
31/01/2025
ጥምረቱ ውሃ በላው😋
፶ አለቃ ቸሩ የሚመራዉን ታጣቂ አስከትሎ ከምሬ ቡድን ወጥቷል!
ሰሞኑን እነምሬ ወዳጆ ጥምረት ፈጥረናል በሚል ይፋ ያደረጉት “የአማራ ፋኖ በወሎ” ገና ከጅምሩ እየፈረሰ የሚገኝ ሲሆን በርካቶች ከወዲሁ ከቡድኑ እራሳቸውን እያገለሉ ነው። ለአብነት መሳፍንት የተባለ አመራር የመሳሪያውን አፈሙዝ ወደምሬ በማዞር የሚመራቸውን ልጆች አስከትሎ ከቡድኑ ወጥቷል። ከዚህም በኋላ በርካቶች በየራሳቸው መንገድ ከቡድኑ አፈንግጠው ስለመውጣታቸው የደረሰን መረጃ ያመላክታል። ሰሞኑንም ፶ አለቃ ቸሩ የተባለ ታጣቂ የሚምራዉን ታጣቂ በሙሉ በማስከተል በምሬ ላይ በማመጽ ከቡድኑ አፈንግጦ ወጥቷል። ጥምረት የሚሉት ቀልድም ገና በሳምንት ስለመበተኑ ይህ በቂ ማሳያ ነው።