Sbahe Tube

Sbahe Tube ‟ሰው መሆን ጥቂቷን ከእኛ የምትጠበቅ ነገር ናት”

 #ናና አማኑኤል 🎤🎤 ***************ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ
04/08/2025

#ናና አማኑኤል 🎤🎤
***************
ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ

====« »=====፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ 🔴ከኦርቶዶክስ ውጭ ላላችሁ የሌላ እምነት አራማጆች አንዲት ምክር ልምከራችሁ‼️ 🔴.ይኽንን ለመፃፍ ያስገደደኝ አንዳንድ ሰዎች በ...
04/08/2025

====« »=====
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔴ከኦርቶዶክስ ውጭ ላላችሁ የሌላ እምነት አራማጆች አንዲት ምክር ልምከራችሁ‼️

🔴.ይኽንን ለመፃፍ ያስገደደኝ አንዳንድ ሰዎች በአስተያየት መስጫው(comment)ላይ ሳይገባቸው የሚቀባጥሩ ስላየሁ ለእነሱ ትንሽ ማብራሪያ ቢሆን ነው።

*********
🔴.ኦርቶዶክሳዊ መረዳት ወይም ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አይደለም ከቅጥሯ ውጭ ላላችሁ ይቅርና ከቅጥሯ ለሚዉሉ ለሚያድሩ እንኳ በእምነት መረዳት ሆነው በማስተዋልና በጥበብ ካልተመላለሱ በቀላሉ መረዳት የሚቻል አይደለም።
*************
🔴.በአጥር ሆናችሁ የቆማችሁበት የእምነት መሠረት እንኳ በውል ሳትረዱ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮዎቿን ለመንቀፍ የምትነሱ ሰዎች «የውቅያኖስን ውኃ በእንቁላል ቅርፊት ጨልፎ ለመጨረስ» የተነሳ ሞኝ ሰው እየመሰላችሁኝ ነውና ቢቀርባችሁ ይሻላል የሚል ወንድማዊ ምክር መለገስ እፈልጋለሁኝ።
****************
🔴.አይደለም የሥላሴን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ይቅርና የእመቤታችን ነገር እንኳ ቅዱሳን መረዳት ቢያቅታቸው እሷን ለመጠየቅ ነው የተገደዱት «ንዑ ንሕትታ ለቅድስት ድንግል»
‟ልብሱ መጋረጃው የእሳት የሆነ ጌታ የተሸከምሽ ድንኳን ሆይ አንቺ ማነሽ? እያሉ።
**************
🔴.ዓለምን ፈጥሮ የሚመግብ፣ ዓለምን በመሐል እጁ የያዘ ጌታ በክንድሽ ታቅፈሽ ሐሊበ ድንግልና ያጠባሽ ድንግል አንቺ ማነሽ? እስኪ ንገሪን እያሉ.......
***********,**
🔴.እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤልና ሱራፌል መሸከም የማይችሉት ጌታ በጀርባሽ የተሸከምሽ ታናሺቱ ሙሽራ ሆይ አንቺ ማነሽ? እያቄምና ሐና የወለዱሽ አይደለሽምን እያሉ?
***************
🔴.ብዙ ብጽፍ ብናገር አእምሮን ያዘነጋል ከታች ያለውን ምክር ልለግሳችሁና መልእክቴን ልጨርስ።
**********
🔴.እናንተ የምታስቡት የቅርቡ ኦርቶዶክስ የተቀመጠችው እጅግ ርቃና ረቃ።ስለዚህ የእናንተ መረዳት ከኦርቶዶክሳዊ መረዳት ጋራ የሰማይና የምድር ርቀት ያህል ልዩነት አለውና የያዛችሁት የምታምኑት እምነት ብቻ መርምሩ ተመራመሩ ለማለት እሻለሁ።

‟ ”===================================✍️.የጌታን ሕማማተ መስቀሉን የሚናገር ምን አንደበት ነው? እያለ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጌታ የተቀበለው መከራ መስቀል ያደን...
03/08/2025

‟ ”
===================================
✍️.የጌታን ሕማማተ መስቀሉን የሚናገር ምን አንደበት ነው? እያለ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጌታ የተቀበለው መከራ መስቀል ያደንቃል
ሊናገሩት የማይቻል ነውና!!

✍️.አይደለም ሕማሙን ተናግረውት በጆሮ ሰምተውት እንኳ ልብን የሚከፍል፣ ‟ወሕሊና ይዘበጥ” ሕሊናን በሐዘን የሚሰባብር ነውና።

✍️‟ነፍስ ትርዕድ” የጌታ ነገረ ሕማሙ ሲነገር አይደለም ፍርኃት ሞት የሚስማማው ሥጋ ይቅርና ሞት ፍርኃት የማይስማማት ውሳጣዊት ነፍስ እንኳ ትንቀጠቀጣለች።

✍️.‟ወሥጋ ይደክም” ሥጋም ከጽኑ ሐዘን የተነሳ ይደክማል፡ ጌታ ይኽንን ሁሉ መከራ መቀበሉ ሥጋ የለበሰውን ፍጥረት ሁሉ ለማዳን ነውና የጌታ ነገረ ሕማሙ እንዲሁ እንደ ቀላል የሚነገር አይደለምና በመስቀል የተደረገው ውለታ ከሕሊናት በላይ በመሆኑ ❝ወሥጋ ይደክም❞ አለ።

✍️.እስከ ሞት ድረስ የወደደን መድኃኔዓለም ይመስገን!!!!

✍️.መልካም ዕለተ ሰንበት

« »=============================ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት። 🔹ቀዳሚት አላት፡በክብር፡በዕለት 🔹ሰንበተ አይሁድም ...
02/08/2025

« »
=============================
ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት።
🔹ቀዳሚት አላት፡በክብር፡በዕለት
🔹ሰንበተ አይሁድም ይላታል፤በኦሪት አይሁድ የሚያከብሯት ሲል ነው።
🔸በዚህ ቀን እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን እናት ናትና የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፡የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፡የብርሃን መጋረጃ ይጋረዳል።ከዚያ ላይ ሆና ‟ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች።እሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል፤‟ወድሰኒ”(አመስግነኝ) ትለዋለች።ክርክር በሰኞ አልቋልና ባርክኒ ይላታል፤ ‟በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ” (የልጄ፣የባሕርይ አባቱ የአብ፣የባሕርይ ሕይወቱ የመንፈስ ቅዱስ)በረከት ይደርብህ ብላ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ትባርከዋለች።እሱም ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል።

🔷.‟ውዳሴ ዘቀዳሚት ውዳሴ በቀዳሚት ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት”
🔸.በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት የሚነበብ የሚጸለይ የሚተረጎም አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ምስጋናዋ ይኽ ነው።

🔷.‟ንጽሕት ወብርህት” ንጽሕት ነሽ ብርህት ነሽ።
🔹.‟ወቅድስት በኲሉ”
🔸.በአፍአ በውሥጥ ንጽሕት ነሽ። ንጽሕናዋ የሚለወጥ ሆኖ አይደለም እሱ ከቀን ወደ ቀን እየበቃ ማየቱን መናገር ነው።

🔹.‟እንተ ሐቀፈቶ ለእግዚእ በእራኃ”
🔸.ጌታን በመሐል እጅሽ የያዝሽው
አንድም በክንድሽ የታቀፍሺው።
🔸.‟ወኲሉ ፍጥረት ይትፌስሑ ምስሌሃ”
🔹.ፍጥረት ሁሉ ከአንቺ ጋራ እንዳንቺ ደስ ይላቸዋል።
🔸.‟እንዘ ይጸርሑ ወይብሉ፦ ሰአሊ ለነ ቅድስት እያሉ።
🔸.አንድም ‟ተፈስሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ”
ምልዕተ ክብር ሆይ ደስ ይበልሽ እያሉ።

🔹.‟ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ፡ተፈሥሒ እግዚአብሔር ምስሌኪ”
🔸.እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ተፈስሒ ደስ ይበልሽ።

🔹.‟ናስተበፅዕ ኦ ግርምት ድንግል”
🔸. ግርምት ድንግል ክብርሽን ገናንትሽን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እናመሰግናለን።ግርምነቷ በአይሁድ ፣በመናፍቃን በአጋንንት ዘንድ ነው።

🔹.‟ወንፌኑ ለኪ ፍስሐ ምስለ ገብርኤል መልአክ”
ከመልአኩ ገብርኤል ጋራ እንደ መልአኩ ገብርኤል ምስጋና እናቀርባለን። ፍስሐ አለ ምስጋናው ተፈስሒ ተፈስሒ እያለ ነውና ያበሰራት።

🔹.‟እስመ እምፍሬ ከርሥኪ ኮነ መድኃኒተ ዘመድነ”
ከማኅጸንሽ ፍሬ የባሕርያችን ድኅነት ተገኝቷልና።አንድም የማኅጸንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርያችን ድኅነት ሁኗልና።

🔹.‟ወአቅረበነ ኀበ እግዚአብሔር አቡሁ” ካባቱ ጋራ አስታረቀን።

🔸.‟ሰአሊ ለነ ቅድስት” ካባቱ ጋራ ካስታረቀን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።

🔷.‟ከመ ከብካብ ዘአልቦ ጥልቀት” እንደ ሠርግ ቤት አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ሆኖ ቢያገኝሽ።
🔸.‟መንፈስ ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ” መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና።

🔷.‟ወኃይለ ልዑል ጸለለኪ” ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ለብሷልና። አንድም መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ ግብራት ከልክሎሻልና።ኃይለ ልዑል ወልድም ከሦስቱ ግብራት ከልክሎሻልና።ሦስቱ ግብራት የተባሉትም በሰው ልጅ ዘንድ የተፈጥሮ ሕግ የሆኑ ናቸው እነኚህም፦
፩.ከወንድ ጋር መገናኘትን
፪.በዘር መጽነስን
፫.ድንግልና ማጣትን እነዚህ ግብራት ግን በእመቤታችን ዘንድ የሉም አልተደረጉም መንፈስ ቅዱስ ጠብቋታልና።

🔷.‟ኦ ማርያም አማን ወለድኪ ቃለ ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም” ከላይ ከዘረዘርናቸው ጠብቃ በመኖሯ በእውነት አካላዊ ቃለ እንደ ወለደች፡ ለቀዳማዊ ልደቱ እውነተኛ ማያ እንደሆነች ከዓለም አስቀድሞ ለዘላለም ከአባቱ ጋራ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ በእውነት ወልደሽልናልና አለ።

🔷.‟መጽአ ወአድኃነነ እምኃጥአት”
ሰው ሆኖ ከኃጢአት አዳነን።
🔸.‟ሰአሊ ለነ ቅድስት” ሰው ሆኖ ከኃጢአት ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።

✍️.ይቆየን
✍️.የቀጣዩን በሌላ ቀን እንቀጥላለን!!
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!



« »🎤     ∞∞∞∞∞∞∞∞∞ስላልተወኝ አንዳች አጣህ ብሎሙሉ ሰው ነኝ የለኝም ጎደሎበከፍታ ብኖር በዝቅታ ደስተኛ ነኝ ሁልጊዜ በጌታ።
01/08/2025

« »🎤
∞∞∞∞∞∞∞∞∞
ስላልተወኝ አንዳች አጣህ ብሎ
ሙሉ ሰው ነኝ የለኝም ጎደሎ
በከፍታ ብኖር በዝቅታ
ደስተኛ ነኝ ሁልጊዜ በጌታ።




-------=-----« #መርቆሬዎስ» -----------===========----=====================✍️.መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።ተወ...
01/08/2025

-------=-----« #መርቆሬዎስ» -----------
===========----=====================
✍️.መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።ተወልዶ ያደገው ሮሜ ከተማ ላይ ነው።

✍️.ወላጆቹ ቀድሞ አረማውያን የነበሩ በኋላ በክርስቶስ አምነው የክርስትና ጥምቀት የተጠመቁ ቤተሰብ የተገኘ ነው።

✍️.ቅዱስ መርቆሬዎስ በገድሉ እግዚአብሔርን ደስ አሰኝቶ ብዙ መከራ ተቀብሎ ለአምላኩ እስከ መጨረሻይቱ ህቅታ ድረስ ታምኖ የክብር አክሊል የተቀበለ ሰማዕት ነው።ከገድሉ ብዛት የተነሳም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ ሊቀ ሰማዕታት ተብሎ እንዲጠራ አድርጎታል።

✍️.ቅዱሳንን በየወሩ በየዓመቱ ማሰባችን ለምንድነው የሚለው ሁላችንም ልናውቀው የሚገባ ጉዳይ ነው። ቅዱሳን በየጊዜው ማሰባችን ለከንቱ አይደለም የሚከተሉት ነገሮች ስለምናገኝባቸው ነው፦

፩.በቃል ኪዳናቸው የሚገኝ ጸጋና በረከት ለማግኘት
፪.የጸኑትን እየተመለከትን በግብር እንድንመስላቸው ነው።
፫.ለቅዱሳኑ ቅሩብ ከሆነ አምላክ አማልደው ምሕረት እንዲያሰጡን ነው።
፬.ከሕይወታቸው እንድንማርባቸው ፍለጋቸውን በመከተል በእምነታችን እንድንጸና ነው።

✍️.ከሰማዕቱ ከቅዱስ መርቆሬዎስ ጸጋና በረከት ያሳትፈን!!!

«ደስ የሚል ዜና ‼️            «በአማን ሕርያቆስ »====++++++======+===+++=======«ሕርያቆስ ብሂል ኅሩይ እምማዕከለ ብዙኃን»  ሕርያቆስ ማለት ከብዙዎች መካከል የተ...
01/08/2025

«ደስ የሚል ዜና ‼️
«በአማን ሕርያቆስ »
====++++++======+===+++=======
«ሕርያቆስ ብሂል ኅሩይ እምማዕከለ ብዙኃን» ሕርያቆስ ማለት ከብዙዎች መካከል የተመረጠ ማለት ነው ለሹመት መርጠውታልና። የቀደመው ሕርያቆስ ከብዙዎች መካከል ለሹመት እንደተመረጠ ሁሉ ፡አባታችን አባ ሕርያቆስ የሀዲያና ስልጤ አኅጉረ ስብከት እንዲሁም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከብዙዎች መካከል የተመረጡ ናቸው።አሁንም በእሳቸው መልካም ፈቃድ የአባታችንን በኲረ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስ የብዙ ዘመን እንባቸውን በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት በኩል አብሰውላቸዋል። ምንም እንኳ ከረፈደ ቢሆነም ብጹዕ አባታችን የሰሩት መልካም ተግባር ግን ከአባታችን ከበኩረ መዘምራን ባሻገር የብዙዎቻችን ልብ ደስ ያሰኘ ተግባር ነውና ይበል ያሰኛል። ብጹዕ አባታችን በቀጣይም ሙሉ እውቀታቸው ይዘው የአስተዳደር በደል ደርሶባቸው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ርቀው ያሉ የተረሱ ሊቃውንት አሉና ቢመለከቷቸው የልጅነት ተማጽኖየ ነው።

) (🎤ተክለሃይማኖት ባሕታዊ ምድራዊ ሲሉት ሰማያዊ ባደባባዩ ተተክለሃል ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል።
31/07/2025

) (🎤
ተክለሃይማኖት ባሕታዊ
ምድራዊ ሲሉት ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል።

« »============================✍️.ኒቆምዲያ ከምትባል ከተማ ትኖር የነበረች ሴት ናት ቅድስት ቴክላ ትባላለች። የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት በቤቷ መስኮት ሆና ትከታተል የነበ...
31/07/2025

« »
============================
✍️.ኒቆምዲያ ከምትባል ከተማ ትኖር የነበረች ሴት ናት ቅድስት ቴክላ ትባላለች። የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት በቤቷ መስኮት ሆና ትከታተል የነበረች ቅድስት ናት።ይህች ቅድስት ከቃሉ ጣዕም የተነሳ ሦስት ቀናት ያለ እህልና ውኃ በማሳለፍ የክርስቶስን ቃል በልቧ የተሳለላት ቅድስት ናት።

✍️.አባትና እናቷ ግን በዚህ ነገሯ ደስተኛ አልነበሩም(የሐዋርያው ጳውሎስ) ትምህርት መስማቷ፣በክርስቶስ ፍቅር መማረኳ አልወደዱላትም ነበር።እሷ ግን የክርስቶስ ፍቅር በልቧ አድሯልና አባትና እናቷን ትታ የለበሰቻቸው ጌጦች ሁሉ አውልቃ ጥላ ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እግር ተቀምጣ ቃሉን ታደምጥ ነበር።በዚህ የተነሳ የገዛ ወላጆቿ ከመኰንኑ ዘንድ ከሰሷት መኰንኑም በእሳት እንዲያቅጣሏት አዘዘ የሚገርመው ነገር ወላጅ እናቷ ከመራራት ከማዘን ይልቅ «ለሌሎች ሴቶች መማሪያ እንዲሆን በደንብ አድርጋችሁ አቃጥሏት» እያለች ትጮኽ ነበር ቅድስት ቴክላ ግን በፍጹም ጽናት ሆና ተጋድሎዋን ትፈጽም ነበረ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም እየጸለየ ያድናት ነበር።

✍️.ከዚህ በኋላ ከኒቆምዲያ ተነስታ ወደ አንጾኪያ ከተማ ሄደች በዚያ የነበረ መኰንንም ደም ግባቷ ያማረ ነበርና ተመኛት እሷ ግን እሱንና አማልክቱን ረገመች።በዚህ ተቆጥቶ ወደ ተራቡ አንበሶች ጣላት በደህና ወጣች፣በሁለት በሬ አድርጎ በከተማው እንድትጎተት አደረገ ምንም ክፉ ነገር አላገኛትም ከዚህ በኋላ በሰላም አሰናበቷት ወደ ቅዱስ ጳውሎስም ዘንድ ደረሰች እርሱም በክርስቶስ ቃል አጽናንቶ አረጋጋት እንድታስተምርም ላካት።

✍️.ከዚህ በኋላ ወደ ቤተሰቦቿ ዘንድ ሄዳ አባትና እናቷ አሳምና ክርስቶስን ወደማመን መለሰቻቸው ተጋድሎዋም ፈጽማ የሐዋርያነት አክሊል ተቀብላ በሰላም አረፈች።ዕረፍቷም ሐምሌ ፳፭ ቀን ነው ።ለዚህ ሁሉ ክብር ያበቃት ግን «በመስኮት ሆና በተማረችው ትምህርት ነው»።

"ከቅድስት ቴክላ በረከት ያሳትፈን"!!

         ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።«ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩጸተ ነፋስ ወዐውሎ       ለዘይጼውዐከ በተወክሎ      ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ     ተወከፍ...
30/07/2025


።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
«ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩጸተ ነፋስ ወዐውሎ
ለዘይጼውዐከ በተወክሎ
ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ
ተወከፍ ወትረ ጸሎተነ ወቃለ ጽራሕነ ኩሎ
እስመ ልበአምላክ ርኅሩህ በኀቤከ ሃሎ።
**************
«በስምህ፡በረድኤትህ ተማምኖ ለሚጠራህ ከአውሎና ከነፋስ ይልቅ ፈጥነህ የምትደርስ ጊዮርጊስ ሆይ፡ልቡ ሩኅሩህ የሆነ አምላክ ከአንተ ጋራ ሁልጊዜ አለና፡እኛም በእምነት ሆነን ስምህን ስንጠራ በምሕረትና በይቅርታ ወደ እኛ ቅረብ።
*************
ሊቀ ሰማዕታት የኢትዮጵያ ገበዝ ቅዱስ ጊዮርግስ በያለንበት ሁላችንንም ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን
የሀገራችን ሰላሟም ይመልስልን!!!

« የሰርክ ዜማ»የደካሞች ምርኩዝ የኃጥአን ተስፋ/፪/ፈጥነሽ ትደርሻለሽ የሰው ልጅ ሲከፋምን በግዞት ቢሆን ጨለማ ቢወርሰው/፪/እንዳዘነ አይቀርም አንቺን የያዘ ሰው/፪/            🙏🙏🙏...
28/07/2025

« የሰርክ ዜማ»
የደካሞች ምርኩዝ የኃጥአን ተስፋ/፪/
ፈጥነሽ ትደርሻለሽ የሰው ልጅ ሲከፋ
ምን በግዞት ቢሆን ጨለማ ቢወርሰው/፪/
እንዳዘነ አይቀርም አንቺን የያዘ ሰው/፪/
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ምን ይሆን ውለታሽ ድንግል የምከፍልሽ/፪/
ላንቺ በመንገሬ ተፈታ ችግሬ/፪/

👉እባክዎን ይህንን ዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ🙏
https://www.youtube.com/-%E1%8B%98%E1%8A%A2%E1%8B%AB%E1%88%B1

 ======++++++=========+++++========✍️እናንተ በምግበ ሥጋ የተራባችሁ ምዕመናን ኑ ምግብና መጠጥ በነፃ ተመገቡ፤ለነፍስም ለሥጋም ምግበ ሕይወት የሚሆን ጌታ ያስገኘች የወይ...
28/07/2025


======++++++=========+++++========
✍️እናንተ በምግበ ሥጋ የተራባችሁ ምዕመናን ኑ ምግብና መጠጥ በነፃ ተመገቡ፤ለነፍስም ለሥጋም ምግበ ሕይወት የሚሆን ጌታ ያስገኘች የወይን ሐረግ አለችላችሁና ይህችውም እመቤታችን ማርያም ናት።

✍️.ሩቅ ተጉዛችሁ የምትሄዱ ሰዎች ከመንገድ ብዛት የተነሳ እንዳትራቡም እንዳትጠሙም ለመንገዳችሁ የሕይወት ስንቅ የምትቋጥርላችሁ እውነተኛ እናት አለችና ስሟን ይዛችሁ ተጓዙ።

✍️.በደዌ ዳኛ፡ በአልጋ ቁራኛ ተይዛችሁ ላላችሁ ሰብአ-ዓለም ፈውሰ ሥጋ ወነፍስ የሆነ ጌታ በእቅፏ ያለ እናት አለችና ሕመማችሁን ለእሷ ንገሯት ፈውስ ይደረግላችኋልና።

✍️.በተስፋ መቁረጥ የምትኖሩ ምዕመናን ሆይ ተስፋን የሚቀጥል ለዘለዓለምም ተስፋ የሚሆነን አባት በክንዷ አለና ሐዘናችሁን ለእሷ ንገሯት ሐዘናችሁን ወደ ደስታ የምትቀይር ናትና።

✍️.ከእናትነት በላይ የሆነች እናት የሰጠን አምላክ ምንኛ ቢወደን ነው! እናቱን እናት አድርጎ የሰጠን?

✍️.ይህችም እናት ስሟ ከማር የሚጣፍጥ ስም ያላት እመ አምላክ ድንግል ማርያም ናት።ማር ጣዕሙ የሚታወቀው ሲቀምሱት ነው የድንግል ማርያም ስም ግን ገና ሲጠሩት የሚጥም ስም ነው!!!
👉. ይህንን ስም ጥሩት......
❤ማርያም ማርያም ማርያም
#የዩቲዩብ ቻናሌ ነው ሰብስክራይብ👇👇👇 https://www.youtube.com/-%E1%8B%98%E1%8A%A2%E1%8B%AB%E1%88%B1

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sbahe Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sbahe Tube:

Share