Yordanos dejene page

Yordanos dejene page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yordanos dejene page, Digital creator, Addis Ababa.

19/07/2025

Live as locally ፡
Think as globally ፡
don't depend locally ፡
as well as globally ፡
the world is flexible :

18/07/2025

''እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ! .... (በዓሉ ግርማ)

“እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው፡፡ እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም ሰምና ወርቅ ነው ... “በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም ፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው፡፡ ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው ፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው፡፡ ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው ፤ የግል ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ ፥ ይሉታል ከነተረቱ፡፡ የሚያሳዝን ነው...
“ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን፡፡ ስንዋሽ
ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም፡፡ እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል ?
“ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው፡
“ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም፡፡ በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም፡፡ የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው፡፡ በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው፡፡ በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም፡፡ መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው፡፡ የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነውየምንኖረው፡፡ ያለ ጭንብል እናስቀይማለን ወይም እናምራለን፤አይታወቅም፡፡ ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!''

በዓሉ ግርማ ፥
የቀይ ኮከብ ጥሪ ፥ ገፅ 234

የኮሪደር ልማት ጉዳት ያደረሱ ከብቶች ተቀጡ::13 ከብቶች የኮሪደር ልማት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው 65 ሺ ብር በቅጣት  የከብቶቹ ባለቤቶች እንዲከፍሉ ተደረገበቦሌ ወረዳ 12 አስተዳደር የኮሪ...
18/04/2025

የኮሪደር ልማት ጉዳት ያደረሱ ከብቶች ተቀጡ::

13 ከብቶች የኮሪደር ልማት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው 65 ሺ ብር በቅጣት የከብቶቹ ባለቤቶች እንዲከፍሉ ተደረገ

በቦሌ ወረዳ 12 አስተዳደር የኮሪደር ልማት ላይ በቸልተኝነት ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል የተባሉ የከብት ባለቤቶች በ13 ከብት እያንዳንዳቸው 5ሺ ብር በጠቅላላ 65 ሺ ብር እንዲቀጡ በዛሬው እለት ተደርጓል።

የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ማህበረሰቡ ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠብ አሳስቧል ።

Via ዳጉ ጆርናል

🌴🌴🌴

09/03/2025

ነገ በስባሽ አፈር ገላ ይዘን አንመፃደቅ

መልክም ይረግፋል

05/03/2025

ሕይወት ልክ ብስክሌት እንደ መንዳት ነው ሚዛንህን ለመጠበቅ መንቀሳቀስህን መቀጠል አለብህ።
"አልበርት አንስታይን"

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yordanos dejene page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share