Ethio channel

Ethio channel FOLLOW AND LIKE OUR CHANNEL TO GET NEW UPDATES

20/10/2023

የመዲናችን አዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት ወይዘሮ አዳነች. አቤቤ ስልጣኔን ለማስረከብ መልቀቂያ አስገብቻለሁ ማለታቸው ታውቋል. ይልቀቁኝ አይልቀቁኝ እርግጠኛ ባልሆንም ግን ካሉብኝ ግን ጫናዎች እና የጤና ሁኔታ አንጻር. ከዚህ በኋላ በሌላ ቀለል ባለ የሥራ መደብ ለማገልገል ዝግጁ ነኝ ማለታቸው መነጋገርያ ሆኗል.
https://youtu.be/Fe-fISLKOp4

ሰበር ዜናበደበረማርቆስ ከተማ በፋኖ አና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል ከባድ ትንቅንቅ እየተካሄደ ነው. የአገዛዙ ሰራዊት ከተማዋን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ነው.ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ሊንኩን...
20/10/2023

ሰበር ዜና
በደበረማርቆስ ከተማ በፋኖ አና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል ከባድ ትንቅንቅ እየተካሄደ ነው. የአገዛዙ ሰራዊት ከተማዋን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ነው.
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ
https://youtu.be/MRLqF5npXJg

አይ ሳሮን
08/02/2022

አይ ሳሮን

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ከእነመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ************(ኢ.ፕ.ድ) መነሻውን ከአማራ ክልል ባህርዳር ልዩ ዞን ባህርዳር ከተማ ባደረገ  አይሱዙ  ተሽከርካሪ ...
27/01/2022

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ከእነመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

መነሻውን ከአማራ ክልል ባህርዳር ልዩ ዞን ባህርዳር ከተማ ባደረገ አይሱዙ ተሽከርካሪ ውስጥ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ጭነው አዲስ አበባ በማስገባት ለሽያጭ ሲያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሶስቱ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በአይሱዙ ውስጥ ሻግ በመስራትና በውስጡ በማድረግ በቁጥር አምስት ሺህ ስድስት መቶ አስር የሚሆን የክላሽ ጥይት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲገባ አድርገዋል።

ግለሰቦቹ ይህንን መሳሪያ ለሽያጭ ሊያቀርቡ ሲሉ በተደረገ ክትትል የጦር መሳሪያውን (ጥይቱን) ጨምሮ ሶስቱም አዘዋዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢፕድ ምንጮች አስታውቀዋል።

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል እርሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ!!!
19/01/2022

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል እርሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ!!!

19/01/2022

በወለጋ ንፁሃን ገበሬዎች ተጨፈጨፉ!

ዓመቱን ሙሉ፣ ሙሉ ወራትና ሙሉ ሳምንታት ንፁሀን የሚታደረዱበት፣ የሰው ልጅ ቄራ ሆኗል።

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳአያና ወረዳ በአንገር ጉትን ከተማ በመንደር 4 ቀበሌ ጥር 8 ቀን ለአዝመራ መሰብሰብ ወደ ማሳቸው ባቀኑ 10 አማራዎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተካሂዷል።

አመት ሙሉ የደከሙበትን አዝመራ ለመሰብሰብ ከወጡት አማራ አርሶአደሮች መካከል 10ሩ ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል፣ ታግተዋል። ከተገደሉት አስር ንፁሀን አማራዎች መካከል፦
1ኛ- ዳውድ አቤ
2ኛ- አብዱ የሱፍ
3ኛ- መሐመድ ይመር
4ኛ- እብራሂም ገበየሁ
5ኛ -ተናኘወርቅ ንጉሴ
6ኛ- ወንድሙ ሀይሌ
7ኛ- ታደሰ ደምሌ እና ሌሎች 3 ስማቸው ያልደረሰን በግፈኞች ጭካኔ በተሞላበት ተገድለዋል።

በተመሳሳይ በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ 8 አማራዎች ሲገደሉ የሁለት ሰዎች አድራሻቸው አልታወቀም። እስካሁን የ5 ሰዎች አስከሬን ተገኝቶ ጥር 7 ቀን 2014 ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕክምና ላይ የሚገኘውን አርቲስት አሊ ቢራን ጠየቁጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በዕለተ ጥምቀት በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል በሕክምና ላይ የሚገኘውን አንጋፋውን አ...
19/01/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕክምና ላይ የሚገኘውን አርቲስት አሊ ቢራን ጠየቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በዕለተ ጥምቀት በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል በሕክምና ላይ የሚገኘውን አንጋፋውን አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራን ጠይቀዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገኝተዋል (ኦቢኤን)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ******************(ኢ ፕ ድ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ፡፡ዋልያዎቹ ከምድቡ የመጨ...
17/01/2022

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ
******************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ፡፡

ዋልያዎቹ ከምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከቡርኪናፋሶ አቻቸው ጋር ባደረጉት ጨዋታ በአንድ አቻ አጠናቀዋል። ቡድኑ በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ከቡርኪናፋሶ፣ ካሜሮንና ኬፕቬርዴ ጋር መደልደሉ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

16/01/2022

ልዩ መረጃ‼️

: ወራሪውና አሸባሪው ቡድን ለ7ኛ ጊዜ የሰሜናዊ የዞን ዋና ከተማና የዞኑ መቀመጫ የሆነችው ከመቀሌ 45 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው #አብአላ ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት ከፍቷል። ሁሌም ዝግጁ ሆኖ የሚጠበቅው የአፋር ልዩሃይልና ህዝባዊ ሃይል ከጁንታው ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ እያካሄደ ይገኛል። ጁንታው መድፍን ጨምሮ ከባድ መሳሪያ እየተጠቀመ በመሆኑና የአፋር ህዝባዊ ሃይህ ከባድ መሳሪያ ባይኖረውም እስካሁን ጠላት ከነበረበት እንዳይንቀሳቀስ አድርጎታል።

ድል ለአፋር አናብስቶች

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio channel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share