃን (ብርሃን ዘበአማንን) የምትወልድ የዓለም ብርሃን ዛሬ በራች (ዮሐ 8:12)(ማቴ 5:14)::

☦️

¹⁰✍️የባሕርያችን መመኪያ የፍጥረት ቅድስና ጥግ ዛሬ በሊባኖስ ተራራ ተገለጠች:: (ሉቃስ 1:28)(መኃልይ 4:8)::

☦️

ይህች የሁሉም እናት ይህች ልዩ ቅድስት ሁላችንም በእጆቿ ትባርከን! በእርሷ ልደት ውስጥ የጌታ ልደት አለ:: ጌታን ትወልድልን ዘንድ ያላት ተወለደችልን! ስለዚህ የልደቷ ቀን ልደታችን ነው:: መልካም በዓል!!

☦️

#አሜን!✅✅✅🌹✅✅✅
✅☦️ ፍ ቅ ረ ፍ ቅ ር ዘ ፍ ቅ ር ☦️✅

09/05/2025
09/05/2025
09/05/2025

#ለቅዱስ #ጊዮርጊስ #ሊቀ #ሰማዕታት #የተሠጠው #ቃል #ኪዳን

“እነሆ በዓለም ሁሉ ለሚጸልዩ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ ስምህን ከስሜ ጋር አንድ አደረግሁት፤ ከሥጋህ ቁራጭ ከልብስህ ቅዳጅ ለማግኘት የታደለውን፤ ስለ ስሜ በተቀበልከው መከራ የታመነውን ከመከራው ሁሉ አድነዋለሁ ብዬ በራሴ ማልኩ።

ወንድም ሴትም ቢሆኑ ቢታመሙ በመከራ ቢወድቁ ወደፍርድም ቢወጡ በጦር ሜዳ ወይም በወህኒ ቤት ቢሆኑ በባሕር በፈሳሽ ወንዝ ቢሆን በመንገድም ቢሆን በሽፍቶች እጅ ቢወድቁ አውሬ ቢያገኛቸው እሳት አደጋ ቢደርስባቸው ክፉ አሟሟት ቢገጥማቸው በችግር ላይ ሆነው እጅግ ተስፋ ቢቆርጡ ይልቁንም የሰዎች ልጆች በሚያዙበት በጽኑ መከራ ቢወድቁ በቅዱስ ስምህ ተማጥነው ሦስት ጊዜ አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ርዳን አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ርዳን አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ርዳን እያሉ ወደኔ ቢጮሁ ያን ጊዜ ራራላቸዋለሁ ፈጥኜም ለጸሎታቸው መልስ እሰጣቸዋለሁ ከልባቸው የለመኑኝን ሁሉ እፈጽምላቸዋለሁ ከመከራቸውም አድናቸዋለሁ።

ስለ ስሜ የተቀበልከውን መከራ ያገኘህን ድካም ገድልህን የሚናገረውን መጽሐፍ የሚጽፈውን ሁሉ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ። ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ በመንግሥተ ሰማያትም ያንተ ልጅ አደርገዋለሁ ለዘለዓለም በአንድነት ካንተ ጋራ አኖረዋለሁ። ለዘለዓለምም አልጥለውም በስምህ የተማጠነውን በሃይማኖት ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በስምህ የጠራውን እኔ እባርከዋለሁ ለዘለዓለም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ ልቡን ደስ አሰኘዋለሁ። በቦታው ሁሉ በቤተ ክርስቲያንህ ማኅበረ መላእክት እንዲያገለግሉ አደርጋለሁ። ለቤተ ክርስቲያንህ እጣን መብራት ስንዴ ወይን የሚሰጥ በስምህ ለተራበ የሚያበላ ለተጠማ የሚአጠጣ የከበረችውን የመታሰቢያህን ቀን የሚአከብረውን እኔ በዚህ ዓለም እረዳዋለሁ በሚመጣውም ዓለም ከአንተ ጋራ በመንግሥቴ ደስ እንዲለው አደርጋለሁ። በስምህ ለተራቆተ የሚያለብሰውን እኔ የክብር ልብስ አለብሰዋለሁ፤ ለቤተ ክርስቲያን በስምህ መብራት የሚያበራውን ዕጣን የሰጠውን መላእክት እንዲያበሩለት አደርጋለሁ ወደ እኔም ደስ ብሎት ይመጣል። በስምህ እንግዳ የሚቀበለውን እኔ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ለዘለዓለም በመንግሥቴ እቀበለዋለሁ። በስምህ ምጽዋት የመጸወተውን እኔ ከቅዱሳን ጋራ እቆጥራዋለሁ ከዚህ ዓለም ሀብትም ምንም እንዳያጣ አደርገዋለሁ። እኔ ፈጣሪህ እግዚአብሔር ነኝ ከአንደበቴ የወጣውን እፈጽማለሁ እንጂ አልለውጥም።”

ምንጭ ፦
ገድለ ጊዮርጊስ ግዕዝና አማርኛ ምዕራፍ 9 ቁጥር 4 – 6 ገጽ 63 – 64 ተስፋ ገብረ ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋ 1991ዓ.ም

#ሰላም #ለጊዮርጊስ ሰማዕት ፀሐየ ጽድቅ
ዘተአምሪሁ ከመ ኆፃ ባሕር
ዘኢይትኌለቍ ኮከበ ክብር
ዘማእከለ ሰማይ ወምድር
ዘአርአየ ኃይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር
ብእሲ አዛል ወመስተጋድል
ኃያል ዝኅዙኃ ገድል

በተጋድሎ ለጸና፣ ጎልማሳና ተጋዳይ ለሆነ፣ ጥንካሬውን በመንበር ሰሌዳ ላሳየ፣ በሰማይና በምድር መካከል እንደ ታላቅ ኮከብ ለሆነ፣ ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ ተቆጥሮ ለማያልቅና የእውነት ፀሐይ ለሚባል ሰማዕት ጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል።

-ከተአምኆ ቅዱሳን ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ዘሐሙስ)

👉"አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ" ዘዳ. 7፥9

09/05/2025
09/05/2025

“በማርያም ልደት ዛሬ ደስታ ሆነ” ቅዱስ ያሬድ
" ልደትሽ ልደታችን ነው "
🔔 የፀሎት መርሐ ግብር 🔔

🗓አርብ ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም
⌚️ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ
💒በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ

09/05/2025

Address

Ayer Tena
Addis Ababa
KIDANEMIHRETENATE

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251925171704

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yekidanemihret lejoch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category