ፍቅር ያሸንፋል

ፍቅር ያሸንፋል 🌍 Voice of the people, working for justice, unity, Building bridges, inspiring change, and empowering communities🌍
(316)

በየአከባቢያችሁ ቋንቋ ምን ይበላል?
03/10/2025

በየአከባቢያችሁ ቋንቋ ምን ይበላል?

Ayyaana Irecha Negaan Geesan !!የተከበሩ አቶ ተፈራ ሞላ....የአዲስአበባ ከተማ  ማዘጋጃ ቤት የሥራአስኪያጆች ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ !!
02/10/2025

Ayyaana Irecha Negaan Geesan !!
የተከበሩ አቶ ተፈራ ሞላ....የአዲስአበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሥራአስኪያጆች ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ !!

 😭💔የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የእግር ኳስ ቡድን የቀድሞው ግብ ጠባቂ የነበረው ሳዳት ጀማል ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ጠቅላይ መምሪያው የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል።***ሳዳት ጀማ...
01/10/2025

😭💔

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የእግር ኳስ ቡድን የቀድሞው ግብ ጠባቂ የነበረው ሳዳት ጀማል ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ጠቅላይ መምሪያው የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል።
***
ሳዳት ጀማል በአዲስ አበባ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን እና በሌሎች ክለቦች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በግብ ጠባቂነት አገልግሏል። በስፖርተኛው ከዚህ አለም በሞት መለየት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።

#አዲስአበበለፖሊስ

ሰበር አሳዛኝ ዜና‼️ሼር ይደረግ❗❗❗😥ዛሬ 21/01/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል  ምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን አመታዊ ክብረበዓልን አስመልክቶ ከጠዋቱ 2:45 ላይ እየተሰራ ...
01/10/2025

ሰበር አሳዛኝ ዜና‼️ሼር ይደረግ❗❗❗😥
ዛሬ 21/01/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል ምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን አመታዊ ክብረበዓልን አስመልክቶ ከጠዋቱ 2:45 ላይ እየተሰራ ያለው ቤተክርስቲያን እየተጎበኘ ባለበት ሰዓት ለፊኒሺንግ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ እስካሁን ከ35 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን በበርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በስፍራው የሚገኙ የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልፀዋል።
እስካሁን የተጎዱ እና የሞቱ ሰዎች በሰው ሀይል እየወጡ ሲሆን ሁሉም የመግስት አካላት ቀይ መስቀልን ጨምሮ ትብብር እንፈልጋለን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
እስካሁን አስኬረን እየወጣ ሲሆን አረርቲ የሚገኙ ሙሉ የመንግሥት እና የግል ጤና ተቋሟት በተጎጂች እና በአስኬረን ሞልቷል ብለውናል።
አሳዛኝ አደጋ😥
ለተጎዱ ሰዎች መልካሙን ሁሉ እንመኛለን፣ህይወታቸውን ላጡ ነፍስ ይማር።
(አዩዘሀበሻ)
===================

በኮሪደር ልማቱ ላይ የተሰራ የትራፊክ ምልክት ነቅለው የወሰዱ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለው በ6 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፤ ተከሳሾቹ በኮሪ...
01/10/2025

በኮሪደር ልማቱ ላይ የተሰራ የትራፊክ ምልክት ነቅለው የወሰዱ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለው በ6 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፤ ተከሳሾቹ በኮሪደር ልማቱ ላይ ከተተከለው የትራፊክ ምልክ ባሻገር በተጨማሪ 6 የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን ( Dust bins ) መስረቃቸውንም በምሪት አሳይተዋል፡፡
***
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ካምብሪጅ ትምህርት ቤት አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሾች ታረቀኝ ታፈሰ እና አፈወርቅ ዮናስ በኮሪደር በለማ መንገድ ላይ ተተክሎ የነበረ የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክት ነቅለው ይዘው ሲሄዱ በወቅቱ በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ፖሊስም ተከሳሾችን ይዞ ባደረገው ምርመራን የማስፋት ተግባር በኮሪደር በለማ መንገድ ላይ ዳር ተቀምጦ የነበረ የዋጋ ግምታቸው 2 መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ 6 የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን ( Dust bins ) በመስረቅ በአካባቢው ለሚገኙ 3 ተቀባዮች በ8 ሺህ ብር የሸጡ መሆኑን አምነው ቃላቸውን በመስጠታቸው ተቀባዮችን በቁጥጥር ስር በማዋል ኤግዚቢቶቹን ማስመለስ መቻሉን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾች ታረቀኝ ታፈሰ እና አፈወርቅ ዮናስ በፈፀሙት የትራፊክ ምልክት የስርቆት ወንጀል የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው ሲሆን በቀጣይም በፈፀሙት የመንገድ ዳር የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን ( Dust bins ) ስርቆት ወንጀል ለውሳኔ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲቀርቡ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በህዝብ ሀብት ላይ የሚፈፀሙ በመሆናቸው ህብረተሰቡ መሠል የወንጀል ድርጊቶችን ሲመለከት ለአቅራቢያው የፀጥታ አካል መረጃ ሊሰጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በካንሰር እየተሰቃየ ያለ ወጣት 😥 😭ፈጣሪ ይማርህ             ስልክ ቁጥሩ👉☎️  0777621547
30/09/2025

በካንሰር እየተሰቃየ ያለ ወጣት 😥 😭ፈጣሪ ይማርህ
ስልክ ቁጥሩ👉☎️ 0777621547

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አባል ነኝ በማለት ሰዎችን በማስፈራራት እያገተ ገንዘብ ሲቀበል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ። *...
29/09/2025

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አባል ነኝ በማለት ሰዎችን በማስፈራራት እያገተ ገንዘብ ሲቀበል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
***

ዳዊት ጥላሁን ወይም ምንተስኖት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ በመጠቀም የተቋሙ ሰራተኛ ነኝ በማለት ሰዎችን በማገትና በማስፈራራት ገንዘብ እንደሚቀበል ከህብረተሰቡ የመጣን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በጥምረት ባደረጉት ክትትል ግለሰቡን መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር እንዲውል አድርገዋል።

ተጠርጣሪው ከሜክሲኮ ወደ ጋርመንት በታክሲ ተሳፍራ የምትሄድን የግል ተበዳይን ሳሮን ተስፋዬን ደህንነት ነኝ በማለት በማስፈራራት እና በመደብደብ ጉዳት ያደረሰባት መሆኑን የግል ተበዳይ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨቷ ይታወቃል። ግለሰቡ በግል ተበዳይ ላይ ባደረሰው ጉዳት በህግ የሚጠየቅ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ እንደተገኘበት ፖሊስ አስታውቋል።

በግለሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመበት ግለሰብ እና ስለ ግለሰቡ ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ለአዲስ ለአበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደረግ እና የጸጥታ አካላትና አባል ነን በማለት የሚያስፈራሩና ተጽዕኖ የሚያሳደሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት በወቅቱ ለፖሊስ እንዲያሳውቅ መልዕክት ተላልፏል።

29/09/2025

#ስለፍትህ ሼር አድርጉ !!

ትክቶከሮች፣ ፌስቡከሮች፣ በተላይ ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉትን አመራሮችን የሚታሽቀብጡ፣ ትላንትና ፕሬዘዳንት ሆኖ በነበረበት ጊዜ ዶክተር ሀብታሙ አበበን ስታሽቀብጩ እና ልዩ ልዩ ጥቅም ስታገኙ የነበራችሁ አካላት ማለትም በሀዲያ ዞን የምትገኙ የማህበራዊ ሚዲያ Bloggers፣ አርቲስቶች፣ እንዲሁም የቤት ችግር የተፈታላችሁ የዋቸሞ ዩንቨርስቲ መምህራንና የግቢ ማህበረሰብ ለታሰሩ ለዋቸሞ ዩንቨርስቲ ዋና ፕሬዚዳንት ለዶክተር ሀብታሙ አበበ፣ ለዶክተር ታምራት ታገሰ ፣ ለአቶ ደሳለኝ አስራደ እንዲሁ ለሌሎች አብሮ ለታሰሩ ወንድሞቻችን ፍትህ ጠይቁ !!

የከምባታ ልጆች ዝምታችሁን ስበሩ የከምባታ ነፃነት #አርማ ለሆኑ ለእነ ዶክተር ሀብታሙ አበበ ፍትህ ጠይቁ። የከምባታ ህዝብ ለዘመናት የዩንቨርስቲ እና የመንገድ መሠረተ ልማት ስጠይቅ የኖረ ህዝብ ሲሆን የመጡት መንግስታት ሁሉ ባልሰማ ስያልፉት የነበረው የከምባታ ማህበረሰብንና የልማት ጥያቄአቸውን ነበረ። ይሁንና የከምባታ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሰሩት ከከምባታ አብራክ የተወለዱ ልጆች ሳይሆኑ ከሀዲያ ማህፀን የተወለዱ እነ ዶክተር ሀብታሙ አበበ ናቸው። የከምባታ ህዝብ መንግስትን ጠይቆ ያጡትን ዩንቨርስቲ በእጃዙር እውን እንዲሆን ያደረጉት ከሀዲያ ማህፃን የተወለዱ የልማት አርበኞች እነ ዶክተር ሀብታሙ አበበ ናቸው። ማንም እንደሚያውቀው፣ ታሪክ እንደሚመሰክረው በሀገራችን በልማት እጦት ስቸገር የነበረ የተረሳ አከባቢ ማለት የከምባታ ምድር ነበረ። ነገር ግን የሃዲያው ጀግና ምሁራን ጉረቤት ዞናችንን ይዘን በአብሮነት ማደግ አለብን የሚል እሳቤ ቀርጾ በሰሩት ስራ ዩንቨርስቲን ቅርንጫ ካምፓስ በመክፈት ፣ በሰበቡ መንገድ እና ውሃ ለከምባታ ህዝብ እንድሰራ በማደረግ ዛሬ በከምባታ ምድር የሚታየው እንቅስቃሴ እንዲመጣ የሰሩት እነ ዶክተር ሀብታሙ አበበ ናቸው። የከምባታ ልጆች ዛሬ አንገታቸውን ቀና ብሎ እንዲሄዱ ምክንያት የሀዲያ ልጆች እነ ዶክተር ሀብታሙ አበበ ናቸው። ስለሆነም የከምባታ ልጆች ከማንም በላይ ለታሰሩ ለልማት አርበኞች ድምጽ ልትሆኑ፣ ፍትህ ልትጠይቂ ይገባል !!

እኛ በዘር ሀዲያ ነን የሚትሉና ከዋቸሞ ዩንቨርስቲ ተጠቃሚ የሆናችሁ የሀላባ ልጆች ለታሰሩ ወንድሞቻችን ፍትህ ጠይቁ። በጂኦግራፊ ብዙ እንዛመዳለን የሚትሉ በደግነት የሚትታወቁ የጎረቤት የየም ልጆቾ ባህር ማዶ ተሻግሮ ለልጆቻችሁ የትምህርት እድል የሰጠው የልማት አርበኛ ዶክተር ሀብታሙ አበበ ታስሯልና ድምጻችሁን አሳሙ።

ዶክተር ሀብታሙ አበበ በሠራው ትጋት የተሻሻሉ የምርጥ ዘር የሰብልና የእንስሳት ዝርያ አገኝታችሁ ኑሮአችሁ የተለወጠላችሁ የሀዲያ እና የከምባታ አርሶአደሮች የልማት አርበኛ ታስሮአልና ድምጻችሁን አሰሙ።

ከባህር ማዶ ዩንቨርስቲዎች ጋር ግንኙት በመፍጠር የተሻለ የትምህር እድል እንዲታገኙ መሠረት ያስተካከለላችሁ ዶክተር ሀብታሙ አበበ ታስሮአልና Scholars ድምጻችሁን አሳሙ።......... ሌሎችም በያላችሁበት ፍትህ ፍትህ በሉ !!!

 #ከሀዲያ ምድር የተገኘችው ለብዙ ሴቶች ምሳሌ መሆን የቻለችው የሀዲያን ባህላዊ ልብስ እንዲሁም የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የባህል ልብስ በመስራት የምትታወቀው የሴቶች አንበሳ Me...
29/09/2025

#ከሀዲያ ምድር የተገኘችው ለብዙ ሴቶች ምሳሌ መሆን የቻለችው የሀዲያን ባህላዊ ልብስ እንዲሁም የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የባህል ልብስ በመስራት የምትታወቀው የሴቶች አንበሳ Meski Gebre ዛሬ ልደቷ ነው !!

መልካም ልደት እህቴ !

28/09/2025

👉ይድረስ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር ለዶክተር አብይ አህመድ አሊ
👉ይድረስ ለኢፌዴሪ ፍትህ ሚንስተር !!

በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ እየተገነባ ባለው በዘመናዊ መምህራን መኖርያ ህንጻ ምክንያት የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ፣ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ታምራት ታገሰ እና አቶ ደሳለኝ አስራደ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ ባለቤትና ስራአስኪያጅ የታሰሩበት አግባቢ ህገወጥ ነው፡፡

አቶ ደሳለኝ አስራደ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ የሚሰራው መምህራን መኖሪያ ቤት በሚመለከት ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የቀረበ ጥቆማና የተደረገ የልዩ ኦዲትና የተሰጠው አስተያየት እንደሚከተለው አቀረብኩኝ፣

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን መኖሪያ የሚሆን ህንፃዎችን ለመገንባት ጨረታ አውጥቶ በወጣው ጨረታ መሰረት ያሸነፈው አቶ ደሳለኝ አስራደ ሥራ ተቋራጭ በጨረታው ሰነዱ ላይ በተቀመጠው 360 ቀናት የግንባታ የውል ጊዜ መሰረት ውሉን ቀርበው እንድፈርሙ ዩንቨርሲቲው በደብዳቤ ያሳወቀው ሲሆን ደሳለኝ አስራደ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታን በተመለከተ የሰጠው ምላሽ ደብዳቤ እንደሚከተለው አቅርቡያለሁ፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 20/2020 (10/01/2013) በጨረታ ቁጥር 1001/2013 በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ በሎት 01 የመምህራን መኖሪያ ሕንጻዎችን ለማስገንባት ባወጣው ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ድርጅታችን ተሳትፎ የቴክኒካል ግምገማውን በማለፍ በተከፈተው የፋይናንሻል ውድድር ድርጅታችን ደሳለኝ አሥራደ ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል። ይልና፡-ይሁንና ይህ በእንዲህ እንዳለ ከብዙ መዘግየቶች በኋላ ዩኒቨርሲቲው በቀን 04/12/2014 በቁጥር 04/232/14 በጻፈው ደብዳቤ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር በሠጠው ማብራሪያ መሠረት የዋጋ ወይንም የፕሮጄክት ማጠናቀቂያ ግዜ ወደ 720 ቀነት የግንባታ ጽ/ቤት በተስማማው መሰራት ዩኒቨርሲቲው ማሻሻያ ማድረግ የማይቻል በመሆኑ ቀደም ሲል ከአንድ ዓመት ከአስራ አንድ ወር በፊት በሰጠነው ዋጋ ለመሥራት ውል እንድንፈራረም ተጠይቀናል፡፡
በማለት፡- ይሁንና እንደሚታወቀው ባለፉት ሁለት ዓመታት በኮንስራክሽን ግብኣቶች ከ100% በላይ የሚሆን የዋጋ ንረት መከሰቱ በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ሆኖ ሳለ ከዓመት ከአስራ አንድ ወር በፊት በተሰጠ ዋጋ ያለ ምንም ማሻሻያ ሥራውን እንድንሰራ መጠየቅ ድርጅቱን ለከፍተኛ ኪሳራ የሚያደርግ ጉዳይ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲፈልግ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ በማለት ትክክለኛ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በዚህ መነሻ የዋቸሞ የዩንቨርሲቲ ማኔጀመንት የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ ጨረታ መሰረዝን በተመለከተ የሚከተለዉን ዉሳኔ ወስኗል፡፡

ከዚህ ቀደም የመምሀራን መኖሪያ ቤት G+6 የሆነ ህንፃዎችን ለማስገንባት ጨረታ የወጣ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የጨረታ ሂደቱ የተጎተተ ሲሆን ጨረታው ተጠናቆ ውል ለመግባት ጊዜ በመወሰዱ ፕሮጀክቱ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ጤናማ ሆኖ መቀጠል ስለማይችል ጨረታው ተሰረዞ ከግዥ ኤጀንሲ በተገኛው የግዥ የቁርጥ ዋጋ ፍቃድ መሰረት የመኖሪያ ቤቶች እንዲሰሩ ተወስኗል፡፡

በመዋቸሞ ዩንቨርሲቲ ማኔጅመንት ዉሳኔ መነሻ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተሰጠዉን ምላሽና የመምህራን መኖሪያ ቤት እንዲገነባ የተፈቀደበት ደብዳቤን እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለማስገንባት ዕቅድ ከያዛቸው የግንባታ ፕሮጀክቶ መካከል ሁለት የመምህራን መኖሪያ ህንፃ የግንባታ ሥራዎችን በቁርጥ ዋጋ ለማሠራት በልዩ ሁኔታ እንዲፈቀድላችሁ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥር ዋዩ/ፕጽ/04/359/14 በተጻፈ ደብዳቤ መጠየቃችሁ ይታወሳል ያለው የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በዚሁ መሠረት በማለት፡-

 የተጠቀሱት የግንባታ ሥራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ቢታሰብ የጨረታ ሂደቱ ከሚወስደው ረጅም ጊዜ አንጻር የግንባታ ፕሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለታለመለት ዓላማ እንዲውሉ ለማድረግ እንደምቸገሩ፣
 የዩኒቨርሲቲው መምህራን በከተማው ውስጥ በኪራይ ቤት እጥረት በከፍተኛ ደረጃ እየተቸገሩ በመሆኑ ጨረታ እንደገና ቢወጣ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ስለሆነ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚፈጥር ጠቅሶ በመፃፍ ከላይ ቀንና ቁጥሩ ከተጠቀሰው ደብዳቤ የተገለጸውን ለመገንዘብ ችለናል ስል በማተት፡-

በመሆኑም ከላይ የገለጻችሁትን እና ቀደም ሲል ይህንን የመምህራን መኖሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያደረጋችሁትን ጥረት በተለያዩ ምክንያቶች አለመሳካቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቅድሚያ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ቁርጥ ዋጋው እንዲጸድቅ በማድረግ ሁለቱን የመምህራን መኖሪያ ህንጻዎች ግንባታ ሥራዎች በቁርጥ ዋጋ እንድታሰሩ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 16/5 መሠረት በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላችሁ ሲሆን አፈጻጸሙን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር መደረግ ያለበት መሆኑን እንገልጻለን ስል ምላሽ ሰጠ፡፡

የመምህራን መኖሪያ ሁለት ህንጻዎችን የቁርጥ ዋጋ ለማሠራት በተየጠቀው በደብዳቤ መነሻ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የጸደቁ የዲዛይንና የቁርጥ ዋጋ በተመለከተ የሚከተለዉን ደብደቤ ለዋቸሞ ዩንቨርሲቲ ላከው፡፡

ቀደም ሲል በቀን 21/02/2015 በቁጥር ዋ/885/15 በተፃፈ ደብዳቤ መሰረት ተቋማችሁ ባጋጠመው የመምህራን መኖሪያ ቤት እጥረት በቁርጥ ዋጋ የመምህራን መኖሪያ ህንጻዎችን ለማስገንባት ከመንግስት ግዢ ባለስልጣን በልዩ ሁኔታ ባገኘው ፍቃድ በ2015 በጀት ዓመት ለሚያስገነባቸዉ የመምህራን መኖሪያ ሁለት ህንጻዎች የቁርጥ ዋጋ እስታቲስቲካል ቀመር ሰነዶችን በአማካሪ ድርጅቱ አኪዩት ኢንጂኔሪንግ የቅድመ ግንባታ ሰነድ በተቋማችን ተገምግሞ እንዲጸድቅ መላካችሁ ይታወቃል። በማለት ባለስልጣን መ/ቤታችን የቀረቡለትን የቁርጥ ዋጋ ሰነዶች ገምግሞ የማስተካከያ እርማት ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፥ በማለት፡-

ስለሆነም የተሰጡት እርማቶች ተስተካክለው በድጋሜ የቀረቡ በመሆናቸው ወደቀጣይ ስራ መግባት ትችሉ ዘንድ ተገምግመው የጸደቁትን ሰነዶች በመ/ቤታችን ክብ መሐተም አረጋግጠን በዚህ ሸኚ ደብዳቤ 2 ጥራዝ የተረጋገጠ የዋጋ ሰነድ ጠቅላላ ዋጋ (260,891,747.75×2) የላክን መሆኑን እናሳውቃለን ስል ህጋዊ ደብደቤ ፃፋ፡፡

ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ህጋዊ መንገድ አልፎ ሥራ የተጀመረው የመምህራን መኖሪያ ሁለት ህንጻዎች የቁርጥ ዋጋ መሠራቱ እና ቀደም ስል በጨረታ አሸንፎ ነገር ግን የጨረታ ማስከበሪያ ጊዜ በመዘገየቱ ምክንያት ጨረታው የተሰረዘበት አቶ ደሳለኝ አስራደ ሥራ ተቋራጭ የመምህራን መኖሪያ ሁለት ህንጻዎች በቁርጥ ዋጋ እንዲሠራ መደረጉን የተመለከቱ ቀደም ስል በጨረታው ተወዳዳሪ የነበሩ አካላት እና በዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልጣን እና ጥቅም ፈላጊ ሀይሎች ጥምረት በመፍጠር ወንጀል ተፈጽሟል በማለት ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት በዋቸሞ የዪንቨርሲቲ ኦዲት ያደረገው ፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የልዩ ኦዲት ሪፖርት አስተያየት እንደሚከተለው አስቀምጧል፡፡

የኦዲት አስተያየት፡-

በቴክኒካል ግምገማው ከተወዳደሩ ስራ ተቋራጮች አንዱ የሆነው ክራፍትስ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማ ያላለፈ በመሆኑ ያላለፈበትም ምክኒያት በግምገማው ተገልፆ እንዲያውቅ ቢደረግም ውጤቱን ባለመቀበሉ እና ቅሬታውን ወደ ግዥ ኤጀንሲ እና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን በማቅረቡ ምክኒያት የጨረታው ሂደት እንዲቆም ተደርጎ ነበር፡፡

ከግዥ ኤጀንሲ እና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጉዳዩ ታይቶ ክራፍትስ ኮንስትራክሽን ቴክኒካል ግምገማውን እንዲያልፍ የተወሰነ ሲሆን ይህንን ውሳኔ ለመስጠት ከአራት ወራት በላይ የፈጀ ሲሆን ዩኒቨርሲቲውም ውሳኔውን ተቀብሎ ቴክኒካል ካለፉ ሥራ ተቋራጮች ምድብ ውስጥ በማስገባት ቴክኒካል ግምገማውን እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡

በዚህ መሰረት ፋይናንሻል ዝቅተኛ ያቀረበው ደሳለኝ አሥራደ ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ያለፈ ቢሆንም የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 20 ቀን 2020 ዓ.ም (10/01/2013) በጨረታ ቁጥር 1001/2013 በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ ባወጣው የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከብዙ መዘግየቶች በኋላ ዩኒቨርሲቲው በቀን 04/12/2014 በቁጥር 04/232/14 በጻፈው ደብዳቤ የቴክኒካል ግምገማውን እና የፋይናንሻል ውድድር ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ የጨረታው አሸናፊ በመሆኑ ውል እንድንፈራረም የተጠየቀ ደሳለኝ አሥራደ ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኮንስራክሽን ግብኣቶች ከ100% በላይ የሚሆን የዋጋ ንረት መከሰቱ በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ሆኖ ሳለ ከዓመት ከአስራ አንድ ወር በፊት በተሰጠ ዋጋ እና የፕሮጄክት ማጠናቀቂያ ግዜ ያለ ምንም ማሻሻያ ሥራውን እንድንሰራ መጠየቅ ድርጅቱን ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርግ ጉዳይ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲፈልግ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል፡፡

ደሳለኝ አሥራደ ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ውል ለማሰር ፍቃደኛ ባለመሆኑ ምክኒያት በማኔጀመንት ውሳኔ ሁለት የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ በቁርጥ ዋጋ እንዲገነባ በመወሰን የቁርጥ ዋጋ ፈቃድ ጥያቄ ለመንግሰት ግዥ ኤጀንሲ እና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የቀረበ ሲሆን መስሪያ ቤቱም በቀን 1/02/2015 ሁለት የመምህራን መኖሪያ ህንፃዎችን በኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቁርጥ ዋጋ አጽድቆ መገንባት እንዲቻል በልዩ ሁኔታ ፈቅዷል፡፡

በመሆኑም የሁለቱን የመምህራን መኖሪያ ህንፃዎችን አስቀድሞ በሚመለከተው አማካሪ ድርጅት ተዘጋጅቶ የነበረውን ለኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቀርቦ ቁርጥ ዋጋ እንዲፀድቅ ከተደረገ በኋላ ህንጻዎችን የሚገነባ ስራ ተቋራጭ ምክረ ሃሳብ ሲጠየቅ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እራሱ ደሳለኝ አስራደ ህንፃ ስራ ተቋራጭ እንዲሰራ የሚል ምላሽ በቀን 19/05/2015 እና በቁጥር 01/መ-34/161/15 ፍቃድ የተሰጠ መሆኑ፣ በመንግስት ኃላፊነት የተሰጣቸው ተቋም ፍቃድ ያገኘ መሆኑ በኦዲት ተረጋግጧል፡፡

በዚህ መሰረት የቀረበውን ጥቆማ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም ስል ፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ የልዩ ኦዲት ሪፖርት በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ታዲያ በዚህ ጉዳይ አቶ ደሳለኝ አስረዳ፣ ዶክተር ሀብታሙ አበበ፣ ዶክተር ታምራት ታገሰ እና ሌሎችም የተሰሩበት አግባብ ህገወጥ በመሆኑ እንዲሁም በአጠቃላይ በዋቸሞ ዩንቨርሲቲ የመምህራን መኖሪያ ሁለት ህንጻዎች ግንበታ ሂደትም ከላይ የገለጽኩትን ህጋዊ መንገድ የተከተለ በመሆኑ የኢፌድሪ ፍትህ ሚንስተር ጉዳያቸዉን በአንክረው ተመልክተው ፍትህ እንዲያረጋግጥላቸው እንጠይቃለን፡፡

ማጠቃለያ

#1ኛ.በአገር ደረጀ የፌደራል ተቋማትን ኦዲት ማድረግና ለተወካዮች ም/ቤት ለመንግስት ውጪ ጉደዮች ኮሚቴ ሪፖርትር የማድረግና ተጠያቂ የሚያደርግ ነገር ካለ ተጠያቂ እንድሆን የማድረግ ስልጠና ያለው የፌዴራል ኦዲት ቢሮ በዩንቨርስቲው የተከናወኑ ሥራዎችን ኦዲት አድርጎ ችግር የሌለበት መሆኑ የተረጋገጠው ቢሆንም ሴረኛ ቡድን በሰጠው ሰነድ በተወሰደው በተሳሳተ ግንዛቤ መሠረት ዩንቨርሲቲውን ኦዲት እንዲያደርግ በህግ ያልተፈቀደውን የገንዘብ ሚኒስተር የውስጥ ኦዲት ሠራተኞ ኦዲት እንዲያደርጉ በማስገደድ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዚዳንት፣ም/ፕሬዘዳንትን፣ ቤተሰቦቻቸውን እና የሰራ ተቋራጩን ጭምር በፖሊስ በማስገደድ ማሰር የተሳሳተ አካሄድ በመሆኑ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአገርቱ ህግ መሰረት ፍትህ እንደሰጥ፤

#2ኛ. መስከረም 2013 የወጣውን የግንባታ ፕሮጅክት የጨረታ ዋጋ በCOVID19 ጫነ ምክንያት በአለም ደረጃም ይሁን በአገር ደረጀ በሁሉም ዕቃዎች ለይ በተለይም በግንባታ ፕሮጄክቶች የመጣውን ለወጥ እየታወቀ በሴራኞች በተዘጋጀው ሰነድነ ጥቆማ ዜጎችን ማሰቀያት የዜጎችን የዜግነት ክበር መሰጠት መሆኑን አውቆ ፍርድ ቤቱ አስቸኳይ ፍትህ እንድሰጥ እንጠይቃለን፤

#3ኛ.የዩኒቨርስቲው አመራሮች ለዩኒቨርስቲው የመንግስት አሰራር በሚፈቅደው መሠረት ተቋሙን እንዲመሩ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣን በሴራኞቹ ሆን ተብሎ በተቀነባበረው ሴራ የተከበሩ ባለሀብትን ጨምሮ የዩኒቨርስቲው አመራሮች እንዲሰቃዩ መፍቀድ አገሪቱ የምትተዳደርበትን ህግን የሚቀር ሆኖ ዜጎችም በህጉ ላይ እምነት እንዳይኖር እና የተደራጀ ልማት አዳካሚ ሀገር አፍራሽ ቡድን ቀድሞ በቀረበው የውሸት ሰነድ የመንግስት አመራሮችንና የሚሠሩ እጆችን ከሥርዓቱ በማስወገድ የአፍራሽ ሀይሎች ሀገር የማዳከም ተልዕኮ እንዲሳካ ስለሚያደርግ መንግስት ለጉዳዩ ትኩርት እንድሰጥ፤

#4ኛ.አሁን በዋቸሞ እየተሰራ ያለው የመምህርን መኖሪያም ይሁን ሌሎች ፕሮጀክቶች ስልጣን ባለው በመንግሥት ባለስልጣናት (በኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣በግዢ እና ንብረት ባለስልጣን እና በዩኒቨርሲቲው 3ተኛ ወገን አማካሪ ደርጅት ተቀጥሮ) የተሰራ ስራ ምንም አይነት የህግም ይህን የአሰራር ክፍተት የሌለ ስራ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አውቆ የተከበሩ ባለሀብት አቶ ደሳለኝ አስራደ እና የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት የግፍ እስረኞች እንደሆኑ ግንዛቤ እንድወስድ፤

#5ኛ.ይህ ሴራ ስራ የሀዲያን ልማት በማፋጠን ምክንያት መሆኑን በመገንዘብ የሀዲያ ምሁራን፣ የፖለተካ አመራሮች እና የሀዲያ ሹመግሌዎች ለታሰሩት ለሀዲያ ምሁራን እና ሀዲያን ለማልማት መጥተው ለታሰራው ባለሀብት ለአቶ ደሳለኝ አስራደ ፍትህ እንድትጠይቁ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

ፍትህ ለግፍ እስረኞች! ፍትህ ለልማት አርበኛና ባለውለታችን ለሆነው ለአቶ ደሳለኝ አስራደ 👨‍⚖️👨‍⚖️👨‍⚖️

አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ...! ሼር ሼር እናድርግባለቤቷ ሀቢብ ባርጊቾ ከድር ነኝ በግሉ የንግድ ማካሄጃ በጀቴን፣በመቀጠል አይሱዙ የጭነት መኪዬን በመሸጥ በመጨረሻም የቤተሰቤን መሰብሰቢያ መኖሪያ...
28/09/2025

አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ...! ሼር ሼር እናድርግ

ባለቤቷ ሀቢብ ባርጊቾ ከድር ነኝ በግሉ የንግድ ማካሄጃ በጀቴን፣በመቀጠል አይሱዙ የጭነት መኪዬን በመሸጥ በመጨረሻም የቤተሰቤን መሰብሰቢያ መኖሪያ ቤት በባንክ በማሲያዝ ሳሳክም ቆይቼ በአሁኑ ሰዓት ግን በሽታው ከሳንባ ወደ አጥንት በማለፍ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ እንድትታከም በመታዘዙ ወንድሞቼ አሁን ላይ ብቻዬን መቀጠል አልቻልኩም በአላህ ፣ በፈጣሪ ስም የህክምና ወጪውን እንድታግዙኝ እያልኩ ለምታደርጉልኝ ድጋፍ አላህ ምንዳውን በዚህ አለምም ሆነ በቀጣዩ አለም በመልካም ይመንዳችሁ እላለሁ።
የንግድ ባንክ ቁጥር
1000013625461
ወንድማችሁ
ሀቢብ ባርጊቾ ከድር እና
የልጆቼ እናት ነጅሚያ ሪዳ ሳሊህ።

አዲስአበባ ከተማ ካስዋቡ እጆች ግምባር ቀደም ሰው 🙏የተከበሩ አቶ ተፈራ ሞላ...የአዲስአበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራአስኪያጆች ጽ/ቤት ምክትል ሥራአስኪያጅ 🙏🙏
28/09/2025

አዲስአበባ ከተማ ካስዋቡ እጆች ግምባር ቀደም ሰው 🙏
የተከበሩ አቶ ተፈራ ሞላ...የአዲስአበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራአስኪያጆች ጽ/ቤት ምክትል ሥራአስኪያጅ 🙏🙏

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፍቅር ያሸንፋል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ፍቅር ያሸንፋል:

Share