10/11/2023
ተመስገን አምላኬ ዛሬ በጣም ደስ የሚል ጠዋት ነው!!ገና በጠዋቱ 11:00 ሰዓት ተነስቸ የሆነ ደስ የሚል መጽሐፍ እያነበብኩኝ ነበር።በሰላም አንቀላፍቶ በሰላም መንቃት ምንኛ ደስ ይላል! እንቅልፍ ከነበርነበት ገቢር ወደ ሚቀጥለው መሸጋገሪያ መጋረጃ ነው።ትያትር ቤት ገብተህ ከአንድ ገቢር ወደ ሌላ ገቢር ለመሔድ መጋረጃ ይዘጋል። እንቅልፍም እንደዛው ነው።ከትናንት ወደ ዛሬ ለመሸጋገር እንቅልፍ ያሰፈልገናል።ካልተኛሁ ትናንትናና ዛሬ ምን ልይነት ይኖረዋል ።የሰው ልጅ ከአምናና ከትናንትና ቁራኛ የሚላቀቀው በመርሳትና በማንቀላፋት ነው።ማስታወስ ጥሩ የሆነውን ያህል መርሳትም ጥቅም አለው። መንቃት ጥሩ የሆነውን ያህል ማንቀላፋትም ጥሩ ነው።ማለዳን ብሎም ቀንን ብሩህ ፣አዲስና በተስፋ የተሞላ የሚያደርገው እንቅልፍ ነው። እናም በሰላም ተኚቸ በሰላም ስለነቃሁ እግዚአብሔር ይመስገን። ምክንያቱም ተኝቶ መነሳት ቀላል ነገር አይደለም።መተንፈስ መቻል ቀላል ነገር አይደለም።መንቀሳቀስ መቻል ቀላል ነገር አይደለም።ምክንያቱም ስንቶች በዚህ ሰዓት እንዳንቀላፉ መንቃት ያልቻሉ፤መተንፈስና መንቀሳቀስ የማይችሉ ሞልተዋልና እኔ ጎን እሱ ፈቅዷልና እትላለሁኝ ተመስገን!!