19/08/2026
የሰማዕታት ክደት!
• ታሪካችን በደም የተጻፈ ነው፦ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም እና ጎንደር ላይ የወደቁት ጀግኖቻችን አባትና ልጅ፣ ወንድማማቾች እና ሙሉ የቤተሰብ አባላት በአንድነት የተሰዉበት ታሪክ ነው። [እነዚህ የቀረቡት ፎቶዎች ማሳያ ናቸው እንጂ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ለዚህ ትግል ወድቀዋል]።
• የአደባባዩ ውሸት፦ ዘመነ ካሴ ግን ከፈረንሳይኛ ጋዜጠኛ ጋር በነበረው ቃለ-መጠይቅ «ፋኖ ከህወሓት ጋር አልተዋጋም» ብሎ ሲዋሽ፣ ይህንን ቤት ሙሉ የፈሰሰውን የቤተሰብ ደም በአደባባይ ካደ።
• ቆመህም ሞተህም ይሸጥሃል፦ ይህ ሰው ቆመህም ይሸጥሃል፤ ሞተህም ታሪክህን፣ የሰራኸውን ስራና የፈጸምከውን ታላቅ ጀብድ ሙሉ በሙሉ የሚክድ የክህደት ባህሪ አለው።
• የጠላት ፈረስ፦ ውስጡ የሰረጸው የህወሓት ስነ-ልቦና ለጠላት ፈረስ መሆንን ስለሚያስገድደው፣ ዛሬ የሰማዕታቱን ደም የካደ ነገም ሙሉ አማራን አሳልፎ መሸጡ አይቀሬ ነው።