27/03/2025
አሳዛኝ መረጃ!
ብርቱካን ተመስገን በተፈፀመባት ከባድ ድብደባ እራሷን መሳቷ ተሰማ!
ተበዳዩዋ ድብደባው የተፈፀመባት ከአገዛዙ አጋፊሪ ሚዲያዎች ተፅፎ የተሰጣትን በትክክል ሸምድዶ ለመናገር ባለመቻሏ ነው ተብሏል።
ብርቱካን ተመስገን ለእስር ከተዳረገችበት መጋቢት 16/2017 ዓ/ም ጀምሮ ከገላን የመጡ የፖሊስ አባላት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት በጋራ በመሆን እየተፈራረቁ "በብልፅግና ጎዳና ላይ ያለውን መንግስት ገፅታ ለማበላሸት ተልዕኮ ተሰጥቶሽ ነው" በሚል ባፍና ባፍንጫዋ ደም እስኪፈሳት ድረስ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመውባታል ተብሏል።
ብርቱካን ተመስገን የአገዛዙ ሚዲያዎች ላስተላለፉት ዘጋቢ ፊልም ቀረፃ እየተደረገች እንዳለ ሸምድዳ እንድትናገር ተፅፎ የተሰጣትን በትክክል ማለት ባለመቻሏ ቀረፃው በተደጋጋሚ ተቋርጦ እንደነበር ምንጮች ገልፀዋል።
"ቀረፃው ሲጀመር እምባ እየተናነቃት ተፅፎ የተሰጣትን በትክክል ካሜራ ፊት መናገር አልቻለችም ነበር" ሲሉ የተናገሩት ምንጮቻችን በዚህም ድብደባ ተፈፅሞባታል ብለዋል።
ተበዳዩዋ የደረሰባትን ግፍ ሳይሆን ተፅፎ የተሰጣትን ብቻ እንድናገር ሲያስገድዷት እምባዋን መቆጣጠር ባለመቻሏ የካሜራ ባለሙያዎቹ በቂ የሆነ ምስል መውሰድ እንዳልቻሉ የተጠቀሰ ሲሆን፡ አብዛኻኛው የዘጋቢ ፊልሙ ማልበሻ ቀደም ብለው ተዘጋጅተው በነበሩ ሀሰተኞ ዶክመንቶች እንዲሸፈን ተወስኗል ብለዋል።
በአማራነቷ የደረሰባትን ግፍና ሰቆቃ ለምን ለሚዲያ ተናገርሽ በሚል በፌደራል ፖሊስ ታፍና በእስር ላይ የምትገኘው ብርቱኳን በተፈፀመባት ድብደባ እራሷን እንደሳተች ነው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው።
ተበዳዩዋ ብርቱኳን ከባለስልጣናት በመጣ ትዕዛዝ በቂ ህክምና እንዳላገኘች የተነገረ ሲሆን፡ ህይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ምንጭ (መረብ ሚዲያ )