Soofam News Tube

  • Home
  • Soofam News Tube

Soofam News Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Soofam News Tube, Digital creator, akakikaliti, .

የ19ኝ ዓመቷ ሀሴትበአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የኬሚካል ኢንጂኔሪንግ ተማሪ የሆነችው ሀሴት ደረጄ፣ በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች ወጣት ነች። እሷም በዓለም አ...
01/06/2025

የ19ኝ ዓመቷ ሀሴት

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የኬሚካል ኢንጂኔሪንግ ተማሪ የሆነችው ሀሴት ደረጄ፣

በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች ወጣት ነች።

እሷም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት በዚህ ታላቅ የቁንጅና ውድድር የፍጻሜ ደረጃ የደረሰች ስትሆን፣

ኢትዮጵያ የት እንደምትገኝ ለማያውቁ በሩቅ ምስራቅ ለሚገኙ ሀገራት ኢትዮጵያን ከፍ ያደረገችና ስሟ በትልቁ መድረክ እንዲነሳ ያደረገች ጀግና ነች።

በመሆኑም ሀሴት ወደ ሀገሯ ስትመለስ፣ የሚመለከተው አካል የጀግና አቀባበል እንዲያደርግላት አጥብቀን በትህትና እንጠይቃለን።
FOLLOW
🇪🇹🇪🇹🇪🇹

FOLLOW
01/06/2025

FOLLOW

የኮሪደር ልማቱ Amnesty ኢንተርናትኦናል ክስ አቀረበበት‼️ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በከተሞች በሚያካሂደው የኮሪደር ልማት ሳቢያ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የግዳጅ መፈ...
11/05/2025

የኮሪደር ልማቱ Amnesty ኢንተርናትኦናል ክስ አቀረበበት‼️

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በከተሞች በሚያካሂደው የኮሪደር ልማት ሳቢያ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የግዳጅ መፈናቀልና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተመለከተ ሪፖርት በጋምቢያ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የሰብዓዊና ሰዎች መብቶች 83ኛ ጉባኤ ላይ ትናንት ማቅረቡን አስታውቋል።

የኮሪደር ልማቱ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ባሳደረው ተጽዕኖ ዙሪያ ጥልቅ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሮጀክቱን እንዲያቆም ኮሚሽኑ ጥሪ እንዲያደርግ አምነስቲ ጠይቋል።

ኢሄን ነገር ልብ ብላቹታል?ለመላው የከተማችን ነዋሪ ማህበረሰብ በሙሉ ከ ማክሰኞ ግንቦት 5 ፣ 2017 - ግንቦት 9 ፣ 2017 ዓም በከተማችን ባሉ የመንግስት ጤና ተቋማት ማለትም (ጤና ጣቢ...
10/05/2025

ኢሄን ነገር ልብ ብላቹታል?

ለመላው የከተማችን ነዋሪ ማህበረሰብ በሙሉ ከ ማክሰኞ
ግንቦት 5 ፣ 2017 - ግንቦት 9 ፣ 2017 ዓም በከተማችን ባሉ የመንግስት ጤና ተቋማት ማለትም (ጤና ጣቢያዎች ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ፣ ሪፈራል ሆስፒታሎች በሙሉ ) ከ ድንገተኛ ህክምና ውጪ አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑ ታውቆ በእነዚህ ቀናት የክትትል ቀጠሮ ወይም የቀዶ ህክምና ቀጠሮ ያላችሁ ይህንን በመገንዘብ ራሳችሁን ካላስፈላጊ መጉላላት እንድትጠብቁ እናሳስባለን ።

እስከ ግንቦት 9 ፣ 2017 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ ያሉ ጤና ባለሞያዎች በጋራ ላቀረብነው ጥያቄ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ካልሰጠን ከ ቅዳሜ ግንቦት 9 ፣ 2017 ዓ.ም በኋላ በየትኛውም የመንግስት የህክምና ተቋም ምንም አይነት የህክምና አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን ።

ለማገልገል_ ቃል_ አልገባንም!

ከጤና ባለሞያዎች በጋራ !

10/05/2025

ዛሬ የጤና ባለሟያዎችን ሰብስበዋቸው ነበር። የስብሰባው ውሎ ምን ይመስል እንደነበር ከአንድ ተሳታፊ የተላከን ምስክረንት
====================
ሰሞኑን በመንግስት የጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የሃገራችን የህክምና ባለሞያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ ተከትሎ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ በተለያዩ የዞን ከተሞችና ወረዳዎች ውስጥ መንግስት የህክምና ባለሞያዎችን ስብሰባ ጠርቶ በማወያየት ላይ ይገኛል። በምስራቅ ቦረና ዞን ነጌሌ ቦረና ከተማ በተደረገው ውይይት እንደተለመደው የዞኑ አመራሮች የህክምና ባለሞያዎቹ ያነሱትን የመብት ጥያቄዎች ተገቢና ወቅታዊ ያልሆነ፤ በሌሎች የተለያየ የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ኃይሎች ግፊት የመጣ አድርጎ በማቅረብ በማስፈራራት ለማዳፈን ሙከራ አድርገው ነበረ። እጅግ በሚያስገርም መልኩ የህክምና ባለሞያዎቹ reaction የሚገርም ነበረ! የህክምና ባለሞያዎቹ reaction የሚከተለው ነው

1. ቀን ከለሊት እራሳችንን ለአደጋ አጋልጠን እየለፋን እየሰራን በልቶ ማደር፣ ቤት ተከራይቶ መኖር፣ ልጆቻችንን ማስተማር የማያስችለንን እዚ ግባ የማይባል ደሞዝ እየተከፈለን ለእርዛትና ለችግር ተጋልጠናል።
2. በትክክለኛ ሊረጋገጥ የማይችል ታማኝነት የሌለው የትምህርት ደረጃና ማስረጃ ያላቸው ወይንም በግዢ የገዙ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከእነሱ ጋር በቅርበት የሚሰሩ በሌብነትና በዘረፋ የተሳሰሩ በመንግስት ቢሮክራሲው ውስጥ ያሉ አንዳንድ የመንግስት ሠራተኞች፡ የሚሠሩትን ቤት፣ የሚገዙትን መኪና፣ ያላቸውን የንግድ ድርጅት፣ የሚዝናኑበትን ቦታና የሚያወጡትን ወጪ እዚሁ አብረን ስለምንኖር እናውቃለን እናያለን። እኛ ወር ላይ ደሞዝ ተብሎ የሚከፈለንን እንዚህ አካላቶች አንድ ጫማ ሲገዙበት ወይንም አንድ መዝናኛ ላይ በቀላሉ ሲከፍሉት ወይንም ለልጆቻቸው መጫወቻ አሻጉሊት ሲገዙበት በአይናችን እያየን ነው። ይህ ሁሉ ባለበት ሁኔታ እንዴት ቢያንስ በልተን ማደር፣ ቤት ተከራይተን መኖር፣ ልጆቻችንን ማስተማር የሚያስችለንን በየጊዜው ቅጥ ባጣ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ያማከለ የደሞዝ ማስተካክያ ይደረግልን ብለን ፍትሃዊ ጥያቄ በመጠየቃችን ታስፈራሩናላቹ፣ ጥያቄዎቻችንን ወደ ሌላ አቅጣጫ ትጠመዝዛላችሁ

3. ለሃገሪቷ አጠቃላይ ኢኮኖሚ እዚ ግባ የሚባል አስተዋፆ የሌላቸው አንዳንድ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ በመካከለኛ የትምህርት ደረጃ የሰለጠኑ ተቀጣሪ ሠራተኞች አንድ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የህክምና ባለሞያ ምናልባትም እጅግ በጣም ጥቂቶች ብቻ በሰለጠኑበት ሞያ የሰለጠነ (specialization and sub-specialization) የሚያገኘውን ደሞዝ ሶስትና አራት እጥፍ ይከፈላቸዋል። ይህ ደግሞ አይን ያወጣ ኢፍትሃዊነት ነው፣ አድሎ ነው፣ ለሃገሪቷም ብሔራዊ ውርደት ነው።
ወዘተ .. ብዙ ብዙ ሌሎችም ጥያቄዎች ተነስተዋል።

ለተነሱት ጥያቄዎች አመራሩ አንድ ጥያቄውን ወደ ሌላ አቅጣጫ መጠመዘዝ ሁለት ደግሞ የሃገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታ አይፈቅድም ብለን ነው እንጂ እኛም የኑሮ ውድነቱ ችግር ውስጥ ከቶናል የደሞዝ ጥያቄ አለን። ስለዚህ ታገሱ የሚል መልስ ነው የሚመልሱት።

ስለዚህ በቀጣይ እነዚህ የዞንና የወረዳ አመራሮች ከተቻለም የክልል አመራሮች እንዲሁም ከእነሱ ጋር ተባብረው በቅርበት የሚሰሩ የጥቅም ተጋሪ መንግስት ሠራተኞች የሰሩትን እንዲሁም ሰርተው የሚያከራዩትን መኖሪያ ቤት (ቤቶች)፣ የንግድ ድርጅቶች፣ መዝናኛ ቦታ ለአንድ መዝናኛ የሚያወጡትንና የሚከፈሉትን ቢል በ photo፣ በ video እንዲሁም በሌሎች አማራጭ መንገዶቸ መረጃዎችን በመያዝና እስከ ስማቸው puplic በማድረግ ለህዝብ ማጋለጥ ያስፈልጋል። ይቻላልም ከታሰበበትም ቀላል ነው። በተጨማሪም ለምሳሌ በአንድ ዞን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሴክተር መስራቤቶች የፋይናስ ሲስተማቸው ያለው የዞኑ የፋይናስ ቢሮ ውስጥ ነው።የፋይናስ ቢሮ አይ ቢ ኤክስ የሚባል Application ስለሚጠቀም የእነዚህ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የፋይናስ መረጃቸው በሙሉ እዚህ አፕልኬሽን ውስጥ ነው ያለው። ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ የሚሰራ ተራ የ It ባለሞያ በዋነኛነት ስራው ከእዚህ Application ጋር ስለሆነ እነዚህን መረጃዎች በሙሉ Access ማድረግ ይችላል። ስለዚህ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎች የሚያወጡትን አበል፤ በፅዳት ሠራተኛ፣ በተላላኪ፣ በዘበኛ እንዲሁም የፊልድ ስራ በማይመለከታቸው ሠራተኞች ለእራሳቸው የሚያስወጡትን አበል፤ በሾፌሮች የሚያስወጡትን የነዳጅ ብር፤ ለስብሰባ፣ ለፀጥታ ስራ ወዘተ እያሉ የሚያወጡት ብር፤ ለተለያዩ የፕሮጀክት ስራዎች ክፍያ በሚል የሚያወጡት ብር ወዘተ መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ምን ያህል የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ መሆኑ በሚገልፅ መልኩ ዝርዝር መረጃዎችን ያለምንም ብዙ ልፋት ማግኘትና ማጋለጥ ይቻላል።

አህመዲን ጀበል አንድ ወንድ ከ አንድ ሴት በላይ ማግባት ይችላል ወይስ አይችልም እየተባለ ሚድያ ላይ እየተቀባበሉት ላለው አለመግባባት በ ማስረጃ ጽፌያለው ብሏል።   🔴🔴🔴🔴🔴🔴እግዚአብሄር ሚ...
10/05/2025

አህመዲን ጀበል አንድ ወንድ ከ አንድ ሴት በላይ ማግባት ይችላል ወይስ አይችልም እየተባለ ሚድያ ላይ እየተቀባበሉት ላለው አለመግባባት በ ማስረጃ ጽፌያለው ብሏል።
🔴🔴🔴🔴🔴🔴
እግዚአብሄር ሚስት ላለው ሰው ሚስቶችን ሲጨምር
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

በጋብቻ ዙሪያ በኢስላምና በነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ላይ ሲሰነዘሩ የነበሩትን የስም ማጥፋት፣ የማጥላላትና የማነወሪያ ዘመቻዎችን ከሥር መሠረቱ ለማንኮታኮት የጀመርነውን ሂደት ዛሬም እንቀጥላለን። ከተንሸዋረ እይታ ለመነጨው ትንኮሳ ምላሽ የምንሰጠው ሙስሊም ወንዶች ተጨማሪ እንዲያገቡ፣ አልያም ማግባት የፈለጉ ሰዎች ከሌሎች ፍቃድ እንዲያገኙም አይደለም። እያሳየን ያለነው አንድ በላይ ሚስት ጋብቻ በኢስላም የተጀመረና ኢስላም የፈጠረው አለመሆኑን ተቺዎች እንዲረዱ፣ እውነታውን ከራሳቸው መጽሐፍ እንዲገነዘቡ ማድረግ ነው።

ኢስላም ከአንድ ሚስት በላይ ጋብቻን ገደብ ከማበጀት ባሻገር የሚያበረታታው ጉዳይም አይደለም። ጉዳዩን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ማየቱን ያስቀደምኩትም ተቺዎች የትችታቸው መሠረት የተገነባውና የቆመው በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ላይ በመሆኑና የተንሸዋረረ እይታቸው ምክንያት የሆነውን ያደፈ መነጽርን ማጽዳት ሊቀድም ይገባል ብዬ ስለማምን ነው።

እንዲሁም አንዳንድ ግንዛቤ የሌላቸው ወገኖች እንደሚሉት ኢስላም ሰባት ሚስት ማግባት የሚፈቅድ ሃይማኖት አይደለም። ከፍተኛው ቁጥር አራት ብቻ ነው። አላህ ከፈቀደ ይህንንም በቀጣይ ጽሑፎች እንመለከታለን።

የዛሬ ጽሑፌ ትኩረት "ከአንድ በላይ ያገቡ ሰዎች እግዚአብሔር እንዲያገቡ ፈቅዶላቸው ሳይሆን በራሳቸው ነጻ ፈቃድ ያደረጉት ስለሆነ እግዚአብሔር እንደፈቀደው መታሰቡ ስህተት ነው" የሚል ትችት ሲያቀርቡ የነበሩትን ወገኖች ሀሳብ ውድቅ መሆኑን ማሳየት ይሆናል። በትዕግስት ከማንበብ ባሻገር መልዕክቱ ለሁሉም እንዲደርስ ላይክና ሼር እንዲያደርጉ፣ አስተያየትዎንም እንዲያሰፍሩ እየጠየቅሁ መልካም ንባብ እንዲሆንልዎ እመኛለሁ!

"የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ"
🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒

በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚያብሔር ለዳዊት ሚስቶችን በሽልማት መልክ እንደሚጨምርለት በመጥቀስ ከአንድ በላይ ሚስት እንዲያገባ ሲያበረታታ ይታያል።

"ናታንም ዳዊትን አለው። ያ ሰው አንተ ነህ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በእስራኤል ላይ ንጉሥ ልትሆን ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ አዳንሁህ፤ የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፤ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።" (2ኛ ሳሙኤል 12፡7-12)

እዚህ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

1/ እግዚአብሔር ለዳዊት የአለቃውን ሚስቶች (በብዙ ቁጥር) መስጠቱ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባቱን ለማጽደቁ ማሳያ አይሆንምን?

2/ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ኃጢአት ከሆነ እግዚአብሔር ኃጢአትን እያበረታታ ነውን?

3/ ፈጣሪ ኃጠአትን እንደ ስጦታና ሽላማት ያበረክታል ማለት ነውን?

4/ ይህ አንቀጽ እግዚአብሔር በበርካታ ሚስቶች የዳዊትን ዘር ለማብዛት መፍቀዱን አያሳይምን?

5/ እግዚአብሔር ለዳዊት የአለቃውን ሚስቶችን እንደሚጨምርለት ቃል ገብቶ እነዚህ ሚስቶች አነሱኝ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ይበልጥ እንደሚጨምርለት "ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር" ሲል መግለጹ አንድ ሚስት ላለው ብቻ ሳይሆን ከአንድ በላይ ሚስቶች ላላቸውም ጭምር የበለጠ የመጨመር ፍላጎት እንዳለው አያሳይምን?

6/ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ኃጢአት ከሆነ ከዳዊት ጋር የነበረው ነቢዩ ናታን እንዴት በዝምታ አለፈው? እንዲያውም የእግዚአብሔርን የሚስት ጭመራ ቃል ኪዳን እንዲናገር የታዘዘው ነቢዩ ናታን አይደለምን?

7/ ዳዊት ሚስት እንዲጨመርለት እግዚአብሄርን ሳይጠይቅ እግዚአብሄር በራሱ ሚስቶችን እየጨመረለት አይደለምን? የዳዊት ፍላጎት ከግምት የገባው ዳዊት ከተጨመሩለት ሚስቶች በተጨማሪ ካስፈለጉት መሆኑን ከጥቅሱ እየተረዳን እንዴት "ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን እግዚአብሄር አልፈቀም" ብለው ለመናገር ደፈሩ?

8/ ከጅምሩ አንድ ሚስት ብቻ እንድትኖር የእግዚአብሄር መመሪያ ከነበረ ለዳዊት በግልጽ ሚስቶች እንደሚጨምርለት ሲገልጽ የበፊቱን ፍላጎቱን መለወጡን የገለጸበት አለን?

"ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፤ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ"
🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵

ሚስት የተጨመረለት ዳዊት ኦርዮንን በማስገደል ሚስቱን ለራሱ በማድረጉ እግዚአብሄር ተቆጣበት።የዳዊትን ሚስቶች ለሌሎች ሰዎች እንደሚሰጥበት እንዲህ ሲል ገለጸ...

"አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሄርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል። ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘላለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፤ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል። አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፤ እኔ ግን ይህን በእስራኤል ሁሉ ፊትና በፀሐይ ፊት አደርገዋለሁ።" (2ኛ ሳሙኤል 12፡9-12)

እዚህ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

1/ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እግዚአብሔር የከለከለውና እንደ ኃጢአት የሚያየው ከሆነ ታዲያ እንዴት እግዚአብሄር የዳዊትን ሚስቶች ለሌላ ሰው ለመስጠት ዛተ? እግዚአብሄር ለሌላ የሚሰጣቸውን የዳዊትን ሚስቶች በብዙ ቁጥር "ሚስቶች" በማለት ጠቅሶ ወሳጁን ደግሞ "ዘመድህ" በሚል በነጠላ ቁጥር መግለጹ ራሱ እግዚአብሄር ብዙ ሚስቶችን ለአንድ ሰው እንደሚሰጥ አያሳይምን? ኃጢአት ቢሆን ኖሮ ራሱ እግዚአብሄር የሚጠየፈውን ድርጊት እንዴት ይፈጽመው ነበር?

2/ እግዚአብሄር ዳዊትን የተቆጣበት ከአንድ ሚስት በላይ ስላገባ ሳይሆን ኦርዮንን አስገድሎ ሚስቱን ስላገባት ከነበረ ሚስት እያለው "ሚስት እጨምርልሃለሁ" ማለቱ እንዴት ያስኬዳል? በዚህስ እንዴት ሊቆጣበት ቻለ?

3/ ኃጢአቶቹ ሲዘረዘሩ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አብሮ አለመካተቱ እግዚአብሄር የተቆጣው በዝሙት፣ ክህደት፣ ግድያና ሚስት ነጠቃ እንጂ ከአንድ በላይ ሚስት በማግባቱ አለመሆኑ ድርጊቱ ኃጢአት አለመሆኑን አያሳይምን?

4/ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ኃጢአት ቢሆን ኖሮ ራሱ እግዚአብሄር ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ያለ ውግዘትና ትችት እንዴት እንደ ትንቢት ተናገረው? ተግባሩ ኃጢአት ቢሆን ኖሮ "ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል" በሚለው ገለጻ ላይ "ሚስት እያለህ" የሚለው ይጨመርበት አልነበረምን?

"ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት"
🔶🔶🔶🔶🔶🔶🔶

መጽሐፍ ቅዱስ "ሁለት ሚስት ያለው ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ስለሆነ አንዷን ይፍታ" አይልም። ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ኃጢአት ቢሆንና ፈጣሪ ባያጸድቀው ግን በግልጽ መከልከል ይችል ነበር። የሆነው ግን በተቃራኒው ነው። ከአንድ ሚስት በላይ ያገቡትን ወገኖች ድርጊት እውቅና ሰጥቶ እንዴት ሊያስተዳድሩ እንደሚገባ የሕግ ማዕቀፍ ነው የደነገገው። የሚከተለው ጥቅስ ምሳሌ መሆን ይችላል...

"ለልጁም ብድራት፥ ለሴት ልጆች የሚገባውን ያድርግላት። ከእርስዋ ሌላም ቢያጋባው፥ መኖዋን ልብስዋንም ለምንጣፍዋም ተገቢውን አያጉድልባት።" (ዘጸዓት 21፡9-10)

ከአንድ በላይ ሚስቶች ባሉበት ትዳር ስለሚወለዱ ልጆች የውርስ መብት የሚደነግግ አንቀጽም መኖሩን ማየት እንችላለን...

"ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፣ አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥ ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኩሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኩር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኩር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኩርነቱ የእርሱ ነው።" (ዘዳግም 21፡15-17)

እዚህ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች
💢💢💢💢💢💢💢💢

1/ እግዚአብሄር ከአንድ በላይ ሚስት ጋብቻን ክልክል ካደረገ እንዴት አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ሊኖሩት እንደሚችሉ እውቅና ሰጥቶ የሚተዳደሩበትን የሕግ ማዕቀፍ ሊያወጣ ቻለ?

2/ ጥቅሱ "ሁለት ሚስቶች ያሉት ሰው ክልክል ስለሆነ አንዷን ይፍታ" በማለት ፈንታ የሚስቶች መብትና የልጆች የውርስ መብት ተጠብቆ ሊኖሩ እንደሚገባ ሲያብራራ የምናየው ለምንድነው? በዚህ ጥቅስ እግዚአብሄር ምን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው የፈለገው? የጋብቻውን ሕጋዊነት ወይስ ክልክነት?

3/ ከአንድ ሚስት በላይ ጋብቻ ኃጢአት ቢሆን ኖሮ እግዚያብሄር ይህ ኃጢአት የሚቀጥልበትን የሕግ ማዕቀፍ ሊደነግግ ይችል ነበርን? ተግባሩ ክልክል እንዲሆን እግዚአብሄር የሚፈልግ ቢሆን ኖሮ አጀንዳው በግልጽ የተነሳበት ይህ አጋጣሚ እንዴት ከክልከላ ይልቅ ለፍቁድነቱ ዋለ?

4/ በአዲስ ኪዳን ከአንድ በላይ ሚስት ጋብቻ ክልክል ተደርጎ ከሆነ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድንጋጌ እየሱስም ሆነ ጳውሎስ ለምን በግላጭ አልሻሩትም? ይልቁንም በመሻር ፈንታ እየሱስ "እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም" (ማቴዎስ ወንጌል 5፡1) ማለቱ "ተሽሮ ሊሆን ይችላል" ብለን እንዳናስብ በሩን አልዘጋውምን?

በዚህ ጉዳይ ላይ የተሻለ አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖርዎ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ስለጥፋቸው የነበሩትን ተከታታይ ጽሑፎች እንዲያነቡ እየጋበዝኩ መልዕክቱ ለሁሉም እንዲደርስ ሼርና ላይክ እንዲያደርጉ እንዲሁም በሰለጠነ መንገድ ከስድብ የራቀ አስተያየትዎን እንዲሰጡበት እጋብዛለሁ።ለዛሬ በዚህ አበቃሁ።(ምስሉ በኤአይ ጄኔሬት የሆነ መሆኑን እየጠቆምኩ) በቀጣይ ጽሑፍ እስክንገናኝ መልካም ቆይታ ይሁንልዎ!

29/01/2023
💚💛❤️
24/01/2023

💚💛❤️

24/01/2023



እንኳን ለበርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል💚💛❤️
19/01/2023

እንኳን ለበርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ
መልካም በዓል💚💛❤️

14/01/2023

የኮካ ኮላ ጠርሙስ አትሁን!

ይህንን አባባል ካነበብኩት ብዙ ዓመት ሆኖኛል። አባባሉ እንዴት እንዳነቃኝ አልነግራችሁም። በየትኛውም አገልግሎት የራስን ዓቅም መገንባትና በብልጫ ለየት ብሎ መገኘት ጥቅሙ የትየለሌ ነው።

የኮካ ኮላ ጠርሙስ አንዱ በሌላው ያለችግር ይተካል፣ ተመሳሳይ ነው። የኮካ ኮላ ጠርሙስ ይመስል ከሌላው ልዩነት የሌለው ሆኖ መታየት ዓቅመ-ቢስ ያደርጋል።

አንተ ግን የኮካ ኮላ ጠርሙስ አትሁን! አገልግሎትህ፣ ሥራህ፣ ችሎታህ ከሌላው የተለየ እንዲሆን ሁሌም ራስህን አሻሽል።

የትኛውም ገበያ ለየት ላለ ሥራና አገልግሎት በብልጫ ይከፍላል። ካልከፈለህ የገበያ ቦታህን ቀይርና ትክክለኛ ዋጋህን ከሚያውቁና ከሚከፍሉህ ጋር ሥራ፣ ተገበያይ።

ደሞዝ ጭማሪ ለመጠየቅ ከፈራህ ዓቅምህ በቅጡ አልተገነባም ማለት ነውና አርፈህ ዓቅምህን ገንባ። ዓቅምህን ሳትገነባ ጭማሪ ክፈሉኝ ማለት ልክም ተገቢም አይደለም።

ዓቅምህ የተገነባ ሆኖ በበቂ ካልከፈሉህ ግን የሥራ ቦታህን ወይም የግብይት ቦታና የአሻሻጥ መንገድህን ቀይር። ሁሉም ነገር ስልት አለው።

ልብ በል! በገበያው ላይ ገንዘብ ሞልቷል። በበቂ የማይከፍሉህ "አይገባህም" ብለው ስለሚያስቡ ነው። እንደሚገባህ ማሳየት ደግሞ ያንተ ፋንታ ነው።

Focus on the Value you bring to the market.

Gabrielle 🖤
11/01/2023

Gabrielle 🖤

Address

Akakikaliti

1000

Telephone

+251946481630

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Soofam News Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share